ለቸኮለ! ረቡዕ፣ መስከረም 13፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ በመንግሥት ወታደሮችና በትግራይ ኃይሎች መካከል በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከማክሠኞ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ በከባድ መሣሪያዎች የታገዘ ግጭት እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሠቀሠው፣ የትግራይ ኃይሎች ከሠቆጣ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሐሙሲት ከተማ ለመግባት መሞከራቸውን ተከትሎ መኾኑን ምንጮች ነግረውናል። ግጭቱን ተከትሎ፤ የትግራይ ኃይሎች ወደ አላማጣ ከተማ አቅራቢያ መመለሳቸውን ምንጮች ገልጸውልናል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የመቀለ፣ ውቅሮ እና ዛላምበሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ በመጀመሪያው ዙር ጦርነት ያጋጠመው ዓይነት ጥፋት እንዳያጋጥም መስጋታቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎች፣ በቀጣዮቹ ቀናት የስልክ፣ የኤሌክትሪክና የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ሊቋረጡ ይችላሉ በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ፣ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ "ጭላ" በተባለ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ኃይሎች ከማክሰኞ ጀምሮ ግጭት ውስጥ መሆናቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
2፤ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ኃይሎች የትግራይና አማራ ክልሎች በሚዋሠኑባቸው የአላማጣና ቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ጧት በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ረፋድ ላይ ግጭቱ ቢቆምም፣ ግጭቱ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል።
3፤ የትግራይ ኃይሎችን የፋኖ ታጣቂዎችንና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ጨምሮ ሰባት ኃይሎች የመሠረቱት "ትብብር ለኅልውና"፣ የ"ትብብሩ" ኃይል ፌደራል መንግሥቱ ከፈተው ያለውን ጥቃት ለመቀልበስ "ጸረ-ማጥቃት" መጀመሩን አስታወቀ። "ትብብሩ"፣ በተለይ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፣ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደርና በአፋር ክልል ሰሜናዊ ቀጠናዎች መጠነ-ሠፊ የ"ጸረ-ማጥቃት" ውጊያ እያካሄደ መኾኑን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ገልጧል። ሥልጣን በኃይል የያዘው ሕወሃት-መራሹ የትግራይ አስተዳደር፣ ፌዴራል መንግሥቱ መስከረም 13 ቀን በእግረኛ ሠራዊቱ ጥቃት ከፍቶብናል በማለት፣ የትግራይ ኃይሎች የመከላከል ርምጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን ዛሬ ጧት መግለጡ ይታወሳል። የአፋር ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ፣ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በኪልበቲ ረሱ ዞን በአብአላ፣ በመጋሌ እና በወሠማ የትግራይ ኃይሎች ጥቃት ከፍተዋል ብሏል።
በፌደራል መንግሥቱ በኩል፣ የሕወሃት አመራር ዛሬ ጧት በአፋርና አማራ ክልሎች በፌዴራሉ መንግሥቱ ይዞታዎች ላይ መጠነ-ሠፊ ጥቃት ከፍቷል ሲሉ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አማካሪ ጌታቸው ረዳ ከሠዋል።
4፤ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሃሙድ የሱፍ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በደቡባዊ ትግራይና በአፋር ክልል ግጭት መባባሱና ታጣቂ ቡድኖች የፈጠሩት የጋራ ትብብር ሁኔታውን ይበልጥ የሚያባብስ መኾኑ በእጅጉ አሳስቦኛል አሉ። የሱፍ፣ የትግራይ ኃይሎች የመቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ አውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠራቸውና የፌደራል ሠራተኞችን ማሠራቸው እንዲሁም በክልሉ የሲቪል አውሮፕላን በረራ መቋረጡ እንዳሳሰባቸው ማምሻውን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። ውጥረቱን የሚያባብሱ ድርጊቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ የጠየቁት የሱፍ፣ ጎረቤት አገራት ሁኔታውን ሊያባብስ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።
5፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የሕወሃት አመራር መጠነ ሠፊ ጥቃት ለመክፈት መወሠኑ አሳዝኖኛል አሉ። ማሲንጋ፣ አፍሪካ ኅብረት የሚያደርውን የንግግር ጥረት ውድቅ ማድረግና ማሸነፍ በማይቻል ውጊያ ውስጥ መግባት፣ ለሕዝብ የሚያስገኘው ነገር የለም ሲሉ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከዚህ አካሄድ ሊቆጠቡ እንደሚገባም ማሲንጋ መክረዋል። አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደ ቁልቁለት ሊገፉ በሚሞክሩ ሌሎች መሪዎች ላይ ጭምር ማዕቀቦችን ለመጣል እድሎች አሏት ያሉት ማሲንጋ፣ ኾኖም አሁንም ትክክለኛው መንገድ ፖለቲካዊ ንግግር መኾኑን አጽንዖት ሠጥተዋል።
6፤ አሜሪካ፣ በትግራይ ክልል ሽረ እንዳሥላሴ ከተማ አቅራቢያ ባንድ የሰብዓዊ እርዳታ በጫነ ተሽከርካሪ ላይ እሁድ'ለት የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት አወገዘች። በድሮን ጥቃት የተፈጸመበት ተሽከርካሪ፣ የካቶሊክ ሠርቪስን ሰብዓዊ እርዳታ የጫነ እንደነበር በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው፣ በድጋሚ ተመሳሳይ ጥቃት ወደፊት እንዳይፈጸም ባለሥልጣናት በጥቃቱ ዙሪያ ሙሉ ምርመራ እንዲያደርጉ እና የምርመራውን ውጤት ይፋ እንዲያደርጉ ጠይቋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ሕወሃት ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ለመፍታት ባስቸኳይ ንግግር እንዲጀምሩም ቢሮው ጥሪ አድርጓል።
7፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሥተዳደር፣ ከዛሬ ረቡዕ መስከረም 13 ጀምሮ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ላልተወሠነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ ጣለ። የከተማዋ አሥተዳደር የሰዓት እላፊ ገደቡን የጣለው፣ "ጸረ-ሠላም" እና "ሠርጎ ገብ" ያላቸውን ኃይሎች ጥቃት ለመከላከልና የሕዝቡን ሠላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ መኾኑን ገልጧል። ለጸጥታ ሥራ ከሚሠማሩ ተሽከርካሪዎችና ከአምቡላንሶች በስተቀር ሌሎች ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ድረስ ከከተማዋ እንዳይወጡና ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ተከልክለዋል። ሆቴሎች፣ ባሮች፣ ሬስቶንቶችና ሙዚቃ ቤቶችም፣ ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ በውጭ የሚሠማ ድምጽ እንዲያጠፉ ታዘዋል።
ኮሬ ዞን ከኦሮሚያው ምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር የሚዋሠን ሲኾን፣ የዞኑ አስተዳደር "የኦነግ ሸኔ" ታጣቂዎች ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር የሚዋሠኑ በርካታ ቀበሌዎችን በኃይል ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሰሞኑን መግለጡ ይታወሳል።
እንዲሁም፤
1፤ የጃዝ ሙዚቀኛው ከተማ ይርጋ "ከተሜ" የተሠኘ በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበረ ገሚስ የጃዝ አልበም መስከረም 18 ቀን በተለያዩ ዓለማቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
2፤ አንጋፋዎቹ ግርማ በየነ እና ዳዊት ይፍሩ ከዘ ፎር ስታር ባንድ ጋር የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት ነገ ሐሙስ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በፈንድቃ የባሕል ማዕከል ይካሄዳል። [ዋዜማ]