TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Wazema Media / Radio

22 Sep, 20:11

Open in Telegram Share Report

ለቸኮለ! ማክሰኞ፣ መስከረም 12፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የዓለም አገራት የሰላም አመላካቾች ከ163 አገራት 138ኛ ደረጃ ተሠጣት። ኢትዮጵያ፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ ዘንድሮ አንድ ደረጃ አሻሽላለች። ለአገራት የሰላም ጠቋሚ ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የኢኮኖሚክስና ሰላም ኢንስቲትዩት፣ ከ5 ከያዘው ነጥብ ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 6 ነጥብ ሠጥቷታል። አገሪቱ ዝቅተኛ ነጥብ ያገኘችባቸው ጠቋሚዎች፣ ፖለቲካዊ ሽብር፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላት ግንኙነት፣ ውስጣዊ ግጭቶች፣ የውስጣዊ ግጭቶች አስከፊነት እና የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች ተደራሽነት ናቸው። ኢትዮጵያ በደረጃው ከተካተቱ 44 የአፍሪካ አገራት ያገኘችው 35ኛ ደረጃ ነው።

2፤ ተመድ፣ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለጠ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቲፋኒ ዱጃሪክ፣ በአገሪቱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መፍጠራቸውን፣ የድሮን ጥቃቶች መደጋገማቸውንና የጸጥታ ችግሮች መቀጠላቸውን ጠቅሠው፣ ድርጅቱ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ትናንት ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዱጃሪክ፣ የአገሪቱ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የጸጥታ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ ከሚያደርጉ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል። ወታደራዊ ርምጃ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ወይም ነባር ቅራታዎችን አይፈታም በማለት ጭምር ዱጃሪክ አጽንዖት ሠጥተዋል።

በተያይዘ፣ በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኦዞኒያ ኦጄሎ፣ በኢትዮጵያ ሰላም፣ መተማመንና አብሮነት እንዲጠናከሩ ጥረቶች እንዲደረጉ ጠይቀዋል። ሃላፊው፣ የአገሪቱ ባለ ድርሻ አካላት ልዩነቶችን በንግግር እንዲፈቱና ለሰዎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሠጡ ጥሪ አድርገዋል።

3፤ የአሜሪካ የእንደራሴዎች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ግሪጎሪ ሚክስ፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ አለማራዘሟ ትክክል አይደለም በማለት ተቹ። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከፍተኛ የግጭት ስጋት እንዳለ የገለጹት ሚክስ፣ በሁለቱ አገራት ላይ አሜሪካ የጣለቻቸው ማዕቀቦች መነሳታቸው የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል በማለት ተችተዋል። ሚክስ፣ በትግራይ ክልልና አካባቢው የታጠቁ አካላት በጤና ጣቢያዎችና በረድኤት ሠራተኞች ላይ በመገናኛ ብዙኀን ያልተዘገቡ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትግራይ ክልል በፍጥነት እያሽቆለቆለ ለሄደው የጸጥታ ሁኔታ ትኩረት አልሠጡም በማለት ጭምር የወቀሱት ሚክስ፣ ፕሬዝዳንቱ ሁሉም አካላት ቀጠናዊ ሰላም ለማስፈን የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

4፤ የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች 6 የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሰኞ'ለት ማሠራቸውን ዋዜማ ሠምታለች። መምህራኑ በታጠቁ ዩኃይሎች ተይዘው የተወሠዱት፣ ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጪ ከሚገኝ ምግብ ቤት መኾኑን ምንጮች ነግረውናል። የትምህርት ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወትም፣ በትግራይ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የሚያደፈርሱና መደበኛ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተጓጉሉ ርምጃዎች እየተወሠዱ ናቸው በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ኮንነዋል። ክንደያ፣ የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እስር፣ "የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን ኅልውናና የተማሪዎችን የወደፊት እድል አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ብለዋል፡፡

5፤ "መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን" የተባለው ተገንጣዩ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክህነት፤ ከሠሞኑ መነጋገሪያ በሆኑት የትግራይ የኃይማኖት አባት ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ተጠየቀ። አክሱም ለሚገኘው የቤቱክህነቱ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤውን የጻፉት፣ የቤተ ክህነቱ ከፍተኛ ዓቃቤ መንበርና የሽሬ እንዳሥላሴ ጳጳስ አባ ጴጥሮስ መሆናቸውን ዋዜማ ከደብዳቤው ላይ ተመልክታለች። አንድ የኃይማኖቱ አባት ከአንዲት ሴት ጋር ጾታዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ የሚያሳየውና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል፣ በካህናትና ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና መረበሽ መፍጠሩን ደብዳቤው ያትታል።

6፤ ከሁለት ወር ከግማሽ በላይ የ2019 ዓ፣ም በጀቱን ሳያጸድቅ የቆየው የሸገር ከተማ አሥተዳድር፣ ዛሬ ማክሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጀቱን ማጽደቁን ዋዜማ ሠምታለች። አስተዳደሩ በጀቱን ሳያጸድቅ የቆየው፣ በውስጡ ተፈጥሯል ከተባለው የመልካም አሥተዳደር ችግርና የሃብት ብክነት ጋር በተያያዘ ምክንያት መሆኑን ተረድተናል። አሥተዳደሩ በ2018 የተያዘለትን የመደበኛ በጀቱ 2 በመቶ መጠባበቂያ በጀት ለከልሉ ሳያሳውቅ በመጠቀሙ፣ የዘንድሮው በጀት ሳይጸድቅ ለመቆየቱ ዋነኛ ምክንያት እንደነበር ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ተናግረዋል። የከተማ አሥተዳደሩ ምክር ቤት፣ የተያዘው ዓመት በጀት ከ47 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን መወሠኑን አረጋግጠናል።

7፤ ግዙፉ የዓለማቀፍ መርከብ ድርጅት ማረስክ፣ ለኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ለዘገየ የክፍያ ጊዜ ያስቀመጠውን የ7 ቀናት ገደብ ወደ 15 ቀናት አራዘመ። ድርጅቱ የ7 ቀናት የክፍያ ማጠናቀቂያ እፎይታ ለሁለቱ አገራት ደንበኞቹ የሠጠው፣ በክፍያ ደረሠኝ ላይ የተጠቀሠው ጊዜ ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ለሚሠላ ጊዜ ነበር። ኾኖም በሁለቱ አገራት ደንበኞቹ ሠነዶችንና የክፍያ ሂደቶችን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመረዳቱ የእፎይታ ጊዜውን ማራዘሙን በድረገጹ ላይ ባወጣው መረጃ ጠቅሷል። ድርጅቱ በተጠቀሠው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ላልፈጸሙ ደንበኞቸ ላንድ ጭነት የሚያስከፍለው ተጨማሪ 40 ዶላር ክፍያ ላይ ለውጥ እንዳላደረገ ገልጧል።

8፤ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር፣ የአንድነት የሽግግር መንግሥቱን ዛሬ በይፋ በተኑ። ኪር የሽግግር አንድነት መንግሥቱን የበተኑት፣ አገሪቱ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ምርጫ ልታካሂድ ሦስት ወራት ሲቀሯት ነው። ኾኖም በመንግሥትና ተቃዋሚው ኃይል መካከል ከሰባት ዓመታት በፊት የተፈረመው የሰላም ስምምነት እንዳልፈረሠ ኪር ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ የሽግግር መንግሥቱን ያፈረሱት፣ በስምምነቱ መሠረት ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት የነበሩት የተቃዋሚው ኃይል መሪ ሬክ ማቻር እስር ላይ ባሉበት ሁኔታ ነው።

እንዲሁም፤

1፤ "ግርዛት" የተሠኘ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ረቡዕ መስከረም 13 ዓ፤ም ከ11 ሰዓት ጀምሮ ሀያት ሪጀንሲ ሥር በሚገኘው ፈንድቃ የባሕል ማዕከል የሥዕል ማሳያ ውስጥ ይከፈታል። በዚህ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ላይ የሚቀርቡ የሥዕል ሥራዎች በሠዓሊ ተወልደብርሃን ኪዳነ የተዘጋጁ ናቸው። ዐውደ ርዕይው እስከ ጥቅምት 9 በዕይታ ላይ ይቆያል።

2፤ የድምጻዊት ፌቨን ዮሴፍ "አዲስ ምዕራፍ" የሚል ርዕስ የተሰጠው አዲስ አልበም ለአድማጮች ቀረበ። በአልበሙ ውስጥ ዘጠኝ ዜማዎች የተካተቱ ሲሆን፣ "ነይ ብራ"፣ "ሀሳቤ"፣ "ነፃነት"፣ "ሰው" የተሰኙ ርዕሶች የተሠጣቸው ሥራዎች ይገኙበታል። አልበሙ በተለያዩ የሙዚቃ ማሠራጫ መተግበሪያዎች በኩል ተለቋል። [ዋዜማ]

20.5k 0 9 117
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot