ቀን፡- 10/03/2017 ዓ/ም
ማስታወቂያ!!
ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!!
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታችሁ ለመማር ከትምህርት ሚኒስቴር ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ/ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ህዳር 26 እና 27 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በማሟላት በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
1ኛ) ከስምንተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁበት ሙሉ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁ (ሠርተፊኬትና ትራንስክሪብት) ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
2ኛ) አራት 3x4 መጠን ያላቸውን ፎቶ ግራፎች፤
3ኛ) ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
ማሳሰቢያ፡-
• ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፤
• በ2016 ዓ/ም 1ኛ ሴሚስተር በውጤታችሁ መሠረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ እናሳስባለን፤
• በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሚድያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት!!