Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የተለያዩ ሙሀደራ እና የኪታብ ደርሶች የሚለቀቅበት ቻናል ነው
መረጃዎችን ለማግኘት በፌስቡክ like ይበሉ 👇
fb.me/AbuZekeriya8
YouTube subscribe ያድርጉ ፣ የተለያየ ፈትዋ ፣ አጫጭር ምክር ፣ እና ወቅታዊ ጉዳዮች የሚላክበት) 👇
http://www.youtube.com/c/AbuZekeriya

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አላህ ያዘዘውን ሁልጊዜ የሚተገብርና ከተከለከለው ነገር ሙሉ ለሙሉ የተከለከለ ሰው :-
_ዱኒያ ላይ ሲኖር የልብ-ሰላምና የሕይወት መረጋጋትን የተላበሰ አካል ይሆናል::
-ጣረ-ሞት ላይ ሲሆን በመላእኮች አማካኝነት ጀነትን የሚበሰርና ሰከራተል-መውትን እንዲቋቋም ይደረጋል:
-ኣኸራ ላይ ደግሞ የአላህን ውደታና ጀነትን በማግኘት የጀሊሉን ሽልማት የሚጐናፀፍና የታላቅ ዙፋን ባለቤት የተከበረ ባሪያ ይሆናል::
https://t.me/UstazKedirAhmed


ኢማናችን ሲደክም ልቦናችን ዝገት ሲገጥመው ከምንጠቀማቸው መፍትሄዎች ውስጥ:-
የእነዚያን ደጋግ ቀደምቶች አላህ ዘንድ የነበራቸውን የፍራቻ ጥግ መመልከት:
የአምልኮ ተግባራት ላይ ያላቸውን ጥንካሬ ማስተዋል:
ለዚህች አለም የነበራቸውን ቸልተኝነት:
መልካምነታቸውን በአጠቃላይ ታሪኮቻቸውን በማስተዋልና በመማር ወደ ነፍሳችን መለስ ብለን ቀልባችንን ለማከምና ኢማናችንን ለማደስ ከሚጠቅሙ መንገዶች ናቸው::
https://t.me/UstazKedirAhmed




አላህን መፍራት ትልቅ ሀብት ነው::
ብልህ ሰው ነፍሱን የመረመረና ከሞት ቡኃላ ላለው ሕይወት የተዘጋጀ ነው::
ከአላህ ብርሃንም በመቃብር ውስጥ ብርሀን ሊሆነው የሚችልን ነገር የወሠደ ነው::
ዐይናማ የነበረ ባሪያ አላህ እውር አድርጐ እንዳይ ቀስቅሰው ይፈራል::
ጥበበኛ ሰው መልካምን ና እውነትን ይናገራል::
ለአላህ የሆነ ሰው ሞንም የሚፈራው ነገር አይኖርም::
አላህ በእርሱ የተመካን መጠጊያም ከለላም ይሆነዋል::
https://t.me/UstazKedirAhmed




አነስ ቢን ማሊክ (ረ ዐ) እንድህ ይላል:-
👉ለአስር አመታት የአላህ መልእክተኛን እንከባከብ ነበር "በአላህ ይሁንብኝ ለእኔ በጭራሽ ኡፍ"ብለውኝ አያውቁም:ለእኔ ብለውኝ አያውቁም" ለምን?ይህን አልተገበርክም:
ለምን?እንደዚህ ተገበርክ?
👏👏👏👏እጅግ ገራሚ ስብዕና ከሰው ልጅ ሁሉ ፈርጥ ከሀቢቡና ሙሀመድ[ዐሰወ]
🍇🍇ይህን ድንቅ ስብዕና አስመልክቶ የእውቀት ባለቤቶች እንድህ ይመክራሉ:-
👂👂በተለይ ወደ አላህ መንገድ ጥሪ በማድረግ ላይ ለሚሳተፋ ና እወቀትን ቀሳሚ በሆኑ አካላቶች ግድ ይሆናል:_
☝️ይህን ሀድሥ ሊያነቡት:
👆ሊያስተነትኑ:ሊያጤኑት
👆በእርሱ ሊሰሩ/ተግባራዊ ሊያደርጉት
ምክንያቱም ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህ መልእክተኛው ሲገልፃቸው እንድህ ይላል:
☔️☂☔️በአላህ እዝነት ምክንያት ለእነርሱ አዘንክላቸው ግርጭርጭና ልበ-ደንዳና ብትሆን ኖሮ"በዙሪያህ የነበሩት በተበታተኑ ነበር"
ግና የእኛ ውድ ነብይ" እነዚያን እንቁ ትውልዶች ያፈሩትና ይህን ውብ እምነት ያንሰራፋት በዚህ ማራኪ ስብዕናቸው ነበር::
🎤🎤🎤ወደ መልእክተኛው መንገድ የሚጣራ አብዛሀኝው ይህን መንገድ መከተል ለምን ተሳነው??????? ነው ሌላ ሞደል አለለት??
⚖⚖⚖ረቡና በመካከለኝዋ መንገድ ላይ አድርገን⚖⚖⚖⚖
https://t.me/UstazKedirAhmed


🎤እውቀትን በአግባቡ ቀስሞ አሸናፊና የላቀ ወደሆነው አላህ ጥሪ ማድረግ:-
☘☘ይበልጥ የተከበረ መቆሚያ
🕌ከስራ ድርሻ ይበልጥ የላቀ ስራ
✈️ወደ አላህ ከሚያቃርቡ መንገዶች ይበልጥ በላጭ የሆነ
#ባጠቃላይ በእውቀትና በጥበብ የተካነ ወደ አላህ የሚደረግ ጥሪ የመልእክተኞችና የነብያቶች የስራ ድርሻ ነበር::
ለሙስሊምች የሚቆረቆር ሊላበሰው ግድነው!!
https://t.me/UstazKedirAhmed


طلب العلم شاق ولكن له لذة والعلم لا ينال إلا على جسر من التعب والمشقة ومن لم يتحمل ذل العلم ساعة تجرع كأس الجهل طول حياته

ما أحلا هذا الكلام قاله بعض أهل العلم ينبغي كتابته بماء الذهب
ከፊል የኢስላም ሊቃውንቶች እንድህ ይላሉ:-
🌾 እውቀትን መማር አስቸጋሪነው ነገር ግን ልዪ ጣዕም አለው🥛🥛🥛
🌾 በችግርና በድካም ድልድይ ላይ ተሻግረን እንጅ አይገኝም🚍🚍🚍
የእውቀት ፍለጋን ለአፍታ ያክል መታገስና መቻል ያቃተው እድሜ ልኩን
የመሀይምነት ዋንጫን ሲጐነጭ ይኖራል::
♦️ይህን ንግግር ምን አስዋበው በወርቅ ውሃ ሊፃፍ የሚገባው ንግግር ነው♣️https://t.me/UstazKedirAhmed/




ዱንኒያ እንደ ተሰባሪ
ሸክላ ናት
ሀብት :ስልጣን:ዝና
የህይወታችን ዋስትና ሊሆኑ አይችሉም
ዋስትናችን መልካም ሥራ ብቻ::
https://t.me/UstazKedirAhmed/


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አላህ ይጠብቀን ጀሀነም እኮ ከምድር ታች ነች::
በእርግጥ የአማኞች ልቦና ይህ ሲመለከት ይበልጥ ጌታውን ይፈራል::
ነፍሣችንን እንመርምር!!
https://t.me/UstazKedirAhmed/8296


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
መጨነቅ አሁን ነው!! አሁንስለተከሰተው እሳት ሳይሆን ወደፊት ስለሚጠብቀን የጀሀነም እሳት!!
"አንተ በምድር ና በሰማያት በእውነት የምትመለክ አምላክ ሆይ"
በክስተቶችህ ተምረን ለአኸራ ህይወት የምንዘጋጅ አድርገን ያመውላህ!!


["ዱዓ "] ማንኛውም ነገር በዱዓ ይቀየራል::
ዱዓ ጠቃሚ መድሀኒት:በሽታን አስወጋጅ,
"ዱዓ "የመከራ ጠላት: **

ይከላከለዋል:ያክመዋል:ከመውረድ ይከላከለዋል:ያስወግደዋል:በወረደ ጊዜ ያቀለዋል::
## ዱዓ የሙዕሚን መሣሪያ##]

**የተጠሉ ነገሮችን በማስወገድ ረገድ ና ተፈላጊ ነገሮችን በማስከሰት ውስጥ ጠንካራ ምክንያት ነው::ነገር ግን ተፅእኖ ሊዘገይ ይችላል::ከሚያዘገዩት ምክንያቶች ውስጥ:-
- ዱዓው ደካማ ሊሆን ይችላል
-ዱዓው አላህ ዘንድ ላይወደድ ይችላል በውስጡ ላለው ወሰን መተላለፍ,
-የልቦና መድከም በአላህ ከመደገፍ,
-መጠጥ:ምግቦች: አልባሳት :ባጠቃላይ አስፈላጊ የሆኑ መጠቀሚያዎች በሀራም ነገሮች የተገነቡ ሲሆኑ ዱዓ ተቀባይነት አይኖረውም::
*** ሰለዚህ ከሽርክ:ሀራም ከሆኑ ነገሮች ነፍሣችንን በማፅዳት,
*** አላህን በመፍራት,በመከጀል,ተስፋ በማድረግ,
*** አላህ በማወደስና በማመስገን እንድሁም
***በመልካም ስሞቹ ና በውብ መገለጫወቹ ችክ ብለን መማፀን ይኖርብናል ::

****አንተ ሁሉን ሰሚ አዋቂ የሆንክ አምላክ "ለእኔ መልካም መስሎ ከሚጐዳኝ ነገር ጠብቀኝ"

https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/UstazKedirAhmed


እምነትህን በሀያሉ አምላክ ባደረክ ቁጥር ይበልጥ ጠንካራና የመልካም ስብዕና ባለቤት ትሆናለህ::
አሏህ ሆይ" ጠንካራ አማኝና
የውብ ሥነ-ምግባር ባለ ቤት አድርገን ያከሪም


Forward from: قناة دروس فضيلة الشيخ أبو عمار أول بن أحمد الخميسي
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

በሸይኽ አወል ቢን አሕመድ፦
በተከታታይ ሲሰጥ የነበረው የቁርአን ተፍሲር ትምህርት በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ በመሆኑ፡ዛሬ"የአቂደቱል ዋሲጥያ" ትምህርት ይጀመራል።ስለሆነም፡በቦታው ተገኝቶ መከታተል የፈለገ፡#አምራች መስጅድ ፎቅ ላይ ስለሚሰጥ መሳተፍ ይችላል።#በአካል መገኘት ለማትችሉ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed

በእራሳና ምክንያት መልእኩቱን ቶሎ ማድረስ ባለመቻሌ አፍወን።


ሙሓደራ 219

ስለ ወቅታዊ መሬት መንቀጥቀጥ አጭር ምክር

🚦 የቂያማ ምልክት 

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed/8288


እድሜህ እያለፈ ፈተናዎች እየበዙ አስፈሪ ነገሮች እየተስተዋሉ አንተ ግን አንዳችም መልካም ነገር አለማድረግህን ባወክ ጊዜ የዛን ቀን አልቅስ :: ጌታችን ሆይ
እንደኛ ተግባር ሳይሆ በአንተ ሰፊ እዝነት ይቅር በለን ያረብ 🤲🤲


Forward from: الشباب السلفيين

አስፈሪ ጊዜ ላይ ደርሰናል!!
---------------------------
ይህ እየሆነ ያለው 🇪🇹ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

...እውነት ግን አሏህ ምን ሊለን ፈልጎ ነው⁉️

በሰሞኑ የሚታየውና የሚስተዋለው ጉዳይ ያስፈራል ምድር የተቆጣች "በቃኝ" ያለች ትመስላለች።

በምስሉ እንደምትመለከቱት ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሲስተዋል የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ያለ ማቋረጥ ከቀጠለ በኋላ እነሆ በምታዩት መልኩ
ውሃ፣
ጭስና
እሳት ከምድር ወደ ላይ እየፈነዳ ይገኛል።

➢አሁንስ አንገሰፅም!?
➢አሁንስ ወደ አሏህ አንመለስም!?
➢አሁንስ አንቶብትም!?
➢አሏህ በዚህ ክስተት ሊነግረን የፈለገው ነገር አለ!!
➢ሊያስታውሰን ሊያሳየን የፈለገበት ምክንያት አለው።

ወደ አሏህ እንመለስ ጉዳዩ ሸሪዐዊ መዳኒት እንጂ ሳይንሳዊ መላምት አያስፈልገውም።

🤲አላህ ሆይ ታረቀን🤲
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi


Forward from: الشباب السلفيين
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በአፋር እሳተ-ገሞራ!!

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi


Forward from: الشباب السلفيين
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
لاحول ولا قوة إلا باالله
إنا لله وإنا إليه راجعون

በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው እሳተ ገሞራ‼️

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ ከባድ የእሳተ-ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል።

ይህ ክስተት በአፋር ክልል እየሆነ ያለ ነገር ነው።
አሏህ ሀገራችንን ይጠብቅልን አሚን

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi

20 last posts shown.