•አዎ አሁንም ቢሆን ዝም አትበሉ፣ አትዘናጉ፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለፈጠራችሁ አምላክ ለአላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ንገሩት፡፡ እሱ ጉዳያችሁን ይፈታል፣ አይቻልም ተብሎ የሚታሰበዉን ሁሉ ያገራል፡፡
አንዳንድ ጉዳዮች የናንተን እጅ ማንሳት ብቻ እየጠበቀ ይሆናል፡፡ እጃችሁን ወደ አላህ አንሱ አትፍሩ፣ አትፈሩ፣ አታመንቱ፣ አመቺ ጊዜ አትጠብቁ፡፡አንድ ሰው ብዙ እንዲሳኩለት የሚፈልጋቸው ሓጃዎች እያሉት እንዴት ይሰንፋል! እንዴት እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል!!፡፡
ብቸኝነት ያደከማችሁና መልካም ትዳር የምትናፍቁ፣ ጉዳያችሁ ከዓመት ዓመት መልስ ሳያገኝ የተንከባለለ አሁንም ወደ አላህ ተጠጉ፣ ከአላህ ጋር አውሩ፡፡ ሪዝቅ የጠበባችሁ፣ ድህነት ያዋረዳችሁ አላህ ሆይ ሪዝቄን አስፋ በሉት፡፡ ያሳሰባችሁን ማንኛዉንም ነገር ሳትፈሩ ሳታፍሩ ለምኑት፣ ጠይቁት፣ ተማፀኑት፡፡
©
እንግዳችንን በታላቅ የመልካም ስራ ድግስ እንቀበለው…የኢስቲጝፋር፣ ተውበት፣ ሰላት፣ ዚክር፣ ሰደቃ፣ ዘካና ሌሎችም ብዙ የኸይር አይነቶች የተሰበሰቡበት ቡፌ ያለው ድግስ የተደገሰበት ረመዻን መጥቶልናል ፤ እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን አላህ ፆመው ከሚጠቀሙት ባሮቹ ያድርገን።
ረመዿን ሙባረክ
https://t.me/asdajlahh