ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ "የጋዛን ሰርጥ እንደምትቆጣጠርና" እና "በባለቤትነት እንደምትይዝ" ዛሬ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ካነጋገሩ በሗላ በመግለጽ "የፍልስጤም ህዝብ ሌላ ቦታ መኖር አለበት" የሚለውን ሀሳብ ማስተዋወቃቸውን ቀጥለዋል::
ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስተያየታቸው የሰጡት ትራምፕ "በጋዛ የሚገኙት ፍልስጤማውያን በዳግም ግንባታ ሂደት ውስጥ ማለፍ የለባቸውም:: እዛ በአሳዛኝ የህልውና ሁኔታ ሲኖሩ ቆይተዋል” ብለዋል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ፣ በኦቫሉ ቢሮቸው ውስጥ ከናታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ፕሬዝዳንቱ "ፍልስጤማውያን በሌላ ቦታ 'በቆንጆ ቤቶች' ውስጥ 'በቋሚነት መቋቋም' አለባቸው"ም ብለዋል።
ትራምፕ "አሜሪካ የጋዛ ሰርጥን ትቆጣጠራለች:: ስራ እንሰራለን:: እኛ ባለቤት እንሆናለን:: በዛ አካባቢ ላይ ያሉትን አደገኛ ያልተፈነዱ ቦምቦችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን እናመክናለን:: የተበላሹ ሕንፃዎችን እናስወግዳለን:: እናስተካክላለን:: ለአካባቢው ሰዎች ያልተገደበ ቁጥር ያላቸው ስራዎችን እና መኖሪያ ቤቶችን የሚያቀርብ የኢኮኖሚ ልማት መፈጠር" አለበት ሲሉ በንግግራቸው አሰምተዋል::
"ወደ ኋላ አትመለሱ:: ወደ ኋላ ከተመለሳችሁ ወዳለፋት መቶ አመት ወደ ነበረው መንገድ መመለስ ነው" ሲሉም ለፍልስጤማውያን መልዕክት አስተላልፈዋል::
ፕሬዚዳንቱ "የሌላ ሉዓላዊ ግዛትን ለመረከብ ምን ስልጣን አለዎት?" በሚል በጋዜጠኞች ተጠይቀው፣ ጉዳዩን ለወራት በቅርበት ሲያጠኑት እንደቆዩ ገልጸው "ቦታውን ለረጅም ጊዜ በባለቤትነት መያዝ የሚለውን አይቼዋለሁ፣ ይህም በመካከለኛው ምስራቅ ክፍል፣ ምናልባትም በዛ አካባቢ በአጠቃላይ ትልቅ መረጋጋትን እንደሚያመጣ ነው ያየሁት" ብለዋል ።
https://t.me/voa_amharic1