" ማጥቃትም መከላከልም አንተውም “ መሳይ ተፈሪ
⏩ “ የግብፅ አጥቂዎችን በጋራ ለማስቆም እንሰራለን “
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከቀጣይ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በፊት ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በንግግራቸው ወቅት የፈርዖኞቹን ኮከቦች “ እንደ ቡድን ለማቆም አቅደናል “ ሲሉ ስለ እቅዳቸው ተናግረዋል።
አክለውም ስለ አቡበከር ናስር የተናገሩት መሳይ ተፈሪ “ እሱን በደንብ አጣርተን ነው የመረጥነው በጥሩ ጤንነት ላይ ነው “ ሲሉ አስረድተዋል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ምን አሉ ?
- " ግብፅን እንዴት ማጥቃት እና መከላከል እንዳለብን በደንብ ተዘጋጅተናል።
- ለመከላከል አይደለም የተዘጋጀነው ሁለቱንም ማመጣጠን ያስፈልጋል ማጥቃትም አንተውም መከላከልም አንተውም።
- ከተጨዋቾች ምርጫ ጋር በተያያዘ ለእኛ የአጨዋወት ታክቲክ ይስማማሉ ያልናቸውን ተጨዋቾች መርጠናል።
- የግብፅ አጥቂዎች በግል ያላቸው ችሎታ የሚታወቅ ነው እኛ ግን በቡድን ስራ ማጥቃቱንም መከላከሉንም በግል ያላቸውን ነገርም ለማስቆም እንሰራለን።
- አቡበከር ናስርን በተመለከተ መረጃዎችን ወስደናል ከእሱ ጋር ያለበትን ሁኔታም ተነጋግረን ነው ጥሪ ያቀረብንለት።
- አቡበከር ናስር በጥሩ ጤንነት ላይ ነው ብቁ ከሆነ ምን ማድረግ እንደሚችል የታወቀ ነው ፤ ከመጣ በኋላም ጥሩ ነገር እያሳየ ነው።
- ከዚህ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እንፈልጋለን ያለንበትን ደረጃ ማሻሻል እንፈልጋለን እቅዳችን እሱ ነው።" ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe