❤️ተማሪዋ ❤️
.
🌹…………ክፍል 42 ……….. 🌹
.
በአይነ ህሊናዬ ታየኝ ፣ ከዚህ ጭለማ በላይ የኔ ሂወት ሲጨልም ታየኝ እውን የሆነ ያህል ደንግጬ •••
"ኧረ ቃልዬ!" አልኩ ሳይታወቀኝ በደመነፍስ ።
"ምንድን ነው የምትለኝ ኤፍዬ ግባና ንዳ እንጂ ቀስ እያልክ ንዳ ማለት ይህን ያህል ያናድዳል?" ስትለኝ ከሄድኩበት የሀሳብ አለም ባንኜ።
"ምናልኩሽ?" አልኳት ደንግጬ።
ግባና ንዳ እራስሽ ንጂው አልነዳም እየተባባልን ስንጨቃጨቅ አንድ ስካር ጢንቢራውን ያጠናገረው ሰካራም ከየት እንደመጣ እንጃ ጎንበስ ቀና እያለ መጣና ድንገት ባጃጇ ውስጥ ጥልቅ አለ።
"ወይኔ ኤፍዬ ድረስ !!" ብላ ጮኸች ቃልዬ ደንግጣ። ዛኪዬ ድረስ አለማለቷም ተመስገን ነው።
"እሰይ እኔን እብድ ስትይ የለየለት መጣልሽ " አልኩ በውስጤ ሰውየውን እያየሁት።
"የየየየየ የምን ኤፍዬ ነው ? የኔ ስም ገረመው ነው ቆንጅት ኤፍዬ ትያለሽ እንዴ ገረመውብለሽ ጥሪኝ ህቅ•••እስቲ ገረመው በይ?" አላት ። ከመስከሩ የተነሳ ቁጭብ ሎም መሸከም ያቃተው ጭንቅላቱ ብቻውን ይንገዳገዳል።
"አሁን ትወርዳለህ አትወርድም ገረመው እኔ ሰው አልጭንም " አልኩት።
"ምናልክ ሹፌሩ ሰው አልጭንም እና ኩንታል ልትጭን ነው እንዴ የቆምከው በባጃጅ ኩንታል ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው የሚለውን ዘፈን ጨርሰህ ዝፈነው እሺ ያኔ አቅምህን ታውቃለህ። እኔ እዚህ ጨለማ ውስጥ ባጃጅ ጥበቃ ስንት ሰአት እንደቆምኩ ታውቃለህ ሰው አልጭንም ይላል እንዴ እና ይቺ ከጎኔ የተቀመጠችው ኩንታል ነች እንዴ ? እሄው በደንብ አየኃት አይደለችም " እያለ ወደ ፉቷ ጠጋ ብሎ ሲመለከታት ቃልዬ ሽምቅቅ ብላ ባጇጇ ላይ ተጣበቀች።
"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ ።
አይገርምሽም ታምሪያለሽ አይገልፅሽም።
አለች እንጂ የኔ ሚስት በጨለማ አትታይ በፀሀይ አትታይ ምኗን አይቼ እንዳገባሁዋት ግራ ገብቶኛል።
ወድጄ መሰለሽ የምጠጣው ምናልባት ምኗን አይቼ እንደወደድኳት ስጠጣ ቢገለጥልኝ ብዬኮነው።
ሴት መሰለችሽ ሰላቢ በያት እሄው እሷን ስከታተል ስንት አመት ሆነኝ እሳን እጅ ከፍንጅ እይዛለሁ ብዬ ስከተላት ስንት ቦታ ፈንጅ ረገጥኩ መሰለሽ።
እኔና ሚስቴኮ አብረን እየኖርን የተፋቷን ብቸኛ ባለትዳሮች ነን ።
አብረን እየኖርን አብረን እያደርን ነው አሁንም ድረስ ግን ተፋተናል።
ብዙ ወሬ ሰማሁ ወሬ ሰምቼ ከምወስን በገዛ አይኔ አይቼ ቢለያኝ ይሻላል ብዬ ምንም እንዳልሰማ ባል ሆኜ በድብቅ እከታተላት ጀመር እኔ እሷን ተደብቄ ልከታተል እሷው ተደብቃ እኔን ትከታተለኝ እስከሚምታታብኝ ድረስ እንኳንስ በማታ በቀንም ላገኛት አልቻልኩም ቀን ከስራ እቤት መጥቼ የለሽም የት ነበርሽ ስላት አጠገብህ ትለኛለች ። በቃ ሁሌ ያለሁበት ቦታ ሁሉ ያለች ይመስለኛል ወድጄ መሰለሽ ድምፄን ቀንሼ የማወራው የምትሰማኝ እየመሰለኝ እኮ ነው ።
" ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ!" አልኩት በንዴት!።
"ስማ ሹፌሩ አንተም ወንድ ነህ ነገ ማግባትህ መውለድህ አይቀርም የጀመርኩትን ወሬ ልጨርስበት አታቋርጠኝ ምን ይመስላል በሚስቴ ሞት።
ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን እኮ ነኝ እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ሲል ቃልዬ ሳቀች። አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው የምትመስይው !
ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !" አላት ። ተበሳጨሁ።
"ስማ ሰውዬ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ የሚደገመው አሁን የምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።
"ጠጅ አልጠጣሁም አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? እኔ ጠጅ አልጠጣሁም አረቄ ነው ነው የጠጣሀት ዝም ብለህ በመላ ምት ጠጅ ትላለህ እንዴ?
ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ
"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ። አንቄ ላወርደው ገና ያዝ ሳደርገው•••
"ኤፍዬ ኤፍዬ ለኔ ስትል ስሞትልህ ኤፍዬ ልቀቀው እራሱ ይወርዳል!" አለች ቃል ግብግብ ብላ።
" አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እራሱ ድብን ይበል አንቺ ለምን ብለሽ ነው የምትሞችው? እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር! ምኑ ዳይኖሰር ነገር ነው በሚስቴ ሞት ተከመረብኝ እኮ"
"እሺ አሁን ትወርዳለህ አትወርድም?" አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ..
"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
"ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"
"ለሷ!"
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው አሃሃሃ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !
ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••
ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ልጠጣ እየሄድኩ ነው ።
ያቺ ግሮሰሪ አትዘጋም። ሙች እውነቴን ነው ያቺ ግሮሰሪ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም
ወደዛ ነው እምሄደው. ዝግ ከሆነች ወደ ከተማ እመለሰላሁ"ሲላት
"በናትህ ኤፍዬ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለችኝ።
ብስጭት እንዳልኩ ባጃጇን አስነስቼ ከነፍኩ።
"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ
እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ እሺ በይኝ ?"
"ምን ?"
"አንዴ ብቻ የቅድሟን ሳቅ ድገሚልኝ " አላት ቃልዬስ ሳቂልኝ የሚላት አግኝታ ነው ለቀቀችው። ደስ አለው።
በናትሽ ይህን ሹፌር እናቃጥለው አሁንም ድገሚው ሲላት እኔ እራሴ ሳልፈልግ ሳቄ መጣ።
"ግን ምን ሆነሽ ነው ከዚህ ባለ አስፈሪ ፊት ሹፌር ጋር በጭለማ ብቻሽን የምትሄጂው ?" ሲላት አልቻልኩም። ሳቄን ለቀቅኩት።
"ግሮሰሪዋ ዝግ ነች ምን ይሻልሀል?"
" ዉ ይ ዝግ ነው እንደውም ባንተ ባጃጅ መሄድ አልፈልግን እዛው የጫንከኝ ቦታ መልሰኝ "
"ምን ?" አልኩት እያቆምኩ።
"ኪኪኪኪ ኤፍዬ በናትህ በቃ አድርሰኸኝ ስትመለስ ጣል አድርገው"
"አንቺ ደሞ አበዛሽው!"
ቃልዬን ግቢ በር ላይ አድርሻት እንደወረደች ።
"ኬት ጠብ አደረካት ይቺን የመሰለች ልጅ እባክህ አንባሳ ነህ አባቴ ይሙት ኮራሁብህ ጀግና " ሲለኝ አሁን ገላጋይ የለም ብሎ እያባበለኝ መሆኑ ገባኝና ፈገግ አልኩ።
https://vm.tiktok.com/ZMh7Q9na4/