የፍርድ ቤት ዳኛው የገዳይን እጅ እያለቀሰ
የሳመበት ክስተት
እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር 1910 በቤሩት ምድር በአንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የሚርመሰመስ ሰው የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሳደባል።
አንድ መንገደኛ ውስጡ በግኖና በንዴት ጦፎ ከኋላ ኋላ ይከተለዋል። ቢላ በሚሸጥበት ሱቅ በኩል ሲያልፍ ወደ ውስጥ አቀናና አንዱን ቢላ መዞ በተሳዳቢው ጉሮሮ ላይ ሰካው። ወደ ውስጥ በመሰምጠጥ ደምስሩን በጥሶ ገደለው።
ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የቤሩት ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት አመታት በኋላ ወንጀለኛው ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አስጠራው። ተከሳሹ ችሎት ፊት ቆመ። አዳራሹ በሰው ተጨናንቋል። ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቷል።
"ሰውየውን ለምን ገደልከው?" የዳኛው ጥያቄ ነበር
"የአላህን መልዕክተኛን(ሰ.አ.ወ) ሲሳደብ ሰማሁትና በእጅጉ ተናደድኩ ስለረሱል ክብር ስል ገድዬ ለመሞት ራሴን አዘጋጀሁ በንዴት ገንፍዬ ጉሮሮውን በጠስኩት" ሲል መለሰ።
ዳኞቹ እርስ በርሳቸው ከተወያዩ በኋላ
"ሆን ብለህ የግድያ ወንጀል ፈጽመሃል ፍርድ ቤቱ የ15 አመት ጽኑ እስራት ፈርዶብሀል። ድርጊቱን የፈፀምከው በንዴት ነውና ቅጣቱ ግማሽ በግማሽ ተቀንሷል። ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ባመነበት ምክንያት የታሰረበት ጊዜ በቂ ስለሆነ እንዲለቀቅ ወስኗል መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት" የሚል ውሳኔ አስተላለፈ።
ዳኛው ከውሳኔው በኋላ "ፖሊስ ሆይ ወንጀለኛውን ፍታው" ሲል አዘዘ ከፍርድ ቤቱ የመቀመጫ ወንበርና ቅስት ወርዶ። ወደ ሰውዬው ቀረብ አለና "ልጄ ሆይ የምንወዳቸው ነቢን(ሰ.አ.ወ) የተሳደበውን ሰው በየትኛው እጅህ ነው የገደልከው?" ሲል ጠየቀ
"በቀኝ እጄ" አለ
"ልጄ እጅህን ዘርጋልኝ"
እጁን ዘረጋ
ዳኛው እያለቀሰ እጁን አቅፎ ይስመው ጀመር።
በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ በእንባ ተሞልተው ተላቀሱ። የቤሩት ፍትህ ሚኒስትር የፍርድ ቤቶች ዋና ሀላፊ ዳኛው የገዳዩን እጅ በመሳሙ ወደ መዲና እንዲዛወር ውሳኔ ተላለፈ። የዳኛው የዘወትር ህልም ተፈፀመ። አላህ ዱዓውን ተቀበለው።
"ጌታዬ ሆይ! የህይወቴን የመጨረሻ ቀናት ረሱል ባሉበት ከተማ ላይ አድርግልኝ ከሳቸው ጋርም አጎራብተኝ" በማለት ዱዓ ያደርግ ነበር።
ዳኛው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን እሱ ዩሱፍ አን-ነብሃኒ ይባላል።
የአላህ እዝነት በእርሳቸው ላይ ይሁን
@yasin_nuru @yasin_nuru