ህዳር 11 ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ::
(ህዳር 11/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን የስርዓተ ፆታ ዘርፍ "ሕፃናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው!" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ 19ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ሕፃናት ቀን በአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት አክብሯል ::
ቀኑን ስናከብር ለህፃናት መብት መከበር በጋራ መስራትና ለህፃናት እንክብካቤና ድጋፍ ማድረግ አለብን ያሉት የቢሮው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ ኢትዮጵያ የህፃናትን መብት ለማስከበር ዓለም አቀፍ ስምምነት የፈረመች ሀገር እንደመሆኗ የሕፃናትን መብት በማስከበር አድሎአዊ አሰራርን ለማስቀረትና በምቹ ቦታ የመኖርና የማደግ መብታቸውን ለማስከበር የትምህርት ተቋማት ድርሻ ትልቅ መሆኑን አብራርተዋል ::
አያይዘውም ለህፃናት መብታቸውን እንዲያውቁ ማስተማርና መሻታቸውን ማሟላት እንዲሁም ህፃናትን ለማዳመጥ ራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ይገባል ብለዋል ::
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ፋሲካ ወርቁ በበኩላቸው የሕፃናትን ቀን ከማክበር ባለፈ የህፃናቱን ሀሳብ በማዳመጥ የተሻለ ትውልድ ማፍራት የትምህርት ማህበረሰቡ ኃላፊነት በመሆኑ ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንወጣለን በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ::