ዛሬ በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የብልፅግና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡትን አጠቃላይ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል ።
(ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም) ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ የሚዘልቀውን 21. 5 ኪ.ሜ የወንዞች ዳርቻ ልማት፤ እንጦጦ ፣ቀበና ፣ግንፍሌ አካባቢ 19.5 ኪሜ የሚሸፍን ወንዝ ዳርቻ ልማት ፣የካዛንቺስን መልሶ ማልማት ፤ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና 40.4 ኪ ሜ የሚሸፍን ኮሪደር ልማት እንዲሁም የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ገላን ጉራ የተቀናጀ የልማት መንደር እና የአካበባቢ ልማት ፤ የፒያሳ ልማት ተነሺዎች የገቡበትን የአቃቂ ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶች መኖሪያ መንደር ፤ የቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ተርሚናል እና የአቃቂ አዲሱ መንገድ የ37 ኪ.ሜ የአረንጓዴ ልማት ሥራ ፤ “የብርሃን አዳሪ ት/ቤት" እና የ "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተናል።
በጉብኝታችን የከተማችን መሠረተ ልማት አቅርቦት እና ቅንጅት በፍጥነት እያደገ ያለ መሆኑን፤ የከተማዋን ፅዱና ዉብ በማድረግ ገፅታዋን እየቀየረ ያለ ልማት ፣ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በፍትሀዊነትን እያረጋገጡ ያሉ ሰዉ ተኮር ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን እነዚህ ሥራዎች ብልፅግና ከባለፈው ጉባኤ ወዲህ በቃሉ መሰረት አዲስ አበባን ዉብ አበባ ለማድረግ የተገበራቸው ሥራዎች አካል ናቸዉ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ