ለቸኮለ! ቅዳሜ፣ መስከረም 16፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ነሐሴ 14 አጋማሽ ላይ በመቀሌ በመኖሪያ ግቢ ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት እንደ "የጦር ወንጀል" ተቆጥሮ ሊመረመር ይገባል አለ። ድርጅቱ፣ በጥቃቱ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 13 ሰላማዊ ሰዎች ጉዳት እንደደረሠባቸው የጠቀሠው ድርጅቱ፣ በወቅቱ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዒላማ እንዳልነበርና ጥቃቱ "ሕገወጥ" እና "ማንንም ያልለየ" እንደነበር ገልጧል። ባለሥልጣናት ጥቃቱን ገለልተኛና ግልጽ በኾነ መንገድ እንዲመረምሩ፣ በድርጊቱ የተሳተፉት አካላትን ለሕግ እእንዲያቀርቡና ለተጎጂዎች በቂ ካሳ እንዲከፍሉ ድርጅቱ ጠይቋል። ከመንግስት ወገን እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።
2፤ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ፎከር ቱርክ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መቀስቀሱ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አስታወቁ። ቱርክ፣ በትግራይ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ አደጋውን እንደሚያባብሰው ገልጸዋል። በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች መስከረም 13 ቀን በሞርታር በፈጸሙት ጥቃት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን የጠቀሱት ቱርክ፣ በትግራይ በአምስት ትምህርት ቤቶች ላይ መስከረም 12 በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰዎች መገደላቸውንና መቁሠላቸውን ገልጸዋል።
ቱርክ፣ ሁሉም ወገኖች ውጥረቱን እንዲያበርዱና ወደለየለት ጦርነት እንዳይገቡ፣ የሲቪሎችን ደኅንነት እንዲጠብቁና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። በትግራይ ሕጻናትን ጨምሮ የሚካሄደውን የግዳጅ ምልመላ ቱርክ ያወገዙ ሲኾን፣ የመንግሥት ኃይሎችም የዘፈቀደ ምልመላ ያካሂዳሉ የሚሉ ሪፖርቶች እንዳሉ ጠቅሠዋል።
3፤ የአማራ ክልል የዓቃቢያነ ሕግ ማኅበር፣ የዓቃቢያነ ሕግ የደመወዝ ጭማሪና ማስተካከያ ጥያቄው እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ገለጠ። ማኅበሩ፣ ለፍትሕ ሚንስቴር፣ ለጠቅላይ ሚንስተር ጽሕፈት ቤት፣ ለገንዘብ ሚንስቴርና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የደመወዝ ጭማሪና ማስተካከያ እንዲደረግ በደብዳቤ ጠይቆ ምላሽ ባለማግኘቱ፣ በሐምሌ ወር የፌደራል መሥሪያ ቤቶች ለጥያቄው ምላሽ እንዲሠጡት በአካል መጠየቁን ጠቅሷል። ኾኖም ጥያቄው ምላሽ ባለማግኘቱ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለጥያቄው ምላሽ እንዲያስገኙ በአካል ጥያቄ ማቅረቡንና ለዚሁ ጉዳይ ያቋቋመውን ኮሚቴ እንዲያነጋግሩ መጠየቁን ገልጧል።
4፤ አሊኮ ዳንጎቴ፣ ዳንጎቴ ኩባንያ በኬንያዋ ላሙ ወደብ ላይ ሊገነባ ያቀደው የነዳጅ ማጣሪያ 1 ሺሕ ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናገሩ። ዳንጎቴ የላሙ ነዳጅ ማጣሪያ ከሚያመርተው ኃይል 500 ሜጋ ዋት ለኬንያ መንግሥት እንደሚሸጥ ትናንት ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ሌጎስ ውስጥ በተገናኙበት ወቅት ተናግረዋል። ነዳጅ ማጣሪያው ከተገነባ በኋላ፣ ወደ ላሙ ወደብ እጅግ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚስብ ዳንጎቴ ገልጸዋል። ዳንጎቴ ኩባንያ በቀን 700 ሺሕ በርሜል ድፍድፍ የማጣራት አቅም ያለውን የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ በቀጣዩ ሳምንት ላሙ ወደብ ላይ ለማስጀመር አቅዷል።
እንዲሁም፤
1፤ የዝነኛው «አይቤክስ ባንድ» አባላት በአውሮፓ አሕጉር ብራሰልስና ስቶክሆልምን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን ሊያቀርቡ ነው። ይህ የሙዚቃ ጉዞ ከጥቅምት 24 እስከ 29 2019 ዓ፤ም (ከኖቬምበር 3 እስከ 8 2026) የሚካሄድ ሲሆን፤ ጊታሪስት ሰላም ስዩም፤ የቤዝ ጊታሪስት ጆቫኒ ሪኮን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃን ከጃዝ፣ ፈንክ እና ሶል ጋር በማቀንቀን የሚታወቁ አርቲስቶችም ይሳተፉበታል።
2.አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ የአዲስ አበባ ማዕከል ፕሬዚዳንት ሆኖ መሾማቸውን ማዕከሉ አስታወቀ። አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ፤ በባሕልና በኪነ ጥበብ፣ በቋንቋ እንዲሁም በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ዘርፎች የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ማዕከል ነው።አዲሱ ፕሬዚዳንት አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ በቅርስ ጥበቃ፣ በታሪካዊ ሕንፃዎች እድሳት እና በአርክቴክቸር ዘርፍ ሰፊ ልምድና አስተዋጽኦ ያላቸው ባለሙያ መሆናቸው ይታወሳል። [ዋዜማ]