❤️በቤተ ክርስቲያን 5 አይነት አክሊላት አሉ❤️
1 አክሊለ ሰማዕት
ይህ አክሊል ሰማእታት በተጋድሎ የሚያገኙት አክሊል ነው ቅዱስ
ጳውሎስም ስለዚህ አክሊል ሲናገር ሃይማኖቴን ጠብቄለው ሩጫዬን ጨርሻለው ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ብሎ ጠቅሶታል
2 ጢሞ 4+6-7
በተመሳሳይ ባለራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስም እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጥሃለው ብሎ የተናገረው ስለ ሰማእታት አክሊል ነው ራዕ 2+10 ክርስቶስም አክላሎሙ ለሰማእት ተብሏል እመቤታችንም አክሊለ ሰማእት ትባላለች
2 አክሊለ ሶክ (አስኬማ መላእክት)
ይሄ አክሊል የአባ እንጦንዮስ አክሊል ሲሆን መነኮሳት የሚያደርኩት አክሊል ነው ይሄ አክሊል በምንኩስና ዓለምን ከናቁ በኋላ የሚገኝ ነው ክርስቶስ በዕለተ አርብ የተቀበለው አክሊለ ሶክ የሚታሰብበት ሲሆኔ ይሄን አክሊል ያደረጉ መነኮሳት እንደ መላእክት በንጽሕና በቅድስና ስለሚኖሩ አስኬማ መላእክት ተብሏል
3 ተክሊል (የተክሊል አክሊል)
ይህ አክሊል በድንግልና ኑረው ለሚጋቡ ኦርቶዶክሳውያን የሚደረግ የድንግልና ምልክት የሆነ አክሊለ ከብካብ ነው ደናግል ላልሆኑ ፈጽሞ የማይደረግ ነው
4 አክሊለ ነገሥት ይህ አክሊል ለነገሥታት ብቻ የሚደረግ ነው ሰሎሞን ሲነግሥ ሲቀባ የተደረገለት አክሊል ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ወአክሊሉ ለሰሎሞን የሰሎሞን አክሊል ነሽ ብሎ የተናገረው የነገሥታት አክሊል እመቤታችን እንደሆነችና ነገሥታት ሲነግሢ ተቀብተው አክሊል እንደሚያደርጉ ለመግለጽ ነው
5 አክሊለ ካህናት
ይህ አክሊል በክህነት የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናት የሚያደርርጉት አክሊል ነው
ክህነት ለሌለው ፈጽሞ የማይደረግ ሲሆን የካህናት አክሊል አሰራሩ ከላይ 4 ማዕዘን ሲሆን የዲያቆናት አክሊለም በአሰራር ከካህናት የተለየ ክብ ነው ዲያቆን የቄሱን አክሊል ፈጽሞ ማድረግ አይችልም አምስቱ አክሊላት እነዚህ ናቸው
አሁን አሁን ግን የካህኑን እና የዲያቆኑን አክሊል ሴቶች ሳይቀር አድርገውት እየታየ ስለሆነ እጅግ የሚያሳዝን ነው
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ ቸል ተብሎ እየታየ ነው ስለዚህ የሊቃውንት ጉባኤ ይሄን ጉዳይ እልባት ሊሰጥበት ይገባል።
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ