በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሊባኖስ የፓኖሲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አናንያ ኩጃኒያን ሊባኖስ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ተገደሉ !ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አራም ቀዳማዊ በጳጳሱ ግድያ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። የሊባኖስ ሪፐሊክ ፕሬዝዳንት ጄኔራል ጆሴፍ አውን በሊባኖስ የአርመን ኦርቶዶክስ ጳጳስ የማኅበረሰብ ጉዳዮችን በመምራት ላይ ሳሉ በተፈፀመው ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።
ፕሬዝደንቱ ወንጀሉን አጥብቀው እንደሚያወግዙ የገለጹ ሲሆን የፀጥታ አካላት የወንጀል ሁኔታን ለማወቅ ፣ወንጀለኞችን ለመያዝ እና ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንዲተላለፉ ለማድረግ ምርመራቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የደኅንነት ምንጮች እንደገለፁት ጳጳሱ ትናንት ከሰዓት በኋላ መጥፋታቸው ተነግሯል። በምርመራው ወቅት የጸጥታ አካላት አስከሬናቸውን በቤታቸው ውስጥ በማግኘታቸው መገደላቸውን አረጋግጠዋል።
©ተ.ሚ.ማ