መግለጫ ተሰጥቷል‼ ሙሉ ዝርዝሩ ከታች ቀርቧል
==============================
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጥላቻ ንግግር ግጭት ለመፍጠርየሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡
በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።
ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይበትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡
በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።

በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይከመካረሩ በፊትየጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስድ
2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤
3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም
4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡
ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ