የ"ዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ" ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ሊቃውንት ጉባኤ አስታወቀ።
+++++++++++++++++++++++++++++
ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም
****አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጉባኤ ጥር 23ቀን 2017 ዓ.ም "የዝክረ ኒቅያ ጉባኤን" ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ለማካሔድ መርሐ ግብር መያዙ ይታወሳል።
ሆኖም ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ማካሔድ ይቻል ዘንድ መርሐ ግብሩን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ በማስፈለጉ ጉባኤው ከሚያዚያ 20-24 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲካሔድ መወሰኑን ሊቃውንት ጉባኤ ገልጿል ስለሆነም ጉባኤው በተያዘለት መርሐ ግብር መሰረት የሚካሔድ ይሆናል።
ሊቃውንት ጉባኤ ያስተላለፈው ውሳኔ ደርሶናል እንደሚከተለው ይነበባል፦
ማሳሰቢያ
ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም.
የዝክረ ኒቅያ ጉባኤ የሚካሄድበት ቀን ማስተካከልን ይመለከታል።
የቅዱስ ሲኖዶስ መጋቢ የሆነው ሊቃውንት ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተወሰነለት መሠረት፦ በአሁኑ ሰዓት ውይይትና ምክክር በሚያስፈልጋቸው የትውልድ ዐበይት ጥያቄዎች ላይ በመምከር ያለፈውን
ለማጽናት፣ የሚመጣውን ለማቅናት፥ ሃይማኖትና ቀኖናን ጠብቆ ለማስጠበቅ የሊቃውንት መሰባሰብ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ “ዝክረ ኒቅያ” በሚል
ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ ሊቃውንት ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለማካሄድ ታቅዶ እንቅስቃሴሲደረግ ቆይቷል።
ሆኖም፦
1ኛ) ጉባኤው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንት የሚታደሙበት እንደመሆኑ፥ በተለይ በጠረፉ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ
መምህራንን በበቂ ቊጥር ለማካተት እንዲቻል፥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ፤
2ኛ) በጥር ወር በርካታ ሀገራዊ ክንውኖችና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት በየአካባቢው የሚካሄዱ በመሆናቸው የጉባኤው መካሄጃ ጊዜ እንዲስተ ካከል ከአንዳንድ አህጉረ ስብከት በተደጋጋሚ አስተያየት በመሰጠቱ፤
3ኛ) ጉባኤው ከዘመናት ቆይታ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድና በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይቶችን በማካሄድ፥
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚጠቅም የውሳኔ ሐሳብና አስተያየት የሚያቀርብ፥ አልፎም የአቋም መግለጫ የሚያወጣ በመሆኑ፤የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ከመካሄዱ ጥቂት ቀደም ብሎ ከሚያዝያ 20-24ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲካሄድ በሊቃውንት ጉባኤ መወሰኑን በአክብሮትእየገለጸን፤ የአህጉረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች የተሳታፊዎች ልየታ መመሪያ እስከሚደርሳቸው ድረስ ለጉባኤው ይመጥናሉ የሚሏቸውን መምህራን በመለየት ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ አደራ እንላለን።
ሊቃውንት ጉባኤ
በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያግኙን፤ ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ።
1. ድረገጽ:-
https://eotceth.org2. ፌስ ቡክ ገጽ:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation
3.https://
m.facebook.com/story.php?story_fbid=507787748855477&substory_index=507787748855477&id=61565158745873&mibextid=ZbWKwL4. በቴሌግራም ቻናላችን#
https://t.me/DimtseTewahido19275.
https://t.me/DimtseTewhido6. eotcprdepartment@gmail.com