አንድ አስናቀች
(ገብርኤላ ይመር)
እንደ ኑሮአችን እነርሱም ተደጋግፈው ከተሰሩት ከምኖርባት መንደራችን በአዲስ ዓመት ጠዋት ላይ አበባይሆሽ የሚጨፍሩ ልጆች ድምጽ ከተንጋለልኩበት ፍራሼ ላይ ሆኜ በስሱ የከፈትኳትን ሙዚቃ ሰብሮ ገርብብ ያለ በሬን አልፎ በጆሮዬ ዘለቀ
"የመስቀል ለታ
የደመራው
ንፍሮ ቀቅዬ ብላ ብለው ጉልቻ አንስቶ ጎኔን አለው ከጎኔም ጎኔ ኩላሊቴን እናቴን ጥሯት መድሓኒቴን እሷን ካጣችሁ መቀነቷን አሸተዋለሁ እሷን እሷን..." ይላሉ።
ኩላሊቴን ሳይሆን ልቤን ካለው ነገር እንደ ወጌሻ የእናት ፍቅሯ አሽቶ እንዳይጠገኝ እናትዬ ካረፈች ልክ 3 ዓመቷ ነው። እርሷን እርሷን የማሸተው መቀነት ባትተውልኝ ዘመኗን አብሪያት ስኖር የምትከፍታት አስናቀች ወርቁ ስቀመጥ፣ ስነሳ፣ስተኛ ስጓዝ እሰማታለሁ፣ በትዝታ ክራሯ አንጀቴን እየከረከረች፣ ከምናፍቃት እናቴ እቅፍ ትጥለኛለች።
ከአመሻሽ ገበያተኛ መኖሪያችንን ልትቃርም ወደ ጉሊቷ ልትመለስ ስትል "እንቅልፍ ጥሎሽ ማደሪያ እንዳታሳጪኝ ሳትሸነቁሪ ገርበብ አርገሽ በሩን ተይው እሺ " ትለኝና ፣ መለስ ብላ ደግሞ "እንዳይደብርሽ ቴፑን ክፈቺ" ብላኝ እስክትመጣ የተገረበበ በሬ ላይ ዓይኔን ጥዬ ከአስናቀች ወርቁ ጋር የምጠብቃት፣ ተመልሳ ለራታችንን የሚሆን ስታዘገጃጅ ከጎኗ ተቀምጬ የእርሷን ወግና አስናቀችን እኩል እየቀዳሁ ዝም ብዬ የማያት፣ ስነሳ እንደ ጠዋት ዜና ከቁርሳችን እኩል ት/ቤት እስክሄድ የምሰማት፣ እናቴ ስትደሰት፣ ስታዝን፣ ስትሰራ፣ ስትቆዝም ሁሉ ከዚህች ሴት ወዲያ የማታውቅ የምትመስለኝ እንደውም ዘመድ ረግጦት የማያውቅ ቤታችን ውስጥ አስናቀችና ክራሯ የልብ ዘመዶቻችን ነበሩ።
አሁንም በትመጣ እንደው ገርበብ ያረኩት በሬ ኩላሊቴን ሳይሆን፣ ልቤን ወዳለው ሰው በረርኩ።
ሳገኘው ሁለተኛ ዓመት የግቢ ተማሪ ነበርኩ።
እንደለመድኩት ኤርፎኔን በጆሮዎቼ ከትቼ አስናቀችን እየሰማሁ፣ ቦርሳዬን ይዤ ልወጣ ስል በአንዱ አልጋ ከላይ ጸጉሯን እየሰራች ያነበረችው ማሂ " እንደለመድሽው ገርብብ አድርገሽ ሄደሽ ከዚህ እንዳታስወርጂኝ ፣ በሩን ገጥመሽ ዝጊው አለችኝ ፈገግ ብላ በፍጹም ሰው ካላስታወሰኝ በቀር በር እስከመጨረሻው ዘግቼ አልወጣም፣ እንደ እናትዬ ገርበብ እንዳለ ነው የምተወው እንደኔ በተስፋ የሚጠብቀኝ ካለ ብዬ ይሆናል።
በሩን እንዳለቺኝ ገጥሜ ከላየረብሪው ስደርስ ከውስጥ በፍጥነት እየተመናቀረ የሚወጣ ልጅ ገፈታትሮኝ በእጄ ያለውን ስልክ አስጣለኝ
"ቀስ አትልም? ያምሀል" ልለው ስዞር ቀድሞኝ "ያምሻል" ብሎ እየጠራ ያለው ስልኩን አንስቶ ወደ ላይ ሄደ
በሆዴ "ሆ ያምሻል? " አልኩና የወደቀ ስልኬ ደህና መሆኑን አገላብጬ አይቼ ወደ ለመድኩት ቦታዬ ስሄድ ተይዞ ተበቀኝና ከአጠገቡ ካለው 4 ሰው የሚያስቀምጥ ወንበር ሄጄ ከፊትለፊቴ የተከፈተ ላፕቶፕ ቦርሳውን ዞር አድርጌ ተቀመጥኩ። ትንሽ ቆይቶ ወዳለሁበት ወንበር በፍጥነት እርምጃ የደረሰ፣ የሚያለከልክ ልጅ ተቀመጠ። ያ የገፈተረኝ። ራሱ ገፍትሮ ደርሶ ያምሻል ማለቱ አናዶኝ ነበርና ፊቴን አጠቆርኩ እርሱ ግን ሀሳቡ ሁሉ በስልኩ ላይ ነበርና የሆነ ነገር ሊሰማ ወደ ጆሮው ሲያስጠጋ አልሰማ ስላለው ያጠቆርኩበት ፊቴን ሳያይ ላፕቶፑ ላይ የተሰካውን ኤርፎን ሲነቅለው ሲሰማ የነበረው ሙዚቃ ላይብሪውን አመሰው።
በራኬብ ቤት እንደተንጠለጠለ ቀይ ግምጃ የጠላው ውቃቢዬን አባሮ መውደድ ሰፈረበት፣ "ያመሃል እንዴ" ብላ በጩኸት እንደ ኢያሪኮ ልታፈርሰው የነበረች ምላሴን መሰብሰቤ በጀኝ። እንደ ራኬብ ከመፍረስ የሚታደገው ቀይ ግምጃ ከላፕቶፑ ወጣች ።አስናቀች ወርቁ
ፈገግ አልኩ
ሰው ሁሉ ወደርሱ በማየቱ አይኖቹን የሚያሸሽበት ነገር ሲፈልግ ፈገግ ብለው የሚያዩት ዓይኖቼ ላይ አረፈ።
ግራ በተጋባ ፊቱ ገረመመኝና፣ የተከፈተውን ለመዝጋት አቀረቀረ።
"ደህና ነህ "አልኩት ቀስ ብዬ
ከሰው ጋር ገጥሞ አለማውራቴ ጉድ ባስባለበት ግቢ የማላውቀውን ልጅ ደርሼ ደህና ነህ ማለቴ ጉድ ነበረ።
ከዚያ ቀን በኋላ ከዚያች ወንበር ከፊትለፊቱ መቀመጥ ልማዴ ሆነ። በመተያየት፣ ሰላምታ፣ ከሰላምታ ወደ መጠያየቅ ወደ መተዋወቅ ተሻገርን። በላይብሪ የታጠረ ድንበራችንን ሰብረን የቀንተቀን ጓደኛ ሆንን
"የት ነሽ?" ለሚለው ጥያቄ
"ሱራፌል ጋር "የሁልጊዜ መልሴም ሆነ።
ብዙውን ጊዜ የዛ ቀን እርሱንም ልቡንም ስላመናቀረችው ቤዛ የምትባል ሴት ይነግረኛል፣ ልክ የእናትዬን ወግና አስናቀችን ዝም ብዬ እንደምሰማ ሁሉ እንዴት፣ ወዴት፣ መቼና ምን ሳልል ዝም ብዬ እሰማዋለሁ። አውርቶኝ፣ አውርቶኝ ሲበቃው "አውርተሽኝ አታውቂም አውሪኝ እንጂ" ይለኛል። ዝም እለዋለሁ። እጆቼን ይይዝና "ነገ ስንገናኝ አንቺ ነሽ የምታወሪው" ይለኝና የያዛቸው እጆቼን ከዛ ግንባሬን ይስመኛል ። ዝም ብዬ አየዋለሁ። "ከመሄዳችን በፊት ግን አንድ አስናቀችን" ብሎ አንዱን የኤርፎን ጆሮ ይሰጠኛል። ትከሻው ላይ ራሴን ጥዬ፣እርሱ በጸጉሮቼ እየተጫወተና ለምን ለእርሱ የምትዘፍን እንደሚመስለው እየነገረኝ ዳግም እንደ እናትዬ የእርሱን ወግ ከአስናቀች ጋር አደምጣለሁ።
እኔ ዝም ብሎ በማዳመጥ ብኖርም ግን ህይወት ዝም አትልምና የት፣ ምን፣ እንዴት ያላልኳት ቤዛ ዳግም ተመለሰች። እንዲሁ አንድ ቀን ከመሄዳችን በፊት አስናቀችን እየሰማን ስልኩ ጠራ አየሁት "ቤዝዬዬዬዬዬ" ይላል ብዙ ዬ ነበረው። ከስልኩ የነበረቀውን ኤርፎን ነቅሎ ሊያወራት ከኔ ራቅ አለ። ከዚያች ቀን በኋላም ከእኔ ራቅ ራቅ እያለ ሄደ ። እኔም በኋላ ማናት ብዬ መልኳን እንኳን ለማየት ያልጠየኳት ቤዛን አወኳት፣ አብረው። ወትሮ ነገርን መዝጋት የማያውቀው ጎኔ ባስለመደኝ ሰዓት እስኪደውል እጠብቃለሁ፣ በየሄድንባቸው ቦታዎች ልክ እንደናትዬ እስኪመጣ አያለሁ ግን አልነበረም። እርሱ ገርበብ አድርጎ የጠበቃት ፍቅሩ ስትመለስ፣ የኔን በር ገርበብ አድርጎት ሄደ።
ሶስተኛ ዓመት ከዛም ወደ መመረቂያ ዓመቴ ስገባ ገርበብ ያረኩትን ልቤን ለራሴ ስል ዘጋሁት። ግን እሰማለሁ "ቤዛ እኮ ጥላው ሄደች በናትሽ የታባቱ" የዶርሜ ልጆች እኔን ሊያስደስቱ እየተሳሳቁ ያወጉኛል። ዝም።" ደግሞ ሌላ ሴት ይዟል ማን ነው ስሟ" ይጠያየቃሉ። ዝም።
የቤዛን እጆቿን አይዛትም ነበር ፣ በጸጉሮቿ አይጫወትም፣ በመሀላቸው ገርበብ ያለ ክፍተት አለ፣ ሌላም ካሏት፣ ከሌላዋም፣ ከቀጣየም አብሯቸው ሆኖ አየዋለሁ ፣ በሴቶቹና እሱ መሀል እንደ በሬ የተገረበበ ክፍተት አለ። ዝም። ባለበት ቦታ ካለሁ ዓይኖቹ ግን የሆነ ነገር ሊሉኝ በመፈለግ እኔ ላይ ናቸው።
የመመረቂያ ቀናችን ደርሶ፣ ተመርቀን እንደ ነገ ልንሄድ እንደ ዛሬ ከግቢው ቡና ቤት ተሰይመናል። በአንድ ጓደኛችን ስልክ እዛው ካለው ሞንታርቦ ስልኩን አገናኝተን ሙዚቃ እየከፈትን የስንብት እንጨዋወታለን። የነርሱ ዲፓርትመንት ለመመረቅ ሁለት ዓመት ቢቀረውም እግር ጥሎት ከጓደኞቹ ጋር እኛ ከተቀጥንበት ፊትለፊት መጥቶ ተቀመጠ። ዓይኖቹ ሰውነቴ ላይ እንደሆኑ አውቄዋለሁ ግን ወደ ማብቃቱ አካባቢ ከመሄዳችን በፊት" አንቺ የምትፈልጊው ሙዚቃ የለም?" አለኝ ስልኩን ከሞንታርቦ ጋር ያገናኘው ጓደኛችን። ያለችኝን አንድ አስናቀችን ላኩለትና ከፈታት። ቀና ብዬ ፊትለፊት አየሁ፣ አየኝ እስከ መጨረሻው ከመሄዴ በፊት አንድ አስናቀች። በዝምታ
By Gabriela
@wegoch
@wegoch
@paappii