❤️ሀና ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍ ማኔ
ክፍል 1⃣6⃣
ይሄን ሱቅ መጀመሪያ ስንከፍተው ቤዛ ገንዘበን ሰጠችኝ ግን ምን ላይ ደረስክ እንዴት ሆነልህ የከፈትከው ሱቅ ምን አይነት ነው ሰዎች እየገዙህ ነው ወይስ አይገዙህም ብላ እንኳን አልጠየቀችኝም ሱቅ ሁላ የት አካባቢ እንደከፈትኩ ያወቀችው ቆይታ ነው በየቀኑ ዛሬ ስንት ሰራህ ይሄን ያህል ብራ አምጣ ከማለት ውጭ አንድም ቀን በርታ ወደፊት ይስፋፋል ብላኝ አታቅም ግን እኔ ሳይሰለቸኝ እየሰራሁ ብር ሴቭ እያደረኩ አንቺ እስክትመጪ የነበረው ደረጃ ላይ አደረስኩት።
ግን ሁሌም ሁሉም ነገር የሷ እንደሆነ ነው ምታወራው እኔ ደሞ ለፍቶ መና ሲሆንብኝ ግዴለም እያልኩ ዝም እላለሁ ግን ጭራሽ በራሴ አልጋ ላይ ከሌላ ወንድጋ ከባድ ነው አልኳት፡፡
እየውልህ ተረጋግተህ ስማኝ አንዳንዴ ሰዎች ትክክለኛ የኛ ጥቅምና ለኛ ያላቸው ፍቅር የሚገባቸው ካጠገባቸው ዞር ስንልና ከበፊቱ የበለጠ አምሮብን ጠንክረን ሲያዩን ነው፡፡
ስለዚህ በቃ ትናት ቤዛን ከሌላ ወንድጋ እንዳላየሀት ቁጥረው ቺት አላረገችብኝም ብለህ አስብ እራስህ ላይ ስራ ከዛሬ ጀምሮ በደንብ ሰአታችንን ስራ ላይ እናሳልፍ የገባ ከስተመር ሳይገዛ እንዳይወጣ እንታገል ከዛ ከሷ ለሱቅ መክፈቻ የተበደርካትን ገንዘብ መልስላት እሷ የማታቀው በደንብ ገበያ ያለበት ቦታ ሂድና በራስህ ገንዘብ በራስህ ተነሳሽነት የራስህን አዲስ ሱቅ ክፈት የዛኔ በራስ መተማመንህ ይመጣል እስከዛ ግን ምንም ነገር ቤዛ ላይ እንዳትቀየርባት አለችኝ
ሀሳቧ በደንብ ነበር የተመቸኝ በአዲስ ሞራል በአዲስ የስራ ፍላጎት ከቤት ተያይዘን ወጣን በለበስኩት ልብስ አድሬ እንደዛው ስራ ቦታ ስሄድ ስለደበረኝ ከተሰቀሉት ውስጥ አንዱን ሸሚዝ አንስቼ ለበስኩት ።
ገና በስርአት እቃ አወጣጥተን ሳንጨርስ ቤዛና እናቴ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ሱቅ መጡ ሀኒ ስታያቸው ወደኔ ዞረችና ጠቀሰችኝ እኔም ገና ሳያቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ውይ እማዬ ቤዚዬ ምነው በሰላም ነው በጠዋት የመጣችሁት አልኳቸው ሁለቱም ንዴታቸው ፊታቸው ላይ እየታየ የታባህ ነው ያደርከው እ ለቤዛ እናቴጋ ነው ማድረው ብለህ ዋሸህ እ ይሄ ምን የሚሉት ቅሌት ነው የት ስትንዘላዘል አድረህ ነው አለችኝ እናቴ ለመምታት እየቃጣት።
ነገሩን ለማብረድ ፈገግ እያልኩ አይ እማ ቤዚን የመሰለ ሚስት ቤት አስቀምጬ ሌላጋ ልንዘላዘል ምሄደው ምን አጥቼ ነው ብዬ ቤዛን ወደኔ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት ባንዴ የጠቆረው ፊታቸው ወደደስታ ተቀየረ ዝም ብዬ የተሰቀሉትን ልብሶች እያሳየሁ እነዚህንኮ ላመጣ ሄጄ ማታ መሽቶብኝ ነው ይቅርታ አስደነገጥኳችሁ አይደል በቃ ኑ እንደካሳ እንዲሆነኝ ቁርስ ልጋብዛችሁ ብዬ ይዣቸው ወጣሁ።
ምሳ ሰአት ላይ ሀኒ ባሏ መጥቶ ይዟት ወጣ ።
እኔ ግን ሀሳቤ ሁላ ገንዘብና ገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ ስለነበር ምሳ ሰአቱንም ሳልዘጋ እዛው ቁጭ አልኩ።
ወደሱቄ የመጣው ሰው ሁሉ
በክብር እያስተናገድኩ መሸኘቱን ተያያዝኩት,,,
ይቀጥላል...
ክፍል 1⃣7⃣ ከ 1⃣5⃣0⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
❤️ https://t.me/yefikirtelegramet ❤️