አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ የትምህርቱ ዘርፉ ለሚያደርገው ሪፎርም አቅም እንደሚሆን ተጠቆመ፤ በአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ይህ አዋጅ በዚህ መንገድ ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው የትምህርት ዘርፉ አሁን ለደረሰበት ደረጃ በሚመጥን ነው ብለዋል። አዋጁን ለማስፈጸም ከክልልና፣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው የትምህርት ሴክተሩ ባለሙያዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ አሳታፊ በሆነ መልኩ በቀጣይ ደንብና መመሪያ እንደሚዘጋጅም ገልጸዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም የትምህርት አዋጁ ለሴክሩ የሚኖረውን ፋይዳ ሲያብራሩ የትምህርት አካታችነትን፣ ተደራሽኝነትን፣ ፍትሃዊነትንና ጥራትን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል። ይህ አዋጁ ለሚደረገው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም አቅም እንደሚሆን ጠቁመው የዜጎችን የመማር መብት የሚያረጋግጥና ሀላፊነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መሆኑን ተናገረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ-ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ እንደገለጹት ደግሞ አዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ የመንግስት ዘርፉን ብቻ ሳይሆን የግል ዘርፉንም የሚያበረታታ መሆኑን ተናገረው አዋጁ ወደትግበራ ሲገባ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ አወንታዊ ለውጥ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
በውይይቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች በውይይቱ ተሳታፊ ሆነዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers