“ መጨረሻው እየቀረበ ነው “ ሮናልዶ
ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግርኳስ ህይወቱ መጨረሻ እየቀረበ መሆኑን አውቃለሁ በማለት ተናግሯል።
በእግርኳስ ደማቅ ታሪክ ከፃፉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ፖርቹጋላዊ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዛሬው ዕለት 40ኛ ዓመት የልደት ክብረ በዓሉን አክብሯል።
ሮናልዶ በሰጠው አስተያየትም “ መጨረሻው እየቀረበ መሆኑን አውቃለሁ በህይወቴ ከእግርኳስ ውጪ አዲስ ምዕራፍ ይሆናል “ ሲል ተናግሯል።
ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ጫማዬን እሰቅላለሁ የሚል ቀነገደብ ማስቀመጥ እንደማይፈልግ ሮናልዶ አያይዞ ገልጿል።
ሮናልዶ አክሎም “ ወደ ስፖርቲንግ ሊስበን እመለሳለሁ የሚል ሀሳብ የለኝም “ ሲል በቀጣይ በአል ነስር ጫማውን ለመስቀል ስለማሰቡ ፍንጭ ሰጥቷል።
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ከዛሬ ልምምዳቸው በፊት የክርስቲያኖ ሮናልዶን ልደት አክብረዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe