ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የመጡ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።
(ህዳር 16/2017 ዓ.ም) ልምድ ልውውጡ በዋናነት በከተማ አስተዳደሩ ስላለው አጠቃላይ የመማር ማ ስተማር ሂደትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የቢሮው የማኔጅመንት እና የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ገለጻ ተሰቷል።
ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መነሻ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሆነው የተማሪዎች ምገባ እና ዩኒፎርምን ጨምሮ በነጻ እየቀረቡ የሚገኙ የመማሪያ ቁሳቁሶች በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲመዘገብ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ጠቁመው በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ የብዝሀ ቋንቋ ተግባራዊ መሆኑንም አመላክተዋል።
የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት የርዕሳነ መምህራን ሪፎርም በማካሄድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጠቁመው የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።