Gize Wegoch, [Oct 21, 2024 at 8:57 PM]
አይጠሩ
...........
በአማት መወደድ ለጥቂት ዕድለኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ የተሰጠ ፀጋ ይመስለኛል።በተለይ ደግሞ በቁመት የምትበልጥህን ሴት ልታገባ እየተዘጋጀህ ከሆነ!ነፍሳቸውን ይማርና ጎረቤታችን አብዬ በላቸው
"ፍቅር ምን ድረስ ክፉ ነው?"ተብለው ሲጠየቁ
"እኔና ሰዋለምን እስቲያጋባን ድረስ" ይሉ ነበረ አብረው ሲቆሙ በጡታቸው ትክክል የሚሆኑትን ሚስታቸውን እያሰቡ።የሞቱት አብሯቸው የኖረው አስም በሌሊት አፍኗቸው ነው ቢባልም የመንደራችን 'ፓፓራዚዎች' እንደሚሉት ከሆነ ግን ለሞት ያበቃቸው አስሙ ብቻ ሳይሆን በባለቤታቸው ጡቶች መሃል አፍንጫቸው መታፈኑ ነበር።
እሰቡት 1.50 ሆኜ 1.75 የምትረዝም እጮኛ ስይዝ! አብዬ በላቸው ከነሚስታቸው ድቅን ይሉብኛል። ከመጋባታችን አንድ ወር አስቀድማ ከቤተሰቦቿ ጋር አስተዋወቀችኝ።ያደገችው ከአሽሙረኛ እናቷና ከጉልቤው ወንድሟ ጋር ነው።ውበቷን ያየ የእናቷን ወግ አጥባቂነት እና የወንድሟን ኃይለኝነት መገመት አያቅተውም።ልታስተዋውቀኝ ቤቷ የወሰደችኝ ቀን እናቷ እትየ ዘውዴ ከእግር እስከራሴ አልቢን በሚያስንቅ አይናቸው እንደሽንኩርት ከላጡኝ በኋላ የሚያበሽቅ ሳቃቸውን አስከትለው
"እንዴት ያለ ኮረሪማ አግኝተሻል ሚጡ!ና እስቲ ሳመኝ"ብለው ሱባኤ እንደገባ ገዳምተኛ ወገባቸዉን በነጠላቸዉ አሰሩና ከምድር ወገብ የሚሰፋ ሽክርክሪት መቀነታቸዉን እየቋጩ ጎንበስ አሉ። መና እንደወረደለት ሰዉ ወደ ላይ ቀና ስል ከመቅፅበት ትከሻዬን እንደቅቤ ቅል እየናጡ አገላብጠው ሳሙኝ።ልጃቸው በሷ እንደወጣች ቁመታቸው ይናገራል።ከፊት ለፊታቸው ስቆም ከአይናቸው ይልቅ ከጡታቸው ጋር ነው የምፋጠጠው።ጃንሆይም እንደሳቸው ጡት መውደቃቸውን እጠራጠራለሁ።እንኳን የሳቸው ጡት ሁለት ልጅ የጠባው ይህች ጉደኛ ሀገር ራሷ ደርግ አይጥ እንደቀመሰው ካልሲ ቦትርፏት፣ኢህአዴግ እንደ ገና ዳቦ በላይ በታች አንድዷት፣የአሁኑ ጉድ በወሬ ፓትራ እስከጥግ ነፋፍቷት...የሳቸውን ጡት ያህል ዝቅ አላለችም።
ሳሎናቸው ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የቤተሰብ ፎቶ ሳይ "አቤት ግጣም በልክ ሲገኝ!" አሰኘኝ።ባለቤታቸው ከእሳቸው የበለጡ ብቅል አውራጅ ቢጤ ናቸው።ወንዱ ልጃቸው ከሚጡ ትንሽ ይረዝማል።ደፍሬ ሳሎናቸውን የረገጥኩ የመጀመሪያው ስንዝሮ እኔ ሳልሆን አልቀርም።
ወደ ምግብ ጠረጴዛው ስናዘግም አሽሙር የተካነ አፋቸውን አሸራመው እየቃኙኝ
"ሶፋው ላይ እንሁን መሰል ጠረጴዛው አለቅጥ ረጅም ነው" አሉኝ።ጠረጴዛው የረዘመብኝ እንደሁ ሌላ ዝርጠጣ ስለሚከተለኝ ጥያቄአቸውን ተቀብዬ ወደ ሶፋው አመራን።ከመቀመጣችን ሌላ ብቅል አውራጅ ባልቴት እየተንጎማለሉ ዘለቁ።ሚጡ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ
"አክስቴ ናት ኃይልሻ" አለችኝ።
እትየ ዘውዴ
"ህብስቴ መጣሽ?ቀረሽ ብየ ነበር'ኮ እመዋ" አሉና አገላብጠው ከሳሟቸዉ በኋላ አቆልቁለው እያዩኝ
"ነይ ሳሚው የሚጡን ባል...እየውልሽ እንዴት ያለውን ምጥን የወንድ አውራ እንዳመጣችው"
"ኧግ!የቢያዝኔ ምትክ...እምጷ...የአባቷ ምትክ...እምጷ...የት አገኘሃት?... እምጷ ይችን መለሎ...እምጷ"
የሞት ሞቴን ፈገግ ብዬ ከመቀመጤ በእህታቸው እግር ተተክተው ይወጉኝ ገቡ።
"ዋዋዋዋዋ...እንደው ከየት አገኘሃት?ማነበር ያልከኝ ስምህን"
"ኃይሌ"
"ምንድን ነዉ ስራህ?"
'ገጣሚ ነኝ' ልላቸው ፈለኩና የዘመኔ ገጣምያን በህሊናየ ድቅን አሉብኝ።
በእዉቄ እንኳን ቁመቱ ጊዜ ጠብቆ የሚጨምረዉ ግጥም ወይም ወግ ሲያነብ ብቻ ነዉ። ምክንያቱም ተመልካቹ ሁሉ ተቀምጦ ስለሚያዳምጠው።
ብዙዎችን በአይምሮዬ ማሰላሰል ስጀምር ገጣሚነቴ ተኖ ጠፍብኝ ።
"ምን አልከኝ ?"ሲሉኝ
"እ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ" አልኳቸዉ በደባልነት የያዝኩትን ሙያዬን።
"እ...መምህርነት ሸጋ ነው!...እና ከየት አገኘሃት በል ይችን መለሎ?"
"እህ...ህ...ህ...ትውውቃችን እንኳን ከድሮም ነው...ከትምህርት ቤት"
"ኧረግ ኧረግ ኧረግ ኧረግ!!...መቸም ተፊት ተቀምጣ እየከለለችህ አስቸግራህ ነው እሚሆን...እሂ...ሂ...ሂ...ሂ"
'ጥርስዎት ለሙቅ አይትረፍ!ድዳም'
"ኧረ በነገር አትያዣቸው ህብስቴ ምሳው ይቅረብ" አሉና አማቴ ሰፋ ባለ ትሪ ዶሮ ወጣቸውን በአይብ አጅበው አቀረቡት።
'ሰው ከረዘመ ሞኝነት አያጣውም' የሚለው አባባል እዚህ ቤት አይሰራም።እንደውሃ ሙላት እያሳሳቁ መግደልን ተክነውበታል።
ህይወቴ በረጃጅም ሴቶች ዙሪያ እንዲሽከረከር ማን እንደፈረደብኝ ባላውቅም 8ኛ ክፍል እያለን በደብዳቤ የጠየቅኋት መለሎዋ ማህሌት ራሱ ደብዳቤውን ለስም ጠሪ ሰጥታ ተማሪዎች ፊት ከማስነበብ የከፋ አልጨከነችብኝም። የልብ ስእል ለመሳል የቀደድኩትን ወረቀት እናቴ ሰብስባ ሶስት እንጀራ ከነ ካሲናዉ እንዳወጣችበት ሳስታዉሰዉ ይደንቀኛል።
በጦር ተወግቶ ለሚደማው ልቤ ማሳያ ይሆነኝ ዘንድ አባቴ በፀሀፊነት ከሚያገለግልበት የሰፈሩ እድር የተቀበለውን ብቸኛ ቀይ እስኪብሪቶ በማገንፈሌ አንድ ፌርሜሎ ከሰል ተቀጣጥሎ ለሳምንት ወጥ መስሪያ የሚሆን በርበሬ ታጥኜ ነበር።ይህን ሁሉ መስዋዕትነት ከፍዬ
"ያም አለ ያም አለ የአተር ገለባ ነው
ሰው ይዋደድ እንጅ ቁመት ለአገዳ ነው" ብዬ መጻፌን ሳስታውስ እንደቂል በራሴ እስቃለሁ።
ዶሮው ተበልቶ ሲያበቃ ያመጣሁት ውስኪ ተከፈተና አንድ ሁለት እያልን ጨዋታ ቀጠልን።በመሃል አማቴ ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የባለቤታቸውን ፎቶ አዩና አንደ መሳቅም እንደማልቀስም እያደረጋቸው
"አየ....የ...የ...ቢያዝኔ ዛሬ ነው የሞትክ!አየ የኔ ጠምበለል!"ወዲያው ወደ ሚጡ ዞረው
"አይደለም እንዴ አንች?ዛሬ አይደለሞይ የሞተው?እንዲህ አለምሽን ሳያይ...አይ ቢያዝኔ!" ብለው በተቀመጥኩበት ከአፈር የሚደባልቅ አስተያየት አከሉልኝ።
የቁመቴን ማጠር የኪሴ መወፈር አካካሰው እንጂ እናትየው የዛኑ ቀን ከኔ በሚረዝም በቡሀቃ ማማሰያቸው እያጠደፉ ቢያባርሩኝ እንዴት ደስ ባላቸው!ባስተዋወቀችን በሳምንቱ የኔዋ ጉድ ከሰርጉ በኋላ የምንገባበትን ቤት እናቴ ካላየችው ብላ እየጎተተች አመጣቻቸው።ሳሎኑን በገረፍታ አዩና ምኝታ ቤት ዘው ብለው ገቡ።አልጋው ላይ አፍጥጠው
"ምነው እንዲህ ሰፋ?በራይ ልትወጡበት ነው?ባይሆን ቁመቱን ጨምሩት!" አሉ።የልጃቸውን ቁመት ያህል በእግዚሀሩ እንኳን መመካታቸውን እንጃ!
ሰርጉ ሳይሰረግ እንዲህ የቋንጃ እከክ የሆኑብኝ ከተሰረገ ወዲያ ሊኖረኝ የሚችለውን ህይወት ሳስበው ሚጡን ማውራት እንዳለብኝ ተሰማኝ።
"እትየ ዘውዴ ከሰርጉ በኋላ ለበዓል ካልሆነ እንዲመጡ አልፈልግም!"አልኩ ምርር ብዬ
"ምን ማለትህ ነው ኃይልሻ?እናቴ'ኮ ናት!"
"ለኔ ደግሞ አማቴ ናቸው!የማይወዱኝ አማቴ!ጣልቃ ገብነትም'ኮ ልክ አለው።አንቺ ለምታገቢኝ የሳቸው አቃቂር አውጭነት ምን ይሉታል?"
"ኢሂ...ሂ...ሂሂሂ...እማዬ'ኮ ተጫዋች ስለሆነች ነው...ደግሞም የምትወደው ሰው ላይ ነው የምትቀልደው...አትቀየማት"ብላ በጥርሷ አዘናጋችኝ።
ሰርጉ 3 ቀን ሲቀረው ለንቦጯን ጥላ መጣች።
"ምን ሆነሽ ነው?" ዝም
"አንቺ ሚጡ ምን ሆነሽ ነው?" ዝም
"አትናገሪም እንዴ?"
"ከእማዬ ጋር ተጣላን"ብላ ለንቦጯን ይብስ ዘረጋችው።
"በምን?ምን ተፈጠረ?"
የስልኳን ፎቶ ማከማቻ ከፍታ አንድ ሂል ጫማ አሳየችኝና
"ይሄን ጫማ ለሰርጌ አደርገዋለሁ ብዬ የዛሬ ወር ነው የገዛሁት።ትናንትና ማታ አይታው 'የዘውዴ መቃብር ሳይማስ ይኸን ለብሰሽ አትሞሸሪም!' " አለችኝ።