TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Wazema Media / Radio

2 Oct, 20:13

Open in Telegram Share Report

ለቸኮለ! ዓርብ፣ መስከረም 22፣ 2019 ዓ፣ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የትግራይ የሰላም ኃይል መላዋን ትግራይ ለመቆጣጠር ተቃርቤያለሁ አለ። ቡድኑ፣ ተዋጊዎቹ ከመቀሌ ደቡብ ምስራቅ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሚላዛት ከተማ መያዛቸውን ገልጧል። የቡድኑ አዛዥ ጀነራል ገ/እግዚአብሔር በየነም፣ የሕወሓት አመራሮች ከመቀሌ እየወጡ መኾኑን ተናግረዋል። ጀነራሉ፣ ቡድኑ ከሕወሃት ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት ላይ የበቀል ርምጃ እንደማይወስድም ማረጋገጫ ሠጥተዋል።

የሕወሃት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው፣ የመንግሥት ኃይሎች የተወሠኑ የትግራይ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን ትናንት ምሽት በሠጡት መግለጫ አምነዋል። ኾኖም የትግራይ ኃይሎች መልሶ ማጥቃት ርምጃ የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል ያሉት ደብረጽዮን፣ ተዋጊዎቻቸው ካሁን በኋላ ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት እንደሚከተሉ ተናግረዋል።

በተያያዘ፣ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ስምረት ፓርቲ፣ በኃይል ሥልጣን ከያዘው ሕወሃት-መራሹ አስተዳደር ጋር ሲሠሩ የቆዩ አካላት ወደ ኤርትራ እንዳያቀኑ ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ከበቀል ስሜት እንዲርቁ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የታጠቁ ኃይሎችም የሕዝብ ተቋማትን በመጠበቅ ለሰላማዊ መንገዶች እንዲዘጋጁ ፓርቲው ጥሪ አድርጓል።

2፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አፍሪካ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀ። አምነስቲ፣ ኅብረቱ ካለፉ ስህተቶቹ በመማር በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሠተው ቀውስ ባፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። በአየር ላይ ጥቃቶች ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዳስደነገጠው የጠቀሠው ተቋሙ፣ ባለሥልጣናት በትግራይ ክልል የተቋረጡ የኮምንኬሽን አገልግሎቶችን በአፋጣኝ እንዲያስጀምሩ ጠይቋል። የድርጅቱ የአፍሪካ ሃላፊ ቲገር ቻጉታህ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፍ ድርጅቶች ሲቪሎችን ከጉዳት እንዲጠበቁና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።

3! ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ “መንገድ ስተው ከአገራቸው በተቃራኒ ቆመዋል ያሏቸው ኃይሎች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ነገ መከበር የሚጀምረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ጥሪ አደረጉ። "ኦሮሞ በትግሉ ነጻ ወጥቷል" ያሉት ዐቢይ፣ ከዚህ በኋላ "በጠመንጃ አፈሙዝ" እና "ከጠላት" ጋር በመተባበር የሚመለስ የኦሮሞ ጥያቄ ሊሮር አይችልም ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።ዐቢይ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን እንዲያጠናክር እና ሰላም፣ እርቅና ወንድማማችነትን እንዲያበረታታ ጭምር ጥሪ አስተላልፈዋል።

4፤ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሺመልስ አብዲሳ፣ ከክልሉ 23 የከተማ አሥተዳደሮች መካከል ስምንቱ በቀጥታ በክልሉ መንግሥት ስር እንዲሆኑ ተወስኗል ሲሉ ከኦቢኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናገሩ። በክልሉ መንግሥት ሥር የሚኾኑት፣ አዳማ፣ ሸገር፣ ነቀምት፣ ጂማ፣ ሻሸመኔ፣ ሮቤ፣ ማያ እና ቢሾፍቱ መኾናቸውን ሺመልስ ገልጸዋል። ሺመልስ፣ የስምንቱን ከተሞች የፋይናንስ፣ የእቅድና ሰው ኃይል ምደባ የክልሉ መንግሥት በቀጥታ እንደሚመራ አስረድተዋል። ቀሪዎቹ 15 የከተማ አስተዳደሮች አዲስ በተዋቀሩት ስድስት ዞኖች ሥር እንደሚተዳደሩ ሺመልስ አብራርተዋል።

5፤ የአፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሐረሬ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች ለቀጣይ አምስት ዓመታት በድጋሚ ተመርጠዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ወደ አዲስ አበባ በተዛወሩት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድሩ ጥላሁን ከበደ ምትክ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ተስፋዬ ቤልጅጌን ሾሟል። ተስፋዬ የክልሉ ምክር ቤት አባል ባለመኾናቸው፣ ሹመቱን የተቀበሉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ነው። ተመሳሳይ የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ ያደረገው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት፣ በነጋሽ ዋጌሾ ምትክ፣ ፍቅሬ አማንን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤትም፣ በቀድሞው ከንቲባ ከድር ጁሀር ምትክ አብዱላሂ አደንን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

6፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ መስከረም 24 ቢሾፍቱ ላይ ለሚከበረው የሆረ ሃርሰዴ ኢሬቻ በዓል ከዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ መስከረም 24 ድረስ በርካታ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ ለተሽከርካሪ ዝግ አደረገ። በሱሉልታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጫንጮና ፍቼ ከተማ ላይ፣ በለገጣፎ ለገደዲ በኩል የሚገቡ ሸኖና ሠንደፋ ከተማ ላይ እንዲኹም በቡራዩ በኩል የሚገቡ ሆለታ ከተማ ላይ እንዲቆሙ ኮሚሽኑ ማሳሰቡን የአገር ውስጥ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። በተመሳሳይ፣ በሰበታ በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ወሊሶ ከተማ ላይ፣ በአዳማ በኩል የሚገቡና ከአዲስ አበባ የሚወጡ በፍጥነት መንገዱ ብቻ አሳስቧል ኮሚሽኑ አሳስቧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ለበዓሉ የዘጋቸውን መንገዶች በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አላደረገም።

7፤ የኬንያው ኤንሲቢኤ ባንክ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለመሠማራት ዝግጅት እያደረገ መኾኑን ገለጠ። ኾኖም ባንኩ ከኢትዮጵያ ባንኮች ጋር ድርድር ስለመጀመሩ ፍንጭ እንዳልሠጠና ኾኖም የራሱን አዲስ ባንክ የማቋቋም ሀሳብ እንደሌለው ኃላፊዎቹ መናገራቸውን የኬንያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ባንኩ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ዝግጅት ላይ መኾኑን የገለጠው፣ ኔድባንክ የተባለው ባንክ በባንኩ ውስጥ የከፍተኛ ድርሻ ባለቤት መኾኑን ተከትሎ ነው። ኤንሲቢኤ ባንክ፣ በኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ጭምር በባንክ ዘርፍ ተሠማርቷል።

እንዲሁም፤

1፤ "አንቀጽ 7" የተሠኘ አዲስ ተውኔት የፊታችን እሁድ መስከረም 24 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመርቆ ለዕይታ ይበቃል። ተውኔቱን ተፈሪ ፍቃዱ ጽፎት ቢያንም እሸቱ አዘጋጅቶታል።

2፤ የአድማስ ባንድ አባላት ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን ከምሸቱ 2 ሰዓት ከ30 በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ። መግቢያው 700 የኢትዮጵያ ብር ነው። [ዋዜማ]

11.1k 0 8 94
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot