#እንድታውቁት
" የሀጅ ጉዞ ምዝገባ ጥር 15 ይጀምራል የሀጅ ጉዞ ዋጋ አሁን ባለው 625,000 (ስድስት መቶ ሃያ አምስት ሺ) ብር ነው " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ
የ1446ኛው የሀጅ እና ዑምራ ጉዞ ምዝገባ ከጥር 15 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ብቻ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል።
ምዝገባው ጥር 15/2017 በሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር የምዝገባ ጣቢያዎች ይጀመራል።
የሳውዲ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ያለው የምዝገባ ጊዜ አጭር በመሆኑ ሁጃጆች (ተጓዦች) በወቅቱ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀርቧል።
የዘንድሮ የሀጅ እና ዑምራ የጉዞ ዋጋ 625 ሺህ ብር መሆኑ ተገልጿል።
ምክር ቤቱ " የጉዞው ዋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የታየው የዶላር ጭማሪና በአየር መንገዶች ላይ ያለው የትኬት ዋጋ መናር ዋጋው ከፍ እንዲል አድርጎታል " ብሏል።
" የሀጅ ዋሃ ከዶላር አንፃር የ4,921 ዶላር ቅናሽ እንዲደረግበት ቢደረግም በብር ግን ጭማሪ አሳይቷል " ሲል ገልጿል።
ጠቅላይ ምክር-ቤቱ የአገልግሎት ዋጋን በመቀነስ በዕቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶችን በማጠፍና በሳውዲ የሚቀርበውን አገልግሎት ተመጣጣኝ እንዲሆን በማድረግ 108 ሺህ ብር ቅናሽ እንዲኖረው ማድረጉን አሳውቋል።
የዶላር ዋጋ ከፍ በማለቱ ግን ብሩ መጨመሩ ተገልጿል።
ባለፈው ዓመት ለአንድ ሀጅ ዋጋ አጠቃላይ ብር 329,000 እንደነበር ይወሳል።
@yasin_nuru @yasin_nuru