TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Wazema Media / Radio

19 Sep, 21:17

Open in Telegram Share Report

ለቸኮለ! ቅዳሜ፣ መስከረም 9፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር፣ በኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ባለው የሥራ ሥምሪት ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሠራጩ ይገኛሉ አለ።
ሚንስቴሩ፣ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ እንደተዘጋ፣ ዜጎች ለሥራ እየተሠማሩ እንዳልኾነና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ለጥቂቶች ብቻ እንደተዘጋጀ በማስመሰል በመሠራጨት ላይ ያሉ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ "መሠረት የለሽ" ናቸው ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚንስቴሩ፣ ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት ሂደቱ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ አማካኝነት አሁንም እየተካሄደ ይገኛል ብሏል። "መሠረት የለሽ" እና "አሳሳች" መረጃዎችን የሚያሠራጩ አካላትን በማጣራት ሕጋዊ እርምጃ ለመውሠድ በዝግጅት ላይ መኾኑንም ሚንስቴሩ ጠቅሷል።

2፤ አፍሮ ፒክስ፤ በድረ ገጽ ለዕይታ በሚያቀርባቸው የኢትዮጵያ ፊልሞች 100 ሺሕ ዕይታ ለሚያገኙ 3 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር ለመክፈል ከፊልም ሠሪዎች ጋር ውል እየገባ ይገኛል። ድርጅቱ፣ ለአንድ የፊልም ዕይታ 0 ነጥብ 03 ዶላር እንዲሁም ለ10 ሺሕ ዕይታ 300 ዶላር ክፍያ ይፈጽማል። የድርጅቱ አሠራር፣ ፊልም ሠሪዎች ፊልማቸውን በሌሎች አማራጮች ጭምር ለዕይታ የማቅረብ መብት የሚሠጥና የፊልሞች የቅጂ መብት የባለቤቶቻቸው ኾኖ እንዲቀጥል የሚፈቅድ መኾኑንም ዋዜማ ተረድታለች። በድረገጹ ላይ ፊልሞችን ለዕይታ ለማቅረብ፣ ፊልሙ የእንግሊዝኛ የትርጉም ጽሑፍ ያለው መኾኑ አንዱ መስፈርት ነው። ድርጅቱ፣ በድረገጹ በወር ከሦስት እስከ አምስት የሚደርሱ ፊልሞችን ለዕይታ ለማብቃት ማቀዱንም ሠምተናል።

3፤ ደቡብ ሱዳን፣ በናይል ወንዝ ላይ የኃይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት እንደማትፈራ አስታወቀች። የአገሪቱ የኢነርጂ ሚንስትር አጎክ ማኩር፣ መንግሥት በወንዙ ላይ ግድብ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ መኾኑን መናገራቸውን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሚንስትሩ፣ ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ተፋሰስ አካል እንደመኾኗ ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብቷ የተጠበቀ ነው ማለታቸውንም ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል። ግብጽ ጭምር የተካተተችበት የናይል ተፋሰስ አገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት፣ በናይል ወንዙ ላይ ግድቦችን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንዲሠሩ ስምምነት ላይ መድረሱን ሚንስትሩ ጠቅሠዋል ተብሏል። ደቡብ ሱዳን ይህን አቋሟን የገለጠችው፣ ግብጽ በታችኛው የናይል ተፋሰስ ላይ ተጨማሪ ግድብ መገንባቱን እንደምትቃወም እየገለጠች ባለችበት ወቅት ላይ ነው።

4፤ አሜሪካ በሶማሊያ ለተሠማራው የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ድጋፍ ለሚያደርገው የተመድ ቢሮ የምትሠጠውን የገንዘብ ድጋፍ ባንድ ተጨማሪ ዓመት ለማራዘም መወሠኗ ተሠማ። አሜሪካ ለተመድ ድጋፍ ሠጪ ቢሮ ከታኅሳስ ጀምሮ ድጋፍ መስጠት እንደምታቆም ባለፈው ሃምሌ ማስታወቋን ተከትሎ፣ የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ቀጣይ እጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ነበር። ኾኖም አሜሪካ ሞቃዲሾ የሚገኘው የተመድ ቢሮ ከቀጣዩ ጥር ጀምሮ ባሉት 12 ወራት ውስጥ ሥራዎቹን ቀስ በቀስ እንዲቀንስ አሜሪካ ዕድል መስጠቷ ታውቋል።

እንዲሁም፤

1፤ የድምጻዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ "ገሪር " የተሠኘ ስያሜ የተሠጠው አዲስ የሙዚቃ አልበም መስከረም 16 ቀን ለአድማጮች ሊቀርብ እንደሆነ ተሠምቷል። ይህ የሙዚቃ አልበም አስር የሙዚቃ ሥራዎችን የያዘ ነው።

2፤ የገጣሚ ሳሚያ ጡሃ "እምወድህዎይ" የግጥም መጽሐፍ ነገ እሁድ መስከረም 10 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ሲግናል አካባቢ በሚገኘው ዴማ ሆፕ ሪልስቴት ህንጻ ይመረቃል። [ዋዜማ]

22.6k 0 11 60
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot