#ተደፍረሽ ታውቅያለሽ ወይ?
ማኅበረሰባዊ ሱሳይድ
እንደ እናት፣እንደሴት ፣ እንደ እህት ያለፉት ሳምንታት ለእኔ ቀላል አልነበሩም። የሴት ልጅ እና የህፃናት ህይወት በኢትዮጵያ ዉስጥ የሲኦል ያህል መራራ ነዉ ። ለዛዉም በሚወዱት፣ በሚያምኑት ፣ በሚያከብሩት የቅርብ ሰዉ ፣የቤተሰብ አባል ነዉ መደፈር የሚደርስባቸዉ ። በአባት፣ በወንድም፣በአጎት፣ በእንጀራ አባት፣ በቤተሰብ ጎደኛ እና በቅርብ ዘመድ! ከዛም ተርፎ ለማን ይነግሩታል የባህል ተፅእኖዉ ፣ ፍራቻዉ፣ ዛቻዉ እና የሚሰጠዉ ስም ሌላ ጠባሳ ነዉ የሚተወዉ ።
የሰው ልጅ ጭካኔ በአንዲት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የ7 ዓመት ብላቴና ሄቨን ላይ መፈጸሙን ከሰማሁ በኋላ እረፍት አጣሁ፤ በሰላም ልተኛ አልቻልኩም፤ ያላዋረሁት ሰው የለም፤ ተደጋገመ በዛ፤ ያስጨንቀኝ ጀመር፤ ነፍሴ እረፍት አጣች፤ ከማገኘው ወገኔ ጋር ሁሉ ከዚህ ሌላ ርዕስ ማውራት አቃተኝ፤ ዕንባዎቼ ያለምንም ስሜታዊ መነካት በድንገት ይፈሳሉ፤ ራሷን መከላከል እና መጠበቅ የማትችል፣ ክፉና ደጉን የማታውቅ፣ የምታገኘው ሁሉ ትልቅ ሰው ደግ እና አባት የሚመስላት፤ ያችን ቀን የተደገሰላት ክፋት እንደነበረ አላወቀችም፤ ልጅ አደለች፤ አሳዛኙ እና ሃገራዊ ውርደትን ያከናነበው ድርጊት ተፈጸመባት፡፡
ማህበራዊ ሚዲያው ተቀባበለው፤ በከፈትኩና ባየሁ ቁጥር በተለያዩ ፎቶዎቿ ታሪኳ የሚነገርላት ብላቴና አንጀቴን አላወሰችው፤ ቀኗ እየቆየ ሲሄድ እንኳን ነፍሴ ከተያዘችባቸው ጥያቄዎች ልታርፍ አልቻለችም፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን ህፃናትና እህቶቼ ሰቆቃ እንደሆነ የታወቀ ነው፤ በተለይ ደግሞ በጦርነት ድባብ ስር ሆነው ቀናቸውን ለሚገፉ እህቶቻችን አሰብኩ፤ አገራችንን በጭካኔ ዳመና ስር ያለች የእህቶቻችን የሰቆቃ ምድር ሆና ታየችኝ፤ የተለያዩ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፤ እንዴት ይህን ማኅበራዊ ጋኔል ማስቆም ይቻላል? እንዴት በደለኞቹን መቅጣት ይቻላል? እንዴትስ ተበዳዮቹን መካስ እና ወደ ሙሉ ሰውነት መመለስ ይቻላል? ብዙ ብዙ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፤ የችግሩን ጥልቀት እና ስፋት ማጥናት ፈለኩኝ፤ ነፍሴ በሄቨንና በሄቨኖች ጩኸት ተይዛለች፤ ጆሮዎቼ የነገ እና የከነገ ወዲያ ሰለባዎችን ጩኸት እና ቃተቶ እየሰማች አስቸገረችኝ፤
ያኔ ነው ችግሩን በቀላል መንገድ መዳሰስ እና መረዳት፣ ቆይቼ ደግሞ ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ጥሩ ጥናት ማካሄድ የሚመኘው የልቤ መሻት ፈነዳ እና ቅድሚያ ሰጥቼው መጠናት አለበት ብዬ ወሰንኩ፤ ብዙ የጥናት ልምድ የለኝም፤ ነገር ግን ጥናት ማለት ጥያቄ ማንሳት እና መልስ መፈለግ እንደሆነ ይገባኛል፤ የተወሳሰበ ሳይንስ ሊሆን ቢችልም ቀለል ባለ መልኩ ልሰራው እንደምችል አሰብኩ፤ ብዙ ጥያቄዎች አወጣሁ አወረድኩ፤ በመጨረሻ ግን አንዲት ቀላል ጥያቄ መረጥኩ፤ “እህቴ ሆይ ተደፍረሽ ታውቂያለሽ ወይ?” የምትል ባለ አምስት ቃላት ጥያቄ ነች፤ ፍጹም ወዳልገመትኩት እና ወዳላሰብኩት የጨለማ ዋሻ እና ብዙዎች በዝምታ ወደሚጮሁበት ጽልመት ያመራችኝ ጥያቄ፤
አትጠይቁ እየተባልን ባደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ እንዲህ አይነቱን ከትላንት እና መራራ ትዝታ ጋር የሚያላጋ ጥያቄ ማንሳት ከባድ ነው፤ ደግሞስ ማን ነች የህይወቷን ገመና እና የተቀቀበረ ቁስል ከፍታ ማውራት የምትፈልገው? ማንስ ነች ይህን ጥያቄ እንደ “ቁርስ ትበያለሽ” አይነት ጥያቄ በቀላሉ እና ወደ አእምሮዋ ጓዳ ዘው ብላ ከዘመናት በፊት ወይም በቅርብ የተዘጋን በር ከፍታ የምታሳየኝ? ፈራሁ፤ ድፍረት ይሆንብኝ ይሆን? ግን ደግሞ ነውርን ፈርቼ የሃገሬን ሴቶች መከራና እና ቁስል እንዴት እያየሁ ዝም እላለሁ፤ ከብላቴናዋ ሄቨን የበለጠ ምን ሊደርስብኝ ይችላል? ኃላፊነት የለብንም ወይ?
ለማንኛውም ያለ የሌለ ድፍረቴን አሰባስቤ በቅርበት የማውቃቸውን አምስት ሴቶች መረጥኩና ስማቸውን ጻፍኩኝ፤ ስልካቸውን አወጣሁ፤ ማስታወሻ ደብተርም ያዝኩ፤ ስፈራ ስቸር ሰ….. ጋር ደወልኩ፤ የሄቨን ጉዳይ ሰሞኑን ያወራነው ወቅታዊ እና አስደንጋጭ ክስተት ስለነበረ ከሁለታችንም ህሊና ያልጠፋ እና በየዕለቱ ከሚለቀቁት ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች እያነሳን ማውራት ቀጠልን፤ ሁለታችንም እየተነፋረቅን ነበር፤ እንደምንም ወደ መረጋጋት ስንመለስ ስፈራ ስቸር ያቺን ባለ አንድ አረፍተነገር ጥያቄ በትህትና እና በጥንቃቄ አነሳሁላት፤
“አንቺ ግን እንደው አገራችን ስትኖሪ ሳትፈልጊና ሳታስቢው እንዲህ አይነት ክስተት ያጋጠማት ጓደኛ ታውቂያለሽ?” አልኩ ቢቸግረኝ አቅጣጫዬን ወደ ሌላ ሰው ቀይሬ፤ ስልኩ ጸጥ አለ፤ የተቋረጠም መሰለኝ፤ “ወይኔ ጉዴ” አልኩኝ በልቤ፤ የሳግ ድምጽ ሰማሁ፤ ከሃገር ከወጣች ብዙ ዓመት አስቆጥራለች፤
“ሁሉም ጓደኞቼ ተደፍረዋል፤ እኔም አላመለጥኩም፤ ምን አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ እንደኖርን፤” አለችና ለቅሶዋን ቀጠለችው፤ ደነገጥኩኝ፤ አንዳንዶቹን ጓደኞቿን አውቃቸዋለሁና እነሱን መገመት አቃተኝ፤ ግን ጓደኛዬ እዛ ላይ አላቆመችም፤ እሷም ራሷ የደረሰባትን ነገረችኝ፤ ለዛውም በቅርብ ቤተሰብ ዘመድ፤ ዝርዝሩን ለመጻፍ አቅምም ፈቃደኛነቱም የለኝም፤
ቆየሁና ሌላዋ ጋር ደወልኩ፤ ከዛም ሌላዋ ጋር ከዛም ሌላዋ ጋር፤ አምስቱም ጓደኞቼ ለማንም ነግረውት የማያውቁትን የህይወታቸውን ጥቁር ጠባሳ ከፍተው ቁስላቸውን አሳዩኝ፤ በጣም ደነገጥኩ፤ ሌሎች አምስት ጓደኞቼን ስም ጻፍኩ፤ ቁጣዬ እየጨመረ ሄደ፤ ሃዘኔም፤ ቁጣዬና ሃዘኔ እየተደበላለቁ ሃሳቤን መሰብሰብ አቃተኝ፤ ስልኩን አቁሜ ትንሽ መረጋጋት እና ማሰብ ፈለኩኝ፤
-----ከዕረፍት መልስ------
ከረጅም ዕረፍት በኋላ ስልኩን እና ማስታወሻ ደብተሬን አነሳሁ፤ ደወልኩ፣ ትንሽ አወራን፤ እራሷ ስለሰሞኑ አጀንዳ አነሳች፤ ጊዜ ሳትሰጠኝ የሷንም ሳግ ሰማሁት፤ ተያይዘን አነባን፤ ወደ ልባችን ስንመለስ ጥያቄውን አነሳሁላት፤ “እህቴ ሆይ አንቺስ ተደፍረሽ ታውቂያለሽ ወይ?” እሷም ጸጥ ብላ ቆየች፤ ሳጓን ሰበሰበችና “አዎ” አለችኝ፤ ዝርዝሩ ለህትመት የሚመች አይደለምና ልተወው፤ ግን ሌላ አስለቃሽ ታሪክ ነው፤ በጣም ልብ የሚሰብር ።
እንደቀላል የጀመርኩት ባለ አንድ ጥያቄ ጥናት ?ሳምንቱን ተቆጣጥሮኝ የሰነበተው ሃምሳ የሃገሬ ሴቶች ጋር አስደወለኝ፤ እያንዳንዱ ስልክ ቀላል ሂደት አልነበረም፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ከሃምሳዎቹ ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማት ያመለጠችው አንዲት ሴት ብቻ ነች፤ አዎ አንዲት ሴት ብቻ፤ ሳምንቴን ከባድና የስቃይ አደረገው፤ ከዚህ በኋላ ሌሎች ሴቶችን መጠየቅ ፈራሁ ፣ ከእያንዳንድዋ ሴት በስተጀርባ ያልተነገረ ፣ያልታከመ፣በየጊዜዉ የሚያመረቅዝ ህመም አለ።
አብዛኞቹ ማለት ይቻላል በለቅሶ እና ሳግ የታጀቡ ናቸው፤ እኛ በተለያየ ጊዜ ምናልባትም ደህና ይባሉ በነበሩት ዘመናት ከሃገር ወጥተን እዚህ ውጭ አገር ያለነው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይሄን ያክል የምናወራው ነገር ካለን፣ አገራችን ላይ በዚህ በከፋ ጊዜ ያሉት እህቶች ምን ያክል እየተሰቃዩ ይሆን?
የሀምሳዎቹ ሴቶች ታሪክ
*ሁለቱ በማያዉቁት ሰዉ የተደፈሩ (አንደኛዋ በ 12 አመትዋ አንደኛዋ በ15 አመትዋ ) አንድዋ ወልዳለች