የእነዚህ ፖሊሶች ጉድ ተመልከቱ‼
ስንት ጀግና ለሙያቸው ታማኝ ፓሊሶች ባለበት ተቋም ውስጥ እንደነዚህ አይነት ደግሞ ዘራፊዎችም አሉ።
👇
ሀሰተኛ የወንጀል ምርመራ መዝገብ በማደራጀት አንድን ባለሃብት በማስፈራራት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ አራት በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና ሁለት ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ ያቀረበባቸው ተከሳሾች
📌1ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው መኩሪያ ማሞ ወይም (መስፍን ማሞ)፣
📌 2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቂሊንጦ ፖሊስ ጣቢያ የክትትል ቲም ሀላፊ ኢንስፔክተር ዘለቀ ጥላሁን፣
📌3ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዘውዴ አሰግደው፣
📌4ኛ በፖሊስ ጣቢያው የወንጀል መርማሪ ዋ/ሳጅን መለሰ ማርቆስ፣
📌 5ኛ በፖሊስ ጣቢያው የክትትል አባል ምክትል/ሳጅን አጅቦ ተፈሪ እና
📌6ኛ በግል ስራ የሚተዳደረው ተገኔ ሀ/ማርያም ወልዴ ናቸው።
ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር (2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች የመንግስት ስራ ላይ በመስራት ላይ እያሉ ከ1ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ባለሃብት ግለሰብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ሀሰተኛ የወንጀል ጥቆማ አቅራቢ ሆኖ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ጥቆማ ያቀረበ በማስመሰል ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች ከህጋዊ አሰራር ውጭ የምርመራ መዝገብ እንዲደራጅ አድርገው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል
በዚህም ግለሰቡን አስረው “የወንጀል ምርመራው እንዲቋረጥልህ ገንዘብ መክፈል አለብህ” በማለት አስፈራርተው የግል ተበዳዩ ለጊዜው ባልተያዘ ምስጋና ዓለሙ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር
📌 በነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም180 ሺህ ብር፣
📌በመስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም 300 ሺህ ብር ገቢ እንዲያደርግላቸው ማስገደዳቸው በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ለጊዜው ባልተያዘ ለማ ባጃ በተባለ ግለሰብ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ
📌በመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም 200 ሺህ ብር ገቢ ያስደረጉ በመሆኑን በክሱ ዝርዝር ላይ የተገለጸ ሲሆን፤
📌 በጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች አማካኝ የግል ተበዳዩን ከህግ አግባብ ውጭ በጣቢያው አስረው ካቆዩ በኋላ በ4ኛ ተከሳሽ ስም ከአዋሽ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ 200 ሺህ ገቢ ያስደረጉ መሆኑ በክሱ ተገልጿል።
በ6ኛ ተከሳሽ ስም ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 300 ሺህ ብር ገቢ ካስደረጉ በኋላ ከዚሁ ገንዘብ ላይ በ4ኛ ተከሳሽ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ 200 ሺህ ብር ማስተላለፋቸው ተጠቅሷል።
ከዚሁ ገንዘብ ላይ ደግሞ ለ3ኛ ተከሳሽ እና ለ2ኛ ተከሳሾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳባቸው ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የተላለፈላቸው መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።
ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱ የሚያስገኘውን አጠቃላይ ውጤት በመቀበል በሀሰተኛ የምርመራ የወንጀል መዝገብ በማደራጀት ግለሰቡን ከህግ ውጪ በማሰር በአጠቃላይ ከግል ተበዳዩ 1 ሚሊዮን 180 ሺህ ብር በመቀበል ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆኑ ተጠቅሶ በልዩ እና ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል።
ዐቃቤ ሕግ ከክሱ ጋር የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዝርዝር አያይዞ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው የክሱ ዝርዝር እንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via:- FBC
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
💎አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed