በትረምፕ ትዕዛዝ በርከት ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ የትምህርት ሚንስቴር ሠራተኞች እረፍት እንዲወስዱ ታዘዙ!
የፌደራሉ የሠራተኞች ማኅበር እንዳመለከተው በዩናይትድ ስቴትስ ትምህርት ሚንስቴር ውስጥ የሚሠሩ ቁጥራቸው የበዛ ሠራተኞች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአወጡት እና በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ‘ብዝሃነት፣ ፍትሃዊነት እና አካታችነት’ የተባሉ ፕሮግራሞችን ለመሰረዝ በሰጡት ትእዛዝ መሰረት መፈጸሙን አመልክቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት ሠራተኞች ፌዴሬሽን የትምህርት ሚንስቴር ሠራተኞችን የሚወክለው 252 የተባለው ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት ሸሪያ ስሚዝ በትላንትናው ዕለት ሲናገሩት ደሞዝ እየተከፈላቸው ለጊዜው እረፍት እንዲወስዱ የታዘዙት ሠራተኞች ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ፤ ወይም በምን ምክንያት ይህ ውሳኔ ሊሰጣቸው እንደቻለ ግልፅ አይደለም’ ብለዋል።
ቢያንስ ቁጥራቸው 55 የሚደርሱ ሠራተኞች ቀደም ሲል ትራምፕ በፈረሙት የፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ መሰረት ወዲያውኑ እንደሚፈጸም የሚገልጽ የኢሜል መልዕክት ባለፈው አርብ ደርሷቸዋል።ትራምፕ ‘የትምህርት ሚኒስቴርን እዘጋለሁ’ የሚል ቃል በመግባት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ይታወሳል።
https://t.me/voa_amharic1