ለቸኮለ! ሰኞ፣ መስከረም 11፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ፖለቲከኞች፣ ፋኖን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትንና ሕወሃትን ጨምሮ ሰባት የታጠቁ ቡድኖችና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ትናንት በይፋ በመሠረቱት "ትብብር" ዙሪያ ለዋዜማ በሠጡት ቃል የተለያዩ አስተያየቶችን አንጸባርቀዋል። የኢሕአፓ ፕሬዝደንት አብርሃም ኃይማኖት፤ ፓርቲያቸው ለአገሪቱ ችግር ብቸኛው መፍትሄ ውይይትና ድርድር መኾኑን እንደሚያምንና ማንኛውንም የትጥቅ ትግል እንደማይደግፍ ነግረውናል። የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት አስተባባሪ ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በበኩላቸው፣ የትብብሩ ዋነኛ ዘዋሪ የኤርትራ መንግሥት ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ባንጻሩ፤ ፓርቲያቸው በትብብሩ ላይ ገና አቋም እንዳልያዘ በመጥቀስ፣ ለጊዜው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የፈረመው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ክንፍ ተወካይ ማስረሻ ሠጤ ደሞ፣ ትብብሩ የፋኖ መሪዎችን ጨምሮ ከሕወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸውና በ"ኢትዮጵያዊነት ስም" ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሰዎችን ማንነት ያጋለጠ ክስተት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሠጥተዋል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሠን አስመላሽ ኮሚቴም፣ "በትብብር" ስም የአማራን ታሪካዊ ግዛቶችና ማንነቶችን ለመንጠቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እቃወማለሁ ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል። ኮሚቴው፣ ትናንት ፋኖ እና ሕወሃትን ጨምሮ ሰባት ቡድኖች በፈጠሩት "ትብብር" ዙሪያ የፋኖ መሪ የሠጡትን መግለጫ እንደሚቃወም አስታውቋል።
2፤ የፌዴራል ስታትስቲክስ አገልግሎት፣ የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ አስተዳደሮች ከሕዝብ አሠፋፈር ጋር የተያያዘ ጥናት ካለፈው ሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ይፋዊ ባልኾነ መንገድ ቤት ለቤት እያካሄደ መኾኑን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ የተቋሙ ባለሞያዎች፣ የቤተሠብ አባላት ብዛት፣ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ሐይማኖት፣ የትምህርት ደረጃ፣ የጋብቻ ሁኔታና ወርሃዊ ገቢ እንዲሁም ባንዳንድ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶችን የቦታ ስፋት መረጃዎች እያሰባሰቡ መኾኑን የዳሰሳ ጥናት ጥያቄ የቀረበላቸው ነዋሪዎች ነግረውናል። ባለሙያዎቹ የመረጃው ዓላማ የከተሞቹን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ናሙና ለመውሠድ እንደሆነ እንደሚገልጹላቸው ነዋሪዎች ነግረውናል።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች፣ የመረጃው ዓላማ የሕዝብ አሠፋፈርና ሥብጥርን እንዲሁም የነዋሪዎችን ትክክለኛ መረጃ ለይቶ መሠነድ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አንድ የተቋሙ ከፍተኛ ሃላፊ በበኩላቸው፣ የሥራው ዓላማ ለአገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ካርታና የቦታ ዝግጅት እንጂ ከሕዝብ አሠፋፈር ወይም የአስተዳደር ወሠኖችን ከመቀየር ጋር የተያያዘ አይደለም የሚል ምላሽ ሠጥተዋል።
3፤ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ)፤ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለፈው ሳምንት በተቀሠቀሠ ግጭት የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገለጠ። ድርጅቱ፣ የአራቱ ቁስለኞች በክልሉ ውስጥ ካቋቋመው ኩሌ የጤና ጣቢያ ከደረሱ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ጠቅሷል። የጤና ጣቢያው በግጭቱ ከባድና ቀላል የመቁሠል ጉዳት የደረሠባቸውን 88 ሰዎች መቀበሉንና 13 ቁስለኞ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጋምቤላ ሆስፒታል እንደተላኩ ድርጅቱ ባወጣው አዲስ መረጃ ላይ አመልክቷል። ድርጅቱ፣ በግጭቱ የተሳተፉ አካላት በሲቪሎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
4፤ በአዲግራት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አገረ ስብከት፣ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የጫነ የጭነት ተሽከርካሪው ትናንት ከሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ በድሮን እንደተመታበት አስታወቀ። የጭነት ሽከርካሪው የድሮን ጥቃት የተፈጸመበት፣ ሽሬ ከተማ ለተጠለሉ 56 ሺሕ 200 ያህል የውስጥ ተፈናቃዮች 36 ሺሕ ሜትሪክ ቶን እህል እና 5 ሺሕ 100 ሜትሪክ ቶን ዘይት ለማድረስ በመጓዝ ላይ ሳለ እንደነበር ቤተክህነቱ ባወጣው መግለጫ ገልጧል። ቤተክህነቱ፣ ባለሥልጣናትና ሌሎች አካላት የረድዔት ጫኝ ተሽከርካሪዎችን ደኅንነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስከብሩ፣ ለረድኤት ሠራተኞች፣ ለእርዳታ ጫኝ ትሽከርካሪዎች፣ ለረድኤት መተላለፊያ መስመሮችና ለዕርዳታ ሎጅስቲክ አቅራቢዎች ግልጽ እና አስተማማኝ የደኅንነት ዋስትና እንዲሠጡ እንዲሁም የሲቪሎችን ሕይወትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን አደጋ ላይ ከመጣልና የነፍስ አድን የእርዳታ አቅርቦቶችን ከማስተጓጎል እንዲቆጠቡ ጠይቋል። ከመንግስት ወገን የተሰጠ መልስ የለም።
5፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን፣ ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሠነ ጊዜ እገዳ ጥያለሁ አለ። ባለሥልጣኑ፣ ማንኛውም ዲጂታል፣ የብሮድካስትም ኾነ የሕትመት መገናኛ ብዙኀን ጣቢያውን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም ጣቢያው የሚያሠራጫቸውን ይዘቶች እንዳያሠራጭ ወይም እንዳያስተጋባ መከልከሉን ገልጧል። ይህን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም መገናኛ ብዙኀን ላይ ባለሥልጣኑ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በግጭት ማቆም ስምምነቱ ማግስት በጣቢያው ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ ተመልሶ ቆይቷል ያለው ባለሥልጣኑ፣ የአገርንና ሕዝብን ደኅንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ጽንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልዕክቶች በተከታታይ ሲያስተላልፍ ቆይቷል ብሏል።
የትግራይ ቴሌቪዥን በበኩሉ፣ የባለሥልጣኑ ውንጀላ "ከእውነታ የራቀ" እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚፈጸም "አፈና" ነው በማለት እገዳውን ኮንኗል። በኢትዮጵያ እውነተኛ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ እንዲመጣና የሕዝቦች የዘመናት ትስስር ተመልሶ እንዲያብብ እየሠራ መኾነን የጠቀሠው ጣቢያው፣ ባለሥልጣኑ እገዳውን እንዲያነሳ ጠይቋል፡፡
6፤ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ የሠራተኞቹን ዝቅተኛ ደመወዝ ከ6 ሺሕ ብር ወደ 10 ሺሕ ብር ከፍ አደረገ። ኩባንያው፣ ከተያዘው ወር ጀምሮ ለሠራተኞቹ ደመወዝ ጭማሪ 3 ቢሊዮን 244 ብር መመደቡን ሥራ አስኪያጁ ጀማል አሕመድ ይፋ አድርገዋል። ኩባንያው ባሁኑ ወቅት 80 ሺሕ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ የኩባንያው ባለቤት ሼህ መሃመድ አል አሙዲ ኩባንያው ተጨማሪ 40 ሺሕ ሠራተኞች እንዲቀጥር መመሪያ መስጠታቸው ባለፈው ሳምንት እንደተገለጠ ይታወሳል።
7፤ ግብጽ፣ ደቡብ ሱዳን በዋይት ናይል ወንዝ ላይ ለመገንባት ያቀደችውን ግድብ እደግፈዋለሁ አለች። ግብጽ ለደቡብ ሱዳን ግድብ ድጋፏን የሠጠችው፣ ግድቡ ቢገነባ ሊደርስባት የሚችለው ጉዳት እጅግ ዝቅተኛ እንደኾነ በግምገማ ስላረጋገጠች መኾኑን የአገሪቱ የመስኖ ሚንስትር ሃኒ ስዊላም ተናግረዋል። ስዊላም፣ የደቡብ ሱዳን ግድብ በናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይና በሁሉም የተፋሰሱ አገራት ምክክር ተደርጎበት የሚካሄድ መሆኑንም ገልጸዋል። ግብጽ አባል የኾነችበት የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ በወንዙ ላይ መገንባት ይችላሉ ብሎ ካጸደቃቸው የተፋሰሱ አገራት ፕሮጀክቶች መካከል፣ አራት የኃይል ማመንጫ ግድቦች ይገኙበታል። [ዋዜማ]