እንኳን አገር አጥበው ቀሽረው ሊያወርሱን ...
(አሌክስ አብርሃም)
በፈረንጆቹ 2011 ጃፓን ውስጥ Fukushima የተባለ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ያውም በሬክተር ስኬል 9.0 የተመዘገበ። በሰዓታት ውስጥ 20 ሺ ህዝብ በዘግናኝ ሁኔታ አለቀ ፣6ሺ ሰው ከከፍተኛ እስከቀላል የአካል ጉዳት ደረሰበት ፣ 2500 ሰው የደረሰበት ጠፋ ፣ ግማሽ ሚሊየን ህዝብ ቤት ንብረቱን ጥሎ ተፈናቀለ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚሉት የኛ አበወች ከነገሩ በላይ ዓለምን ያስደነገጠ ሌላ ዜና ተሰማ ። ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ጣጣ!
ይሄ ጦሰኛ አደጋ የተከሰተባት ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ የኒውክሌር ማብለያ ተቋም አለ። Fukushima Daiichi nuclear power plant ይባላል። በዓለማችት ካሉ 25 የኒውክሌር ሀይል ማምረቻወች አንዱ ነው። በአደጋው ከዚህ ግዙፍ ተቋም የራዲዮ አክቲቭ ጨረር አፈትልኮ ወጣ። ራዲዮ አክቲቭ በቀጥታ ካገኘ ማንኛውንም ህይወት ያለው ፍጡር የሚገድል እንዲሁም ውሃ ይንካ ድንጋይ ሁሉንም ቁስ በመበከል ወደገዳይ ቁስነት የሚቀይር መራዢ ጨረር ነው። በአካባቢው ላይ ለአመታት በመቆየትም ይታወቃል። ከዚህም የከፋ ነው ኬሚስትሪው። ተጠቅቶ ከአደጋ መትረፍ ቢቻል እንኳን መትረፍ አይበለው። ዓለማችንን የሚያስጨንቃት የኒውክሌር መሳሪያ የሚፈራበት አንዱ ምክንያት ይሄው ነው።
አደጋው ጋፕ ሲል ከአካባቢውን ከገዳዮ ብክለት ለማፅዳት መላው ጃፓናዊ ተረባረበ። ይሄን ሁሉ መከራ ያወራኋችሁ ቀጥሎ ለምነግራችሁ የሚያስቀና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ብክለቱን ማፅዳት፣ ጉዳቱንም መቀነስ ይቻላል ፣ ግን መጥረጊያህን አንስተህ በሞራል ዘው የምትልበት ዘመቻ አይደለም! የረቀቀ ሳይንስ ነው። በክር ላይ የመራመድ ያህል ጥንቃቄ ልምድና ዕውቀት እንዲሁም ዕድል የሚጠይቅ ነገር! በደመነፍስ ቦታው ላይ መገኘት ወዲያው ከመሞት የእድሜ ልክ ካንሰር ፣ለሌሎችም ዘግናኝ ጉዳቶች ሊዳርግ ይችላል። መቸስ ችግር ጀግኖችን ይፈጥራል። መላው ዓለም
"Fukushima 50"ብሎ የሰየማቸው ጡረታ የወጡ ሽማግሌወች ይህን ራዲዮ አክቲቭ ጉዳት ለመከላከል በፈቃደኝነት ከፊት ተሰለፉ።
እነዚህ ሰወች የጡረታ ክፍያቸው ያነሰባቸው ፣ ከዚህ ኑሮ ሞት ይሻላል ያሉ ጧሪ አልባ ሽማግሌወች እንዳይመስሏችሁ ፣ ከፍተኛ የኒውክሌር ኢንጅነሮች፣ ተመራማሪወች የነበሩ ጡረታ ወጥተው የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ ጃፖናዊያን አባቶች እንጅ። ብቸኛ ዓላማቸው የድርሻችንን ኑረናል ይህን የኒውክሌር ተቋም የመሰረትነውም እኛ ነን ሀላፊነቱን መውሰድ ያለብን እኛ ነን፣ ልጆቻችንና ለቀጣዮ ትውልድ ይሄን ገዳይ ቆሻሻ አናወርስም! የድርሻውን ንፁህ አገር ይረከብ ዘንድ ሞትም ቢሆን ዋጋ እንክፈል የሚል ነበር። አንዷ የ72 ዓመት ጡረተኛ እንዲህ አለች "My generation built these nuclear plants. So we have to take responsibility for them. We can't dump this on the next generation,"እናም ወጣቶቹንና ብዙ ሊሰሩ የሚችሉትን ኢንጅነሮች ተክተው በዛ ቀውጢ ወቅት ወደተበከለው ተቋም ባጭር ታጥቀው ገቡ።
በእርግጥም ይህን ከባድ ሀላፊነት በመወጣት አደገኛውን ስራ በመፈፀም ከኋላ ለሚመጡ ወጣት ኢንጅነሮች እና ብክለቱን ለማፅዳት ለተሰለፉ ሁሉ መንገድ ጠረጉ። ጣቢያው ውስጥ ለቀናት በመቆየትና ሪአክተሩን በማቀዝቀዝ ጃፓን ይገጥማት ከነበረ የሚሊየኖች ሞት ታደጓት! ትውልድን ከቆሻሻና የሀዘን ታሪክ ውርስ ታደጉ!! የሚደንቀው ነገር አንድኛቸውም በአደጋው አልሞቱም!! አገር ለትውልድ እንዲህ ታጥቦ ተቀሽሮ በውርስ ይሰጣል ። እኛስ? እንኳን አገር አጥበው ቀሽረው ሊያወርሱን የኛን ዕድሜ የሚቀሙ፣ የቀጣዮ ትውልድ ዕጣፋንታ ላይ የጥላቻ ቆሻሻ ደፍተው የሚፎክሩ አባቶች ልጆች ሆንን ! አየህ ወጣትን እየማገዱ ኑሯቸውን ለሚያመቻቹ የጠነዙ ፖለቲከኞቻችን ይሄ ጅልነት ነው። ጃፓን እንደምን ሰለጠነች ይሉናል አገራችን እንደምን ሰየጠነች ብለን ስንጠይቅ!
@wegoch
@wegoch
@paappii