📚
ለ Entrance Exam ውጤታማ የአጠናን ስልትሰላም ውዶች ዛሬ ስለ-አጠናን-ስልት ላወጋችሁ ወደድኩ።
✅ በትምህርት አለም ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ እንደ Body guard የምናየው ነገር ቢኖር ንባብ ነው። ትምህርት እና ጥናት (ንባብ) የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸዉ፤ እና ብዙዎቻችን ንባብ አስፈላጊ መሆኑን እናውቃለን፤ ማንበብ እንዳለብንም እናምናለን ግን በአንድም ይሁኑ በሌላ ምክንያት አናነብም። አንገርምም ?
ግን የምር ለምን አናነብም ❓
✅ ለንባብ እንቅፋት ከሚሆኑብን ነገሮች መካከል ፦
1⃣ ለራስ ዝቅተኛ ቦታ መስጠት ( ባነብም አይገባኝም የሚል እሳቤ) አንዱና ዋነኛ ነው፤ እስቲ ይሄ አይነት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሆነ ነገር ልበል ፦
😀 አንባቢ ለመሆን ስናስብ ማድረግ ያለብን ቅድመ ሁኔታዎች ፦ ( የምርም ይሰራል )
🖱 class አለመቅጣት ( አስቸኳይ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር መቅጣት የለብንም፥ class ከገባንም በኃላ ትኩሰት ሰጥተን መከታተል፤ short note መውሰድ፣ እንደሰማውት ከሆነ አሁን አሁን መምህራን ከሚፅፉት ይልቅ ሚያወሩት ፈተና ላይ ማምጣት ይቀናቸዋል፤ እና በሚያወራበት ጊዜ ከአፍ ከፍ እየለቀምን note መያዝ ይጠቅማል
🖱 ሁል ጊዜ ቋሚ የሆነ የንባብ ፕሮግራም ሊኖረን ይገባል፤ ያለንበትን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ቋሚ ፕሮግራም ቀርፀን ወደ ተግባር መቀየር።
➡️
መከተል ያለብን የንባብ ሙድ በተመለከተ የራሴን ሙድ ላካፍላችሁ፥ SQ3RA ይባላል detail ለማየት ያህል ፦
✏️ S= Survey ( የገረፍታ ንባብ ማለትም ስለምናነበው ነገር ለማወቅ ይረዳናል፤ ለ 1 ገፅ ምን ያህል ደቂቃ ይበቃል ካላችሁ ደግሞ minimum 4 min )
🔄 Q= Questioning( by using WH questions, why... How.. በሚሉት logical ጥያቄዎች ማውጣት፤ አስተውሉ ምናወጣው ጥያቄ አመራማሪ እና ከበድ ማለት አለበት።)
🔄3R=3 round Reading (እስኪገባን ድረስ ደጋግመን ማንበብ)
🔄 A= answering the questions
💻 ይሄን ካረጋችሁ ቀለሜነት የግላችሁ ነው ፤ Entrance Exam ተሰቀለ ማለት ነው ።
በመቀጠል ደሞ በምናነብበት ጊዜ የ formula ትምህርቶችን ለብቻ formula ለይተን ብናስቀምጥ ፤ የሽምደዳ ትምህርቶችን ስናነብ በ presentation መልክ (ማለትም ድምፃችንን ቀንሰን ለራሳችን ማነባነብ) የተሻለ እንዳይጠፋብን ያደርጋል።
🔥
ስለ ፈተና አሰራር 🤔 ብዙ ጊዜ ጎበዝ ተማሪዎች 'የፈተና ቀን አይጠናም' ይላሉ : ነገር ግን ይሄን ለማድረግ በጣም አንባቢ እና ሁሌ ትምህርቱ ሳይጠፋ ጭንቅላት ውስጥ ማቆየትን ይጠይቃል ።
ይህ ደግሞ አድካሚ ነው። ስለሆነም መሸምደድ ያለባቸው አጭር ነገሮች : formulaዎች: ሠንጠረዦች እና መሠል ነገሮች የፈተና ቀን ሲደርስ ቢሸመደዱ የተሻለ ይሆናል።
📚 ስለ ፈተና አሠራር ደግሞ paragraph ካለ ከሱ አለመጀመር: እንደ History እና Biology ያሉ ትምህርቶችን በትዕግሥት ማንበብ: የmaths ትምህርት መምህሮች በብዛት ጭንቅላታቸው ፈጣን ስለሆነ ምን ብላችሁ ልትሳሳቱ እንደምትችሉ ያውቃሉ ስለሆነም በቀላል መልስ ከመጣላችሁ ደግማችሁ ስሩት: ከባድ እና መልስ የማታገኙላቸውን ጥያቄዎች እለፉት ፤ በቃ አትችሉትማ 😀፤ ብዙ ተማሪ ሚሸወደው ደግሞ ለ physics ትምህርት ከ concept ይልቅ formula የሚጠቅም ይመስለዋል ነገር ግን ባብዛኛው concept ነው: እና ዋናው ነገር ፀንሰ ሀሳብ ነው ።
🔒 Maths እና Physics Entrance ላይ 100 ለማምጣት ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች :
📝
Mathematics ✅ይህ ትምህርት በቅድሚያ በሚገባ ማዳመጥ ይጠይቃል ፤ ምክንያቱም አንዴ ካመለጠ መልሶ ለመረዳት ይከብዳል ። እና በሚጠናበት ወቅት እንደ biology ሁላ ቀጥታ እየገለጡ ማንበብ ነው ። እዚጋ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር, ስናነብ አብረን የተሰሩትን ጥያቄውች ማንበብ አለብን ፤ እና እንዴት እንደመጣ ያልገባንን ለይተን መጠየቅ ይኖርብናል ።
📝
Physics ✅ አመናችሁም አላመናችሁም እንደ Physics ቀላል ትምህርት የለም ፤ ግን ሙዱ ሊገባችሁ ይገባል ፤ በመሆኑም ይህንን ትምህርት ከመፅሐፍ ማንበብ የተሻለ ይህናል ። formulaዎቹን ለይቶ ማጥናትም ጠቃሚ ነው ፤ እና ጥያቄውችን በደንብ መለማመድ ያስፈልጋል ....በቀጣይ ብዙ ነገሮችን አጋራችኋለሁ።
ያም ይሁን ይህ እነዚህ 2 ትምህርቶች ላይ ጥሩ ውጤት ባይመጣም ተበሳጭቶ
'ለኔ አልተፈጠረም' ማለት አያስፈልግም ። መሞከር ነው የማይሳካ ነገር የለም...አንድ ጊዜ ጭራውን እስከምትይዙት ነው የሚያለፋችሁ።
Share :
🌐
@WENDETUTORIAL 🔂