(እግዚሐር ማለት ለኔ..)
እግዚሐር ማለት ላንተ
ብሎ ቢጠይቀኝ
እስክመልስ ነበር እድሜዬ ያለቀኝ
እርሱ ማለት ለኔ
ብዬ እንደፃፍኩት
እስከዛ ድረስ ነው መኖርን የኖርኩት።
;
እሱ ማለት ለኔ...
እናት አባት እህት ወንድም
ጓደኛዬ በመውደድም
ተንከባክቦ ያሳደገኝ
ከነ ክምር እድፍ ጎኔ
ሞግዚቴም ነው አምላክ ለኔ።
ያምላክ' ወጉን ለኔ ጥሎ
ከመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ
አጀገኖ በጣር ልቡን
አንጠባጥቦ የደም ላቡን
የገደለ ስጋ ነፍሱን በጭካኔ
አዳኜም ነው አምላክ ለኔ።
ከሰማያት ከአሪያም ዘንድ
ከራሱ ላይ የደፋ ዘውድ
ህዝብ ኩሉ የሚወደው
ግርማ ሞገስ የሚያውደው
የሚገዛ አለማትን
በሚቃጠል በፍም ወኔ
ንጉሴም ነው እግዚሐር ለኔ።
የሲኦልን ደጃፍ መዝጊያ
ከነውጥ አለም መሸሸጊያ
በሁካታው በማዕበሉ
ቢተራመስ አለም ሁሉ
የሚያኖረኝ በእርጋታ
አለኝታም ነው ለኔ ጌታ።
እርሱ ማለት ለኔ
ብዬ እንደፃፍኩት
እስከዚህ ድረስ ነው መኖርን የኖርኩት።
እግዚሐርኮ ለኔ...
:
:
:
:
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
@wengelbeArt
እግዚሐር ማለት ላንተ
ብሎ ቢጠይቀኝ
እስክመልስ ነበር እድሜዬ ያለቀኝ
እርሱ ማለት ለኔ
ብዬ እንደፃፍኩት
እስከዛ ድረስ ነው መኖርን የኖርኩት።
;
እሱ ማለት ለኔ...
እናት አባት እህት ወንድም
ጓደኛዬ በመውደድም
ተንከባክቦ ያሳደገኝ
ከነ ክምር እድፍ ጎኔ
ሞግዚቴም ነው አምላክ ለኔ።
ያምላክ' ወጉን ለኔ ጥሎ
ከመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ
አጀገኖ በጣር ልቡን
አንጠባጥቦ የደም ላቡን
የገደለ ስጋ ነፍሱን በጭካኔ
አዳኜም ነው አምላክ ለኔ።
ከሰማያት ከአሪያም ዘንድ
ከራሱ ላይ የደፋ ዘውድ
ህዝብ ኩሉ የሚወደው
ግርማ ሞገስ የሚያውደው
የሚገዛ አለማትን
በሚቃጠል በፍም ወኔ
ንጉሴም ነው እግዚሐር ለኔ።
የሲኦልን ደጃፍ መዝጊያ
ከነውጥ አለም መሸሸጊያ
በሁካታው በማዕበሉ
ቢተራመስ አለም ሁሉ
የሚያኖረኝ በእርጋታ
አለኝታም ነው ለኔ ጌታ።
እርሱ ማለት ለኔ
ብዬ እንደፃፍኩት
እስከዚህ ድረስ ነው መኖርን የኖርኩት።
እግዚሐርኮ ለኔ...
:
:
:
:
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
@wengelbeArt