🦋💚…………
"ይሆናል ……! " "አይ አይሆንም! "ይደረጋል……" "አይ አይደረግም "…………
"እያልሽ ነው እራስሽን ያሳደግሽው ፣እናም ባንቺ ደስተኛ ነኝ ፣ ኮራብሻለው "…… ይኽን ሲለኝ ሊሰናበተኝ አርባ አምስት ቀናት ይቀሩት ነበር………
"አሁን እረፍት ይሰማኛል ፣ የምትፈልጊውን ታውቂያለሽ ፣ ለመኖር ዝግጁ ነሽ ፣ ያለኔ ፣ ያለማንም ………"
ተሳስቶዋል ያለሱ ለመኖር ዝግጁ አልነበርኩም ፣ ደስታውን በማየት ውስጥ ነው እራሴ ላይ የሰራሁት ፣ ያበበውን መሰራት አይቶ እየተደሰተ ማይኖርልኝ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ምኖረው ?……ምክንያቴ እሱ ነው ……እንደማስበው ፣ እንደሚያስበው ጠንካራ አደለውም …… ላሳካ ስላሰብኩት ነገር ነግሬው ፣ ትችያለሽ በርቺ ብሎ ሳይመልስልኝ በምን ተስፋ እሮጣለው ?…… አዎ ያለማንም መኖር እችላለው ፣ ያለሱ ግን እንዴት ኖራለው ?
እያወራልኝ ማስበው ይኼን ነበር
" ምኞቴ አንቺ ለኔ እንደ ሺ እድቶኚ ሳይሆን ፣ አንቺ ለራስሽ ሺ እንድትሆኚ ነበር…… ከህይወት ምትፈልጊውን እንድታውቂ ፣ እንደ ልጅነትትሽ ጨለማን ብትፈሪም ከጨለማው ለመውጣት ግን እያለቀሽ ሰው ምትጠሪ ሳይሆን እራስሽ ለጨለማው መውጫ መፍትሔ እንድታበጂ ነበር ፍላጎቴ ፣ ያን አይቻለው ……በቃ !"
……ከጨለማው መውጣት ምፈልገው እኮ አንተ ስላለክ ነው ፣ አንተን ለማየት ፣ ስታረጅ ፣ ከልጅ ልጆችህ ጋር ስትጫወት " ኦ ሚገርም አያት እኮ ነው ያለን " ሲሉ ለመስማት ፣ እናታቹ እኮ እያልክ ልጅነቴን ስታወራላቸው ፊትክ ላይ ያለውን ደስታ ለማየት ነው ከድቅድቁ ሚያስመልጡኝን ብዙ ብልሃቶችን የገነባሁት ፣ እንዳልወድቅ አቋቋሜን ያሳመርኩት ከኔ ቀጥሎ ስላለው ስምክ ስላለኝ ክብር ነው ……… ትላለች ነፍሴ ለራሷ ………ግን ንግግሩን በመልሷ አታቋርጠውም ፤ ያለሱ ጠንካራ መሆኔ ደስታ ከሰጠው ለምን ያን ደስታ ነጥቀዋለው ?
:
:
. ኖሮ ነው ያኖረኝ ፣ እጆቹ እየኮተኮቱኝ ሲሻክሩ ፣ "ለኔ ነው" ይለኛል ላንቺ ነው ብሎ ውለታ እደሆነ ነግሮኝ አያውቅም. .ለሚፈቀር ነፍስ የሚሰራ ሁሉ ለራስ እደሆነ እያስተማረኝ ነበር . . ታላቅ ዓለም ነው !!
. . .ቃላቶቹ ከአንደበቱ ሲወጡ የነፍሴ አክናፋት ዙሪያዩን ያቅፉታል ፣ ቃሉ የተስፋ ዜማ ታዜማለች ፣ በአዲስ ብርታት ኃይልም ትሞላለች ። ሁሉን መሆን ይችላል፣ ሁሉንም ማስሆን ይችላል. .
ከቅርፊቴ በብልሃት ተፈልፍዬ ጫጩነቴን በማስተዋል እዳልፍ መንገድም ሂወትም ሆኖኛል ………
ነፍሴ አደገኛ ተናዳፊ እባብ ከማይደርስባት የመንፈስ ከፍታ ላይ እድትሆን ጥበባዊ ስሪቱ አለበት………
ይኽ ሰው ነው ህይወቴ ላይ የጎደለው ……… ይኽን አባት ነው ነፍሴ ያጣቹ ………ይኽን መጠርያ ነው ሞት የነጠቀባት ………
:
:
እንዳልኩት አበቃልኝ ብዬ ነበር ፣ ግን እሱ እንዳለው ቆምኩ ፣ ሰሪ ከስሪቱ በላይ አዋቂ ነውና ……"ትቆምያለሽ !" አለኝ ቆምኩ
አንዳንዴ ባይኖሩም ፣ ለመኖር ግን አዲስ ሃይል የሚሆኗቹ ታላቅ ነፍሶች አሉ ……… አባቴ !
/ትዝታ / @tiztawe
#ፍትሕ ለሴት ልጆች