🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 1️⃣0️⃣
ሌላኛው ቆጣ ብሎ አይ እንግዲ ስርአት ያዝ አሁን እንደዚህ ጠዋትና ምሽቱ ተምታቶባት ስትንከራተት እያየህ ስሜትህ እራሱ ይታዘዝልሀል ብሎ ይቆጣውና ከባለቤቴ አጠገብ ያሸሸዋል።
እሷም የሰዎቹ አጥር ስር ተደግፋ ስታለቅስ አድራ ሌሊት ዶሮ ሲጮህ ተነስታ ጉዞ ትጀምራለች።
እኔ እሷ ያንን ሁሉ ስታሳልፍ ቤት ተኝቼ ልጁ አለቀሰ እያልኩ ስበሳጭ ነበር ።
በገጠር ጡጦ የለ አልሰጠው እንዲህ እንዳለቀሰ ነጋለት ጠዋት ላይ እንቅልፍ ወሰደው እሷም ክሷን ጨርሳ ለሷ ተፈርዶላት በፀሀይ ያንን ተራራ ስትሮጥ ትወርዳለች።
እንደገባች ደሞ እኔ ለምን ልጁን ትተሽ ሄድሽ ሰዎቹ ልጅ እንዳለሽ ካወቁ ላንቺ አይፈርዱልሽም አንቺን አይፈልጉሽም አደል ብዬ ቁጣ ጀመርኩ ማታ ወጥታ ያጋጠማትን ስትነግረኝ ግን በራሴ አፍሬ አንገቴን ደፍቼ ከቤት ወጣሁ።
እኔ እንደሴት ቤት ተኝቼ እሷ እንደወንድ ስትሆን ሞራሌ ተነካ ሆድ ባሰኝ ።
ብቻ ህይወት ቀጠለ ልጃችንም አንድ አመት ሆነው መቼስ ቁንጅናው ማማሩ የገጠር ልጅ አይመስልም ነበር እኔ በልጅነቴ የነበረኝን መልክ የሚያስንቅ ነበር የሱ ደሞ።
በየመንገዱ ያገኘኝ ሰው ሁሉ ልጁ ግን ያንተ ነው ካንዱ ከተሜ ዲቃላ ወልዳ ባንተ አሳባ እንዳይሆን እሷ እንደሆነ ጎዳና ስታድር መስጠቱን ለምዳዋለች ይሉኝ ጀመር።
ሞኝ እንደመከሩት ሆኖቦኝ የምር እሷን መጠራጠር ጀመርኩ በሰበብ ባስባቡ እየተነሳሁ ልጁ የኔ አደለም ማለቱን ተያያዝኩት ጭራሽ ከቤት እየወጣሁ እመቤትጋ ማደር ጀመርኩ ።
እሷ ግን ከለቅሶ ውጪ ምቴድበትም ስላልነበራት ዝም ብላ ተቀመጠች።
እኔ ጭራሽ ይባስ ብዬ አዲስ አበባ እሄዳለሁ እዛ ቀን ስራ እየሰራሁ እኖራለሁ አልኩኝ እሷ በየሄድኩበት እየመጣች እባክህ መሬታችንን እያረስን ልጃችንን እናሳድግ አለች እኔ አሻፈረኝ አልኩ።
በእናትና አባቴ ተስፋ ስለቆረጥኩ አዲስ አበባ መጥቼስ ማንጋ አርፋለሁ ሴት አደለሁ ሰው ቤት አልገባ ብዬ ጨነቀኝ አባቴንም ካሁን ቡሀላ አልፈልገውም አንድ ቀን ልጄ ምን ላይ ወደክ ብሎኝ ሳያውቅ ዛሬ እሱን ፍለጋ አልንከራተትም እኔ እሱን ለማግኘት እንደሚከብደኝ ያውቃል እሱ ግን እኔን ማገኘት ከፈለገ ገጠር መምጣት ብቻ ነበር ሚጠበቅበት በቃኝ አልኩኝ።
በዚህ ጭንቀት ውስጥ እያለሁ ልጄ ታመመ አንገቱ መተነፍስ እስኪያቅተው አበጠ።
ሌሊቱንም መተንፈስ ይቸገራል አይተኛም አፉን ለደቂቃ መግጠም አይችልም ከገጠመው ታፍኖ ይሞታል።
ያንን ስሰማ እንደ እብድ አደረገኝ የማደርገው ጠፋኝ ወደ ህክምና ወሰድንው መፍትሄ የለውም ጎረቤት ሁሉም ተስፋ ቆረጠ የተለያየ ባህላዊ መድሀኒት ተሞከረ ሁሉም ሳይሆነ ቀረ ተስፋ ቆርጠን በቃ ሞተ አለ ሁሉም ሰው።
ሌሊትና ቀኑ እስኪምታታብን ድረስ ከጎኑ ቁጭ አልን ከዛ ግን አጎቴ በጣም ጨንቆት ሌላ ሀገር ሄዶ የሚያቅ ሰው ይዞ መጣ ። በፈጣሪ እርዳታ የልጄ በሽታ ታወቀ አልቅት የምትባል ነገር አለች ጉሮሮ ላይ ተለጥፋ የምትቀር አታስተነፍስ አታስበላ አታስጠጣ ትክክለኛ መዳኒቷን ካላገኘች ከጉሮሮ አትንቀሳቀስም ተለጥፋ በየቀኑ እየገዘፈች እየገዘፈች ትሄዳለች።
ያ ሰውዬው ግን መዳኒቷን ያውቅ ነበርና አደረገለት ባንዴ ከጉሮሮው ተመንጭቃ ወጣች በጣም ትልቅ ናት በሱ እድሜ ይሄንን መቋቋሙ ሁሉም ሰው ተገረመ።
በዛ መሀል ሚስቴም ሰውነቷ ደካከመ አመመኝ አመመኝ አበዛች የገጠር ሰው በጣም ዝንጉ ስለሆነ ማርገዟን እራሱ አላወቀችም ነበር ።
ለካ ሁለተኛ ልጃችንን ካረገዘች በጣም ቆይታለች ጥርጣሬ ነበራት ግን ምታወራው ሰው አጥታ ነው ዝም ያለችኝ እንኳንም ጥያት አሌድኩ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩ።
በድጋሜ የእርሻ ወራት መጣ ያው የፈረደበትን አጎቴን ቦሮች ለምኜ እያረስኩኝ የባለቤቴ እንጀራ አባት መጥቶ አስቆመኝ መቼስ አንዴ ሀገሬው ላይ ፈሪ ተብሎ ስሙ የተነሳ ሰው በሁሉም የተናቀ ነው ።
ስንት አመት ስገብርበት የኖሮኩትን መሬት እናንተ አታርሱትም ፍታ ብሎ ከብቶቹን አስፈታኝ እሺ ብዬ እንደሴት ወደቤቴ ተመለስኩ ነገርኳት እያበደች ከቤት ወጥታ ሄዳ አስፈራራችው እሷ ወንድ እኔ ሴት ሆነን እኔ ፈርቼ ቤቴ ስመጣ እሷ ሄዳ ተጋፈጠችው።
እሱ እናንተ አታርሱትም እናትሽ ብትሞትም እኔም መብት አለኝ አለ።
እንደለመደችው ወደ ፍርድ ቤት ሄደች እርጉዝ ሆና ያንን ተራራ ተራራ ሳይመስላት ወጣችው ።
ከሰሰችው ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ተንከራተተች በድጋሜ እሱንም እረታችውና ለሷ ተፈረደላት እንደውም እስከዛሬ እሷ ጎዳና ላይ እየኖረች እሱ የሷን መሬት ለተጠቀመበት ካሳ እንዲከፍላት ተፈረደበት ባለቤቴ የሱን ምንም ነገር አልፈልግም አለች።
ከዛን ቡሀላ የሀገሬው ሰው በጀግንነቷ አደነቃት አንዳንዶች ክስ ሊካሰሱ ሲመጡ እሷን መጠየቅ ጀመሩ እናቷን,አጎቷን,እንጀራ አባቷን በክስ አሸንፋለችና ከሷ ብዙ ነገር እንማራለን ብለው ነበር አጠያየቃቸው ።
ብቻ ወንዱ ልጃችንን በማሳደግ ክንዷ ሳይጠነክር ሁለተኛ ልጃችንን ወለደች ምጧ ቀኑ ቀድሞ ይሁን ወይ ተራራው አድክሟት ተጎድታ አይታወቅም ግን ታመመች።
ልክ ልጃችን እንደተወለደች አሷ አልጋ ላይ ተዘረረች በደቂቃዎች ውስጥ ሰውነቷ እንዳለ ተነረተ በቃ ሞተች ተብሎ ሊጥ ተቦካ ሰወ ተሰበሰበ ህፃኗ ታለቅሳለች እንዲሁ እስክትሞት እየተባለ ከንፈሯ ላይ ቅቤ ያደርጉላት በገጠር እናት ጡቷ ካልፈነዳ ለህፃኗ ቅቤ እየተደረገ በህይወት እንድትቆይ ትደረጋለች ...
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል1️⃣1️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet💔
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔