🔰ዒሳ የአላህ ቃል ነውን?🔰
አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ከመፅሀፋቸው የዒሳን አምላክነት ለማሳየት ሲጠናቸው ወደ ቁርአን ይመጡና ቁርአን የዒሳን አምላክነት ያሳያል ብለው ይህንን አንቀፅ ይጠቅሳሉ👇
إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابنُ مرْيمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ
"የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው፣ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃል ነው፣ ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው”*፡፡
📚 ኒሳእ 4፥171
ይህንን አንቀፅ በመያዝ ዒሳ የአላህ ባህሪይ የሆነው የአላህ ቃል ነው ብለው ይሟገታሉ።
ለዚህ መልሳችን
➤➤1. በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ዒሳ መልእክተኛ መሆኑን ስለተጠቀሰ አምላክ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱ አምላክ ላኪ እንጂ መልእክተኛ አይደለም።
➤➤2. ሲቀጥል የአላህ ባህሪይ ፍጡር አይደለም። ዒሳ ደግሞ ፍጡር ነው። ማስረጃው👇አላህ ስለ መርየምና ልጇ(ዒሳ) ጂብሪል ለመርየም ያላትን ሲተርክልን እንዲህ ይላል
قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡
📚 ዒምራን 3:47
የአላህ ባህሪይ ፍጡር ካልሆነ ዒሳ ደግሞ ፍጡር ከሆነ ዒሳ ""የአላህ ባህሪይ የሆነው የአላህ ቃል"" ሊሆን አይችልም።
▶▶ እና ዒሳ የአላህ ቃል ነው ሲባል ምን ማለት ነው ከተባለ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የሰው ልጆችን ከአባትና ከእናት ፈጥሯል። ከዚህ አፈጣጠር ውጭ በተለየ መልኩ የተፈጠሩ አሉ። ለምሳሌ አደም እና ዒሳ።
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ አደምን ያለ አባት ያለ እናት "ሁን" በሚለው ቃሉ ፈጥሮታል።
ልክንደዚሁ ዒሳን ዐለይሂ ሰላምንም ያለ አባት "ሁን" በሚለው ቃሉ ፈጥሮታል።
ዒሳ የአላህ ቃል የተባለው አፈጣጠሩ ልክ እንደ አደም ከሌሎች ሰዎች በተለየ መልኩ ያለ አባት "ሁን" በሚለው የአላህ ቃል ስለተፈጠረ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል👇
إِنَّمَا قَوْلنا لِشيْء إِذا أرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن
فَيَكُونُ
ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ "ቃላችን" ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡
📚ነህል16፥40
➩ ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ልጅ አለው" ሲሉ አምላካችን አሏህ፦እንዲህ አለ
مَا كان لِلّه أن يَتّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سبحانَه ۚ إِذا قَضَىٰ أَمرا فَإِنّما يَقولُ لهُ كن فَيكُونُ
ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡
📚 መርየም 19፥35
➩ መርየምም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ መልስ፦
قالت ربّ أنىٰ يكون لِي وَلد ولم يمسسني بَشَرٌ ۖ قال كَذَلك اللّه يخلق ما يشاء ۚ إذا قَضَىٰ أمرا فَإِنّمَا يَقولُ لَهُ كن فيكون
፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡
📚 ዒምራን 3፥47
☝️ከነዚህ አንቀፆች ምንረዳው አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ዒሳን የፈጠረው "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደሆነ ስለነገረን ዒሳ የአላህ ቃል ነው ሲባል "የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ" ማለት ሳይሆን "ሁን" የሚለው ቃሉ ውጤት ("ሁን" በሚለው የአላህ ቃል የተፈጠረ ፍጡር) ማለት ነው።
➤➤3. በተጨማሪ በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ቃልን ለመግለፅ የገባው
➩ "ቃል" ለሚለው የገባችው ከሊማህ" كَلِمَة ሲሆን አንስታይ መደብ ናት። ይቺ ቃሊት አንስታይ መደብ ስለሆነች “አልቃ-ሃ” أَلْقَاهَا ማለትም “የጣላት” ተብላለች፥ ዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ “አልቃ-ሁ” أَلْقَاهُ ማለትም “የጣለው” ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው።
➤➤ 4. በቁርአንና በሀዲስ እነሱን እንድንከተል የታዘዝነው የሆኑት እና ስለ ቁርአን በበለጠ እውቀት ያላቸው አላህ በቁርአኑ የማታውቁ ብትሆኑ ጠይቋቸው ብሎ ያዘዘን የሰለፎቻችን(ሶሀቦች፣ታቢኢዮች፣አትባዒ ታቢዒን) ኡለሞች ዒሳ "የአላህ" ቃል"" ነው ሲባል በምን ተረዱት የሚለውን በማስረጃ እንመልከት👇
➩➩ ሰነዱን ወደ ቀታዳህ በማድረስ ቀታዳህ ረሂመሁላህ "ወደ መርየም የጣላት ቃል ነው" በሚለው አንቀፅ ላይ ቃሊቷ "ሁን" የምትለው ናት።" ብሏል
📚 ተፍሲሩ ጦበሪይ ሱራ ኒሳእ 4:171
وقال ابن أبي حاتم : حدثنا أحمد بن سنان الواسطي قال : سمعت شاذ بن يحيى يقول : في قول الله ( وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ) قال : ليس الكلمة صارت عيسى ولكن بالكلمة صار عيس
ኢብኑ አቢ ሐቲም እንደዘገበው፦ “አሕመድ ኢብኑ ሢናነል ዋሢጢይ እንደተናገረው፦ “ሻዝ ኢብኑ የሕያ"እንዲህ አለ፦ ”ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው” የሚለው አንቀፅ ላይ “ቃሊቷ እራሷ ዒሣ አልሆነችም፥ ነገር ግን በቃሊቱ ዒሣ ተገኘ እንጂ”።
📚 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ሱራ 4፥171
➤➤5. በተለምዶ በንግግሮቻችን አንዳንድ ጊዜ በቋንቋ ውጤት በመንስኤው (በምክንያቱ)ይጠራል። ለምሳሌ የሆነ አከባቢ መሬት መንቀጥቀጥ ወይም ከባድ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ሰዎች ይሄ የአላህ ቁጣ ነው ይላሉ።
ሰዎቹ የአላህ ቁጣ ነው ሲሉ ሚፈልጉት የአላህ ቁጣ ውጤት ለማለት ነው እንጂ
መንቀጥቀጡ፥ጎርፉ፥ረሀቡ፥አደጋው የአላህ ባህሪይ የሆነው ቁጣው እራሱ ነው ለማለት አይደለም። ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ፍጡራን ሲሆኑ የአላህ ባህሪይ የሆነው መቆጣት ደግሞ ፍጡር አይደለም።
የአላህ ቁጣ ለምን ተባሉ ከተባለ የአላህ ቁጣ ውጤት ስለሆኑ ነው።
በተጨማሪ ዝናብ ሲዘንብ የአላህ እዝነት ነው ይባላል።
ይህ ማለት የአላህ ሲፋ(ባህሪይ) የሆነው እዝነቱ ማለት ሳይሆን የእዝነቱ ውጤት ማለት ነው
ልክንደዚሁ ዒሳ የአላህ ቃል ሲባል የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ ሳይሆን የአላህ ቃል ውጤት(በአላህ ቃል የተፈጠረ) ማለት ነው።
➩ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ዒሳ ዐለይሂ ሰላምን ከሌሎች ሰዎች አፈጣጠር በተለየ መልኩ ልክ እንደ አደም "ሁን" በሚለው ቃሉ ስለፈጠረው "የአላህ ቃል" ተባለ እንጂ የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ ነው ማለት አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል👇
إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ"እርሱ" «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡
📚 ዒምራን 3፥59
➤➤➤አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን➤➤
https://t.me/iwnetlehullu1
ተቀላቀሉ ባረከላሁ ፊኩም☝️☝️