💫🦋…………
"የሚፋቀሩ ሰዎች አይጋቡም "……ይች ትንሽዬ ዓ.ነገር እንደ ክፋት ሚከብደኝ እኔን ብቻ ይሁን?…ሟርት ነው ሚመስለኝ … እሺ ቆይ የተጋቡ ሰዎች አይፋቀሩም ማለት ነው ?ወይስ አንዱ በአንዱ ፍቅር ውስጥ ህይወት ስለሚያገኝ ነው ? ………
ያም ሆነም ይኼ የኔና የሱም ታሪክ ተፋቅረው ካልተጋቡት ውስጥ ይመደባል ……
በአብሮነታችን ወቅት ………
ተፋቅረው ስላልተጋቡ ጓደኞቹ ሲያወራልኝ ፣ ስለኛ እጣፋንታ እያሰብኩ በመሃል ነፍሴን ስረብሻት እንደነበር አልነገርኩትም ……
"ይዋደዱ ነበር እኮ ግን ሁለቱም አገቡ ……"
"ሲያናድድ "…
"ትንሽ ኢጎዋቸውን ላለማሸነፍ ብለው …እሷ ሁለት ልጅ ወልዳለች …"
"እምም ……"
፣
፣
ከአመታት ደማቅ የፍቅር እውነት በኃላ የኛም ታሪክ በሌሎች ህይወት ውስጥ ተቋጨ ……
ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ፣ ቆንጆ ምሳ በላን ፣ የአራት ኪሎን ሁካታ ባልሰማ እረስተነው እጅና እጃችንን አነባብረን ከኛ ጣዕም ያነሰ ቀዝቃዛ ሻያችንን ኡፍ እያልን ጠጣን ፣ በእግሮቻችን የቤተ መንግስትን ጎዳናዎች እየቆጠርን ተያየን ፣ የኛ ጊዜ ሲያረጅ ስለተሰሩ መዝናኛዎች ከፋን ፣ ባረኩት ሂል ሳቀ ፣ በተቆረጠው ፀጉሩ አሾፋኩ …… ጣዕሙን ማላስታውሰውን ኬክ በላን ……በመጨረሻም እስከአሁን ድረስ ሳየውም ሲሸተኝም በሚረብሸኝ የበቆሎ ሽታ ታጅበን …"አፈቅርሻለው "……"አፈቅርካለው " ተባብለን ተለያየን ……… ለካስ እንደዚህም ተባብሎ መለያየት ይቻላል ?
ልክ እንደፈረሰው ሰፈር የፈረሰ ታሪካችንን ያለአሻራ ለማስቀመጥ የተገናኘንበት የመጨረሻዋ የህይወታችን የአብሮነት ቀን ትመስለኛለች ያቺ እለት ……
ያስፈራው እንደነበረ በጊዜ ሰንሰለት ላይ የፈጠርናቸውን ና የታጋራናቸውን ታሪክና ትዝታ ብቻ ሆነው ቀሩ ……ከእንሁን ሆነንን ነበር በሚል ቀዝቃዛ ዝምታ ተዋጡ ……
ከተመሰቃቀለ ልቤ ውስጥ እንደተረሳ ወይም እንደተደበቀ ሚስጥር ከራሴም ሸሽጌ ደበኩት ……
አበቃ ……
/ትዝታ /@tiztawe