💐የእግዜር ልጓም💐
ክፍል 23
ተከታታይ ልብ-ወለድ
✍Aksan Adane
........... ላገኘው ወደ ተኛበት ቦታ ሄድኩ :: ገና የክፍሉን በር ከመክፈቴ ሊበርር ምንም አልቀረው
:-ዜማ እንዴት መጣሽ አየሁት እኮ አየሁት ዜማ::
:-ማንን ?
:-አየሁት ዜማ የት አግኝቼ ልንገርሽ?.
ስለ አቶ ዴቪድ ነው? ምንድነው ሚያወራው ልጁ?ምንድነው
የሆነ ደስታም መገረምም በተቀላቀለው ስሜት ነበር የተቀበለኝ :: ተጠግቼ እጄን ዘረጋሁለት :: አለባበሴ ሁኔታዬ ግራ ሳያጋባው አልቀረም ከእግር ጥፍሬ እስከ ራሴ እያየኝ አአአንንቺቺ ዜማ ነሽ ? ራስሽ ነሽ? እንዴ መንፈስ መሠልኩህ እንዴ ከግድግዳ ጥግ የተቀመጠውን ወበርን ወደ አልጋው አስጠግቼ ተቀመጥኩ :: በሩን ዝጊው አለኝ ኦዉዉዉ እሺ ብዬ በሩን ዘጋሁት ::
:-ሀኪሞችህስ?
:-ወጥተዋል ::
:-አሁን በጣም ደህና ትመስላለህ ለምን እንደዛ አደረክ አልልህም ግን የሆነ ነገር ብትሆን ፀፀት ይገድለኝ ነበረ ዚያድ ::
:-ዜማ አመንሻቸው ማለት ነው? ምን አስነክተው ነው የቀየሩሽ በዚህች አጭር ጊዜ ሁሉ ነገርሽ እነርሱን እኮ ነው የሚመስለው ::
:- አረጋጋው ዚያድ ወደ ጆሮው ተጠግቼ እየተወንኩ ነው አልኩት ::
:- እየተወንኩ ማለት ?
:-ይከዉልህ ዚያድ የአቶ ዴቪድ ንግግር ትውስ አለኝ ስለ እርሱ ለማንም እንዳልናገር ያስጠነቀቀኝ ::እእእእእእ ምንነቱን አሁን አልነግርህም ግን ተመሳስዬ እያስመሠልኩ እንጂ በጌታዬ ቀልድ አላውቅም::
:-አንተ ምንድነው አየሁ አየሁ ያልከኝ?
መርዙን ጭልጥ እንዳደረኩት ከደቂቃዎች በኋላ የሆነ ነገር ምንጭቅ አድርጎ ወሰደኝ አንዲት የብርሃን ጭላንጭል በሌለበት ፀጥታ ቦታ ቀጥላም ነብሴ ከደመና በላይ ከፍ ከፍ ከፍ አለች ደመናውን እየሰነጠቀች በኃይል ትበር ነበር :: በከፍታ ላይ ሆኜ ክንፌ እየተርገበገበ ታላቅ ከተማ አየሁ ታላቅ ነበረች ውበቷ ግሩም ነበር በቃለ የማይገለፅ ውበት የነገስታት ከተማ ትመስላለች:: ሁሉ ሰዉ ደስተኛ ነው ::
ወዲህ እና ወዲያ ይቦርቃል :: ዋዉዉዉዉዉ እዚህ ነበር መኖር ወርጄ ልቀላቀላቸው አማረኝ ::ይህን እያሰብኩ ወዲያው እሳት ወረደባት ምንጩ የማይታወቅ እሳት ::አንዳንዱ እሳቱን ያላየ ባለበት ድርጊቱን ቀጠለ ::እንዴ ምን እየተደረገ ነው ኸረ አለቃችሁ ነደዳችሁ እያልኩ እጮህ ጀመር ::ርቀታችን ለየቅል ነበርና ማንም አልሰማኝም ስትቃጠል አየሁ ፈራርሳ ባድማ ሆነች ያደነቅሁት ውበቷ ዶቃአመድ ሆነ :: አዘንኩ ውይይይይይይ ምንድናት ይህቺ እንዲ በሚንቀለቀል እሳት የምትነድ ? ጥያቄ ፈጠረብኝ::
ይህቺ አንተ የምትኖርባት ዓለም ናት::
ከበስተኋላዬ የተዋበ ልብን የሚያልፈሰፍስ ድምፅ ተሰማኝ እንዴት ያለ ድምፅ ነው ብዬ ለመዞር ገና ሳስብ የብርሃኑን ጨረር መቋቋም አልቻልኩም ::

💐💐 @wengelbeArt 💐💐
እንኳን መልኩን ላየው ከፊቱ የሚወጣውን
ብርሃን መቋቋም አቃተኝ እና በጉልበቴ ተንበረከኩ በቃ እሷቱን ያዘነበው ሰዉ ነው ሚሆነው ሊፈጀኝ ነው::አለቀለኝ እያልኩ
አንተ ማነህ? አልኩት
ድምፁ በጆሮዬ ሲፈስስ ያለመልማል እኔ ኢየሱስ ነኝ አለኝ::
ታላቅ ፍርሃት ወደቀብኝ ኢየሱስ ? ኢየሱስ ኢሳ?
አዎን ኢሳ ብለህ የምታውቀኝ ያለሁ የነበርኩ ለዘለዓለምም የምኖር እኔ ነኝ አለኝ::
ዜማ በቃ ከአሁን ከአሁን ፈጀኝ ብዬ በሰቀቀን አለቅሁ ::
እባክህን አታጥፋኝ እባክህ የአሁኗን ከተማ በእሳት እንደመታህ በቁጣህ አታጥፋኝ አልኩት :: ቀና ብዬ እጅ ለመንሳት ስሞቅር በቅፅበት በብርሃን መካከል ያየሁት መልክ እንባው ይወርድ ጀመር ከቀድሙ በእጥፍ አበራ
ወደ እኔ እንዳተረቀርብ ግዜህ ገና አልደረሰም ::
ያየኸውን ትመሠክራለህ መፍጠርም ማጥፋትም ዘለዓለማዊነትም ህያውነትም የእኔ ነው በስሜ የሚመጡ ሁሉ የሚያምኑብኝ የዘለዓለም ህይወት አላቸው ያርፋሉ በመንግስቴ ይሰማራሉ ::
አሁን የምትኖርባት አለም አትቀጥልም ትጠፋለች አሁን ካየኸው በእጥፍ እሳት ትቃጠላለች በጎቼን ግን እሰበስባቸዋለሁ ::
ለዘለዓለምም ከእኔ ጋር ይኖራሉ ::
እሺ ንጉሥ ሆይ አታጠፋኝም?
:-የምህረት ደጆች አልተዘጉም አላጠፋህም ታርፋለህ ::
ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም አቤቤቤቤቤቤቤቤትትትትትትት እንዴት ያለህ መሀሪ ነህ ብዬ ጮኹኩ ከጩኸቴ ሳበቃ ያንኑ ሰዉ በደም የተጨማለቀ ነጭ ልብስ ለብሶ አየሁት እጆቹ ቀዳዳ ነበራቸው እግሮቹም እንደዚያው ከአናቱ ላይ እሾህ ተከምሯል ደነገጥኩ ይሄ በፊልም ሲያሳዩን ድራማ ነው የምንለው ነገር አይደል እንዴ?
በውስጤ ነበር ያልኩት ድራማ አይደለም አንተ ትድን ዘንድ ስለ ሀጢያትህ ዋጋ እከፍል ዘንድ ይህን ሆኜአለሁ እወድሃለው እያለኝ ጀርባውን ሰጥቶኝ ወደ ታላቅ ብርሃን ገባ ቆይ አውራኛ አትሂድ አንዴ ልንካህ እባክህ አንዴ ልንካህ ምንም መልስ የለም ወደ ታላቁ ብርሃን ዘለቀ አቤት ፍቅርርርርርርር ብዬ ስጮህ ከከፍታው ላይ ተወረወርኩ እየጮኹኩ ስመጣ ራሴን እዚህ አልጋ ላይ እየጮኹኩ አገኘሁት ዜማ አየሁት እኮ እምባው እኔንም አስለቀሰኝ ተጠግቼ ከቀፍኩት ወዲያው በታላቅ ሀይል በሩ ተከፈተ ወደ 10 የሚደርሱ ሰዎች ነበሩ :: አንደኛው አጠገቤ ደርሶ በጥፊ ደረገመኝ እሺ የኛ ተዋናይ አንቺ ነሽ ጌታችንን ልታታይ ምትሞክሪው? አንቺ ትንኝ.....
........ይቀጥላል.......
✍written by Aksan Adane
💐💐 @wengelbeArt 💐💐
💐💐 @wengelbeArt 💐💐