እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም ጉዳይ ላይ ለመወያየት ወደ ኳታር ተደራዳሪ ቡድን ልትልክ ነው
የትራምፕ እና የኔታኒያሁ ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄደው የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ሊደረግ ባለበት ወቅት ነው።የኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት ዛሬ ቀደም ብሎ እንዳስታወቀው የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን በመጪዎቹ ቀናት በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ለመነጋገር ወደ ኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ መሆናቸዉን አስታዉቋል።
ቡድኑ በስምምነቱ ላይ "ለመቀጠል ቴክኒካዊ ዝርዝሮችን" እንደሚወያይ በመግለጫው ተነግሯል፡፡ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኳታር ከግብፅ እና ከአሜሪካ ጋር በመሆን በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሽምግልና ላይ ነች።ትራምፕ ከእስራኤል እና ከሌሎች ሀገራት ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ያደረጉት ውይይቶች "እድገት እያሳዩ" ብለዋል፡፡ነገር ግን ምንም ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡
ፕሬዚዳንቱ ግን የተኩስ አቁም ስምምነት እርግጠኛ አለመሆኑን አምነዋል።ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሰላሙ እንዲሰፍን ምንም አይነት ዋስትና መስጠት እንደማችሉ አክለዋል።ሰኞ እለት ከኔታንያሁ ጋር የተገናኙት የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ አክለው እኛ በእርግጠኝነት ለሰላም ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
https://t.me/voa_amharic1