የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሹ ኃይል በኦምዱርማን ከተማ ባንድ የገበያ ቦታ ላይ ፈጽሞታል ላለው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትና ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ ማስገባቱን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የሱዳን ባለሥልጣናት፣ ቡድኑ በዚህ ጥቃት በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ዓለማቀፍ ሕግጋትን ኹሉ ጥሷል በማለት መክሰሳቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
የሱዳን መንግሥት በዚኹ አቤቱታው፣ ቡድኑ በእዚህና መሰል ጥሰቶች፣ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ ሊፈረጅ የሚያስችሉትን መስፈርቶች አሟልቷል ብሏል ተብሏል።
https://t.me/voa_amharic1