ለቸኮለ! ሐሙስ፣ መስከረም 14፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የቀድሞው የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ወታደራዊ መረጃ ኃላፊ ኮሎኔል ተወልደ እንበብ እና የትግራይ ኃይሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊና የቀድሞው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ኢሳያስ ታደሠ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዋዜማ ሠምታለች፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ለፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ መረጃ ያቀብላሉ በሚል ተጠርጥረው መሆኑን ምንጮች ነግረውናል። ሌሎች ሦስት የጸጥታ ኃይሉ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችም እንዲታሠሩ ትዕዛዝ መተላለፉን ምንጮቹ የገለጡልን ሲኾን፣ የወታደራዊ አዛዦቹን ማንነት ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሠ ወረደም መኖሪያ ቤታቸው ከረቡእ ምሽት ጀምሮ በአዳዲስ የጸጥታ ኃይል አባላት እየተጠበቀ እንደሚገኝ ሠምተናል። የጀነራሉ ቤተሠቦችም ሆኑ የቅርብ ወዳጆቻቸው ከቤታቸው መውጣትም ሆነ መግባት እንደተከለከሉም ምንጮቹ ገልጸውልናል፡፡
2፤ መከላከያ ሠራዊት፣ ከመስከረም 12 ሌሊት 9 ሰዓት ጀምሮ በሕወሓትና አጋሮች ናቸው ባላቸው ቡድኖች ላይ በወሠደው ርምጃ 272 ታጣቂዎችን መግደሉንና 260 ማቁሠሉን ገለጸ። የሬዲዮ መገናኛዎችንና በርካታ የጦር መሣሪያዎችን መማረኩን የገለጸው ሠራዊቱ፣ በሕወሓት ተዋጊዎችም ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሻለሁ ብሏል። የሕወሓት ኃይሎች በሰሜን ወሎ ዞን ተኩለሽ፣ ድልድይ፣ ቀይ አፈር፣ በረሃ ማርያም፣ ባይብዋ፣ ጭሮ እና ኩቤ ቀረንሳ በሚባሉ አካባቢዎች ለመግባት ሞከረው እንደነበርና ሆኖም ወደ ኋላ እንዱመለሱ እንደተገደዱ ጠቅሷል።
3፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና የዳንጎቴ ኩባንያ ባለቤት አሊኮ ዳንጎቴ፣ የጅቡቲውን ዳመርጆግ ከኢትዮጵያዋ ደዋሌ ጋር የሚያገናኘውን የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ዛሬ በይፋ አስጀመሩ። ዐቢይ፣ ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ላይ በሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ እንደሚሆን ገልጸዋል። የመሠረተ ልማት ግንባታው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት እንደሚተገበር ዐቢይ ጠቅሠዋል። ዐቢይ፣ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ ወጭንና መዘግየትን በመቀነስ የኢነርጂ ዋስትናን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የንግድ መስመርን ፍጥነትና ዘላቂነት የሚያሳድግ መኾኑንም አስምረውበታል።
4፤ ተመድና አውሮፓ ኅብረት፣ የትግራይ ኃይሎች በትግራይ የሚገኙ ሦስት አውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠራቸውን ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሳስቦናል አሉ። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ሁሉም ወገኖች ባስቸኳይ ውጥረቱን እንዲያረግቡ፣ ሲቪሎችን ከጥቃት እንዲጠብቁ፣ የእርዳታ መስመሮች ለረድዔት ድርጅቶች ተደራሽ መኾናቸውን እንዲያረጋግጡ እና ሁኔታው ወደ አውዳሚና መጠን ሠፊ ግጭት እንዳያመራ ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
አውሮፓ ኅብረትም፣ ውጥረቱን ባስቸኳይ ማብረድ እንደሚያስፈልግና ለፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተገዢ ለመሆን ጊዜው እንዳልረፈደ ገልጧል። ኅብረቱ፣ ልዩነቶች በፖለቲካዊ ድርድር ብቻ እንጂ በወታደራዊ ርምጃ ሊፈቱ እንደማይችሉም አጽንዖት ሠጥቷል። ሲቪሎችን ከጥቃት መጠበቅና የረድዔት ሥራዎችን ገለልተኛነት ማክበር ለድርድር የሚቀርቡ አይሆኑም ያለው ኅብረቱ፣ በረድዔት ድርጅቶች ላይ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን እንደሚያወግዝ ገልጧል።
5፤ በትግራይ ሥልጣን በኃይል የያዘው ሕወሃት-መራሹ አስተዳደር፣ የአሜሪካውን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋንና አፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሃሙድ የሱፍን ወቀሠ። ማሲንጋ በግጭቱ ዙሪያ ላንድ ወገን ያደላ መግለጫ ያወጣሉ ብለን አልጠበቅንም ነበር በማለት ያለው አስተዳደሩ፣ ማሲንጋ ፌደራል መንግሥቱ ለዳግም ጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱን በቸልታ ማለፍ መርጠዋል በማለት ተችቷል። አምባሳደሩ በትግራይ ያለውን ሁኔታ ባግባቡ እንዲገመግሙና ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ለማምጣት እንዲሠሩም አስተዳደሩ ጠይቋል።
በተያያዘ፣ አፍሪካ ኅብረት በትግራይ ያለውን ችግር ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን መግለጡን ከእውነታው ጋር ለማስታረቅ ያስቸግራል በማለት የማሃሙድ የሱፍን የትናንቱን መግለጫም አስተዳደሩ ተችቷል። አስተዳደሩ፣ ድርድር እንዲሳካ ሽምግልና ገለልተኛ እና ከሁለቱም ወገኖች ጋር ወጥ በሆነ መንገድ ግንኙነት ማድረግን የሚጠይቅ መኾን እንዳለበት ገልጧል።
6፤ ኦነግ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ጋር ይደረጋል የተባለው ወታደራዊ ትብብር ኦሮሚያ ክልልንና የኦሮሚያን ሃብት ዳግም በቁጥጥር ሥር ለማስገባት ያለመና የኦሮሞ ሕዝብ በተወሠነ መልኩ ያገኘውን መብት ወደ ኋላ የሚመልስ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲል ተቃውሞውን ገለጠ። ግንባሩ፣ "ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እንታገላለን የሚሉ" ያላቸው ወገኖች "ጠላት" በማለት የጠራቸውን አካላት አጀንዳ ከማስፈጸም ይቆጠቡ፤ ሕዝቡ በትግሉ ያስወገደውን የግፍ አገዛዝ በድጋሚ ለመመለስ የሚያደርጉትን የተሳሳተ አካሄድም ያቁሙ በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። ሆኖም ኦነግ የትብብሩ አካል የሆነውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን በስም ለይቶ አልጠቀሠም።
7፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የኢሕአፓ አባላት ይስሃቅ ወልዳይ እና አበበ አካሉ እንዲሁም የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣ ጠበቃ አበራ ንጉስ በተፈቀደው ዋስትና ላይ ፖሊስ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ዋዜማ ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ሠምታለች። ተጠርጣሪዎቹ በአርባ ምንጭ ከተማ በዘይሴ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ተፈጸመ ከተባለው ግድያና መፈናቀል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በፖሊስ የምርመራ መዝገብ ላይ ተጠቅሷል። ችሎቱም፣ በዋስትናው ላይ በቀረበው አቤቱታ ላይ ዛሬ ውሳኔ ለመስጠት ነበር የተሠየመው። ሆኖም ችሎቱ "የስር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት ሲፈቅድ የፖሊስን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ውድቅ ማደረጉ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከአርባ ምንጩ ግድያና መፈናቀል ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ፖሊስ ያቀረበውን የምርመራ መዝገብ ባግባቡ ተመልክቶ ነው ወይስ አይደለም?" የሚለውን ጉዳይ መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት እንዲችል የምርመራ መዝገቡ እንዲቀርብለት አዟል።
8፤ አዲሱ የጋራ የኢንቨስትመንት አሠራር መመሪያ ጸደቀ። የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ መመሪያው የጋራ የኢንቨስትመንት እቅዶችን ለማቋቋም፣ ለመመዝገብ፣ ለማስተዳደር የሚያስችል ሠፊ የሕግ ማዕቀፍ መኾኑን ገልጧል። መመሪያው፣ የጋራ ኢንቨስትመንቶች የሚያካሂዱ አካላትን፣ የባለ አደራ ጠባቂዎችን እና ሌሎች የባለሙያ አካላትን ኃላፊነቶችና ግዴታዎችን ይደነግጋል። ባለሥልጣኑ፣ መመሪያው መጽደቁ የዜጎችን ቁጠባ በባለሙያ አስተዳደር እና በጠንካራ የኢንቨስተሮች ጥበቃ አማካኝነት ወደ ውጤታማ ኢንቨስትመንት ለማዞር ትልቅ ርምጃ መሆኑን ገልጧል።
በመመሪያው ሕጋዊ እውቅና የተሠጣቸው የጋራ ኢንቨስትመንት ሥራዎች ስድስት ሲሆኑ፣ እነሱም የገንዘብ ገበያ ፈንድ፣ የጋራ ፈንድ፣ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ፈንድ፣ ኤክስቼንጅ ትሬድድ ፈንድ፣ አማራጭ የኢንቨስትመንት ፈንድ እና በልዩ ሁኔታ የሚታይ ፈንድ ወይም ስፔሻል ዲዝግኔትድ ፈንድ ናቸው። [ዋዜማ]