♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 34...🌹
.
.
"አመረርክ እንዴ ትናንት እኮ እኔን ለማሳቅ ብለህ እኔን አሸናፊ አንተን ተሸናፊ አድርገህ እንደቀለድክ እንጂ ከልብህ እንዳልሆነ ነበር ያሰብኩት፣ ኤፊዬ ሙት እኔ ትናንት በነበረው ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ምንም ያጎደልክብኝ ነገር የለም ተመችቶኛል"
"ገሎ ማንሳት፣ ጠብሶ ማሸት የሚባል ነገር ታውቂያለሽ"
"ገሎ ማንሳት አላውቅም ጠብሶ ማሸት ግን ለበቆሎም ሊሆን ይችላል ለሰውም ይሆናል ያው ጠብሰክ እያሸኸኝ አይደል እንዴ ኤፊዬ?"
"ካካካ አንቺ ነሻ ገለሽ የምታነሽው ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ብለሽ ከገደለሽኝ በሁዋላ አይደለም በሽንገላ በክሪክ አልነሳም።
ያለው አማራጭ ወንድነቴን ማሳየትና ማስመከር ብቻ ነው"
"ክሪክ ምንድን ነው ኤፊ ?"
"የተሽከርካሪ ጎማ ለመቀየር ለሌላም ጉዳይ ብቻ መኪናው ከፍ የምናደርግበት ነዋ " አልኳት በቃ ወሬህ ዞሮ ዞሮ ከትራፊክ ህግና ከተሽከርካሪ አይወጣም አይደል እንዳትለኝ ውስጥ ውስጡን እየተሳቀቅኩ።
"እኔ እንግዲህ ወንድነትህን አይቼዋለሁ ሌላ የምታሳየኝ አዲስ ነገር አለ?"
'አዎ አለ"
"እና አሳየኛ "
"አሁን አይደለም ስንመለስ " ብዬ እጇን ይዤ በመጎተት ከአልጋው ላይ አነሳኋትና ይዣት ወጣሁ።
እየሄድን መንገድ ላይም "አይ ኤፊ" እያለችና ዝም ብላ እያየችኝ ትስቃለች።
"ለምንድን ነው የምትስቂው ቃልዬ?"
" ኤፊዬ ግልፅነትህ በጣም ደስስስስስ እንደሚለኝ ታውቃለህ ግን?"
"አላውቅም ነበር ይሄው አሁን ነገርሽኝ። እና ግልፅነቴ ብቻ ነው ደስ የሚልሽ?"
"ሌላውን ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ"
"በጣም የሚገርመኝ ባህሪሽ የሆነ ነገር ለማውራት ቀጠሮ የምትይዥው ነገር ነው"
"ሁሉም ነገር እኮ ባንድ ግዜ አይወራም ኤፍዬ"አለችኝ ወገቤን አቀፍ አድርጋ ወደሷ በመጎተት በዳሌዋ ገጨት እያደረገችኝ።
ተንገዳግጄ ልወድቅ ነበር ። የሴት ቀጭን የለውም አለች አያቴ። ቃልዬ በርግጥ የሰማዩ ንጉስ ክብሩ ይስፋና ከወገቧ ቀጠን ከዳሌዋ ሰፋ አድርጎ ስላስዋባት በዛ ዳሌ ተገጭቼ ብንገዳገድ በኔ አይፈረድም። ቃልዬ
" ና በደንብ ልግጭህና ውደቃ በቃ ነጋ ሳረግህ ተንገዳገድክኮ መውደቅ አምሮህ ነው" እያለች ድጋሚ ልገጨኝ ስትሞክር አንገቷን አቅፌ ተረፍኩ።
ለጥሬ ስጋ እስከዚህም ብትሆንም አንተ የበላኸውን ነው የምበላው ሌላ ምግብ አላዝም ብላ አብራኝ በላች።
በልተን እንደጨረስን እዛው በስሱ ማወራረጃውን እየተጎነጨን ቆየን። እንደትናንትናው ከዚህ በላይ እንዳትጠጣ በቃህ አላለችኝም። እኔም በነፃነት በላይ በላይ እልፈው ጀመር።
ነገር ግን ቃልዬም እንደስከዛሬው ከሁለት በላይ አልጠጣም የምትለውን ረስታው ይሁን ትታው ደገም ደገም ስታደርግ ኦኦ ሁለታችንም ከሰከርን ማን ማንን ሊጠብቅ ነው ? አልኩና የኔን መጠጣት ገታ ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ጭራሽ " ጠጣ እንጂ ኤፊዬ" ስትለኝ እየጠጣሁ ነው ጠጪ እያልኩ ከንፈሬን እያረጠብኩ መመለስ ጀመርኩ።
እንዲሁም በትንሽ በትልቁ ሳቅ ሳቅ የሚላት ቃልዬ ምንም ሳናወራ ሁላ ዝም ብላ እያየችኝ መሳቅ ጀመረች።
ይውጣላት አልኩና ከምግቤቱ ይዣት በመውጣት ቅልጥ ወዳለ ጭፈራቤት ይዣት ሄድኩ።
እንደገባን ጭፈራውን ታቀልጠው ጀመር ። ጭፈራው ላይም የዋዛ አልነበረችም። እኔ ደከመኝ ብዬ ጥግ ጥግ ላይ ወዳሉ
"ባለጌ ወንበሮች" ሄጄ ለመቀመጥ ስሞክር እየጎተተች ታስነሳኛለች።
ያልጨፈረችበት የዘፈን አይነት የለም። ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ•••
"ቃልዬ ያ የውዝዋዜ ዳኛው ትናንት ያደነቀሽ የእውነት መሰለሽ እንዴ? አቀለጥሽው እኮ" ስላት
ሙዚቃውን ያስናቀም ያሳቀቀም ሳቅ ሳቀች ። መቀመጥ የሚባል ነገር የማይሞከር ሆነ ።
"ተነቅቶብሻል ባክሽ ወይ በዳንስ አድክመሽ ልታስተኝኝ አስበሻል ወይ ትናንት የጀመርሽውን ወገብ ሰበራ በዳንስ ልትጨርሽው ፈልገሻል " አልኳት።
ቃልዬ እኔ ባወራሁ ቁጥር ስትስቅ በተለይ ቀዝቀዝ ያለ ዘፈን ሲሆን የሷ ሳቅ ጎልቶ እየወጣ በቤቱ ያሉ የተወሰኑ ሰዎችን ትኩረት መሳባችንን እንዳስተዋልኩ ማውራቴን ተውኩት።
ቃልዬ ግን እኔ ማውራት ባቆምም ከዚህ ቀደም ከወር እና ከሁለት ወር በፊት ያወራነውን ሁሉ እያነሳች በትዝታ መሳቅ ጀመረች።
ከምሽቱ አምስት ሰአት አለፍ እንዳለ ሌላ ቦታ የተሟሟቁና የሰከሩ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ በብዛት መግባት ጀመሩ። ሰው እየበዛ ቤቱም እየሞላ መጣ። ይዣት ለመውጣት ብወስንም ቃልዬን ከዛ ቤት ይዞ መውጣት ቀላል ስራ አልነበረም።
በብዙ ውትወታ እና ልመናም እሺ ብላ አልወጣ አለችኝ። በግድ ተሸክሜም ቢሆን ይዣት መውጣት ነበረብኝ።
"እንግባ ይበቃናል ቃልዬ ነገ ጥዋት አራት ሰአት ክላስ አለሽ እኮ በጥዋት ስለምንሄድ ገብተን መተኛት አለብን"
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 35 ይለቀቃል🌹
Like አርጉ እኛም ቶሎ እንልቀቀው 🙏
https://vm.tiktok.com/ZMh9xdBnV/