❤️ ተማሪዋ ❤️
.
.
🌹…… ክፍል 40……..🌹
ኢትዮጲያ ውስጥ የትም ቦታ የትኛዋም ሴት ከአክስቷ ልጅ ጋር እንደዚህ የምትደንስ አይመስለኝም ።ለቃልዬ ባክስት ልጅ እና በኔ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ። ጭፈራ ቤቱ ጥግ ላይ እንደግርግዳ ቋሚ ተለጥፌ እነቃልዬን እያየሁ ስንጨረጨር ስልኬ ጮኸች። ከጭፈራ ቤቱ እየወጣሁ ስልኬን ስመለከታት ያ መልክት የተላከበት የማይታወቅ ስልክ ነው። አነሳሁት።ሄሎ ስል የሚያስጠላ የሴት ልጅ ሳቅ። ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አላብድ ያልኳቸው ሰዎች በዙርያዬ አሉ እንዴ ? ደሞ ይሄንን ሳቅ አውቀዋለሁ። መቼ እና የት እንደሆነ ባላውቅም ይህንን ሳቅ የሆነ ቦታ አውቀዋለሁ። ለማስታወስ ሞከርኩ። የመክሊት ሳቅ ነው ። አዎ እራሷ ነች ። በገንኩ ። እንደእብድ አደረገኝ ። አይ ኪያ የቶማስ ሳያንሰው ለመክሊትም አሳልፎ ሰጠኝ ። ደግማ ከሳቀች ለማረጋገጥ ደወልኩ አይነሳም ።
ይሄ ልጅማ ከኔ ጋር የከረረ ፀብ ፈልጓል ፣ጭራሽ ለመክሊት ፣ ወይኔ ኤፍሬም እኔና ኪያ የሚለይልን ዛሬ ነው።
ወደ ጭፈራ ቤቱ መመለስ ይኑርብኝ ወደኪያ መሄድ መወሰን አቅቶኝ ጭለማው ላይ እንዳፈጠጥኩ ደቂቃዎች አለፉ። ኪያን ምን እንደበደልኩት ለማስታወስ ሞከርኩ። ምንም ትዝ አይለኝም ። አንድ ሰፈር ተወልደን አንድ ላይ ተምረን እንደየፍላጎታችን በምንፈልገው የስራ ዘርፍ ተሰማርተን ሂወትን ለማሸነፍ መፍጨርጨር እስከጀመርንበት ድረስ የከረረ ፀብ እንኳን ተጣልተን አናውቅም እንደማንኛውም ያንድ ሰፈር ልጆች በተለያየ ግዜ በተለያየ ጉዳይ ከመከራገር ከመበሻሸቅ፣ከመኮራረፍ እና መልሶ አስታራቂ መሀላችን ሳይገባ በጫወታ ሞቅታ ከመታረቅ ያለፈ ክፉ ነገር በመሀላችን ተፈጥሮ አያውቅም።
ቢያውቅም የዛሬን ያህል በኪያ የተከፋሁበት ቀን የለም የማትነካውን እየነካብኝ ነው ኪያ በማይመጣው እየመጣብኝ ነቅ ኪያ ማንንም ልታገስ በማልችልበት ደካማ ጎኔ እየመጣብኝ ነው። ኪያ ሁሉ ነገሬ ከራሴም በላይ በማፈቅራት በቃልዬ ከመጣብኝ አብሮ ማደግ፣ አብሮ መማር፣ ጓደኝነት፣ወንድምነ ሁሉ ለኔ ቦታ አይኖራቸውም ምክንያቱም ቃልዬ እንኳንስ ከኪያ ከራሴም በላይ አፈቅራታለሁ። እሷ ካጣሁ እኔ እራሴ የታለሁና ቃልዬ እኮ ነች እጅ ላይ በሚጠለቅ ቀለበት ሳይሆን በፍቅሯ ልቤ ላይ ቃልኪዳን ያሰረች የኔ ፍቅር ቃልኪዳን ነች ድጋሚ ወደ ጭፈራ ቤቱ ብገባና ቃልዬን በዛ መልኩ ከልጁ ገር ስትጨፍር ባያት ያስችለኝ ይሆን በጭራሽ ።
መሀላቸው ገብቼ ቃልዬን ከዛኪ ላይ መንጭቄ እየጎተትኳት ስወጣና ማንው ደሞ ይሄ ጥጋበኛ እያለ ስከተለኝ በደምፍላት ዞሬ አፍንጫውን ብዬ ደሙን ሳንዥቀዥቀው ታየኝ። ከዛ ቡሀላስ በኔና በቃልዬ ማሀል ምን ይፈጠራል?
ሁሉም ነገር ድብልቅልቁ ሲወጣ ታየኝ። ስልኳ ላይ ሞከርኩ አሁንም ጥሪ አይቀበልም። የማደርግ የምሆነው ነገር ግራ ገባኝ።
የቃልዬ አደናነስ ፉቴ ላይ ይውለበለባል ተቃጠልኩ። በኪያ ተንኮልና ወሬ ቃልዬ ላይ መናደድ የሱን ሀሳብ ማሳካት መስሎ ቢታየኝም አለመናደድ አልቻልኩም። እኔኮ የቃልዬን ገላ አይደለም የቃልዬን ቀሚስ ንፋስ እንኳን ሲገልበው እቀናለሁ። ታድያ እንደዛ ተጠብቃበት ስትጨፍር እያየኃት እንዴት ብዬ ነው አለመናደድ የምችለው።
ስለኔና ስለቃልዬ ለኪያ ያወራሁባትን ቀን ያቺን አርብ ምሽት ክፉኛ ጠላኋት ፣ከአያቴም ከእናቴም የሰማሁትን እርግማኖች ሁሉ ረገምኳት።
ግን ቀኗ ምን ታድርገኝ ። በግድ አፌን ፈልቅቃ አላስወራችኝ። እራሴው ነኝ የግል ሚስጥሬን ሳልጠየቅ የለፈለፍኩት ሊያውም ለኪያ ። እሄ የተረገመ ልጅ አሁን የት ነው ያለው? በሱ ወሬ ከቃልዬ ጋር ሳይሆን ከሱ ጋር እንደምጣላ ከዚህ ቀደም ነግሬዋለሁ ። ዛሬ በተግባር አሳየዋለሁ እያልኩ ባጃጄን አስነስቼ ከነፍኩ።
እንዴት እና በምን ፍጥነት እቤት እንደደረስኩ አላውቅም። ኪያ እቤት ውስጥ የለም። ገራዡ ዝግ ነው። ገኒ ጋርም ፈለኩት እዛም የለም።
ጭለማ ውስጥ ባጃጄን ተደግፌ እንደቆምኩ እንድ ጥያቄ ውልብ አለብኝ። አዋ እንዴት ግን ቅድም ልክ ጭፈራ ቤቱ በር ላይ ስደርስ ጠብቀው "አትወጣም" ብለው መልክት ላኩልኝ? ያ ማለት እኮ ስገባ እያዩኝ ነበር ማለት ነው። በቃ ኪያ ከመክሊት ጋር እዛው ጭፈራ ቤት አልያም እዛው አከባቢ ነው ያለው። እሄን ሁሉ ነገር የሚያደርገው መክሉትን ለማስደሰት እንደሆነ ግልፅ ነው ። እሱ መክሊትን ለማስደሰት ቶማስን ከዛኪ ጋር እንዲተዋወቅና የት ምሳ እንደሚበሉ የት እንደሚያመሹ መረጃ እንዲያቀብለው አደረገ። ከዚህ የከፋ ነገር አለመሸረቡንስ ማን ያውቃል እስቲ እንተያያለና እንግዲህ ። ድጋሚ ወደ ጭፈራ ቤቱ ገሰገስኩ።
እነቃልዬ ጭፈራ ቤቱ ውስጥ የሉም ሄደዋል። ኪያንም በዛው ጭፈራቤትና በአከባቢው ባሉ ሆቴሎች ፈልጌ አጣሁት። ቃልዬ ስልክ ላይ ሞከርኩ አሁንም ዝግ ነው። ወደቤት ስመለስ ኪያ አልገባም። ጭራሽ ሳይመጣ አደረ። እንቅልፍ ባይኔ ዝር ሳይል አስቀያሚና ረጅሙ ለሊት እንደምንም ነጋ። እንደተነሳሁ ቀጥታ ወደ ገራዥ አመራሁ። ከኪያ ጋር ክፉኛ ተጣላን። የገራዡ ሰራተኞች መሀላችን ገብተው ባይገላግሉን ከሱ ጋር ከመነጋገር መደባደቡ ይሻለኝ ነበር።
በዛ ተምዘግዛጊ ምላሱ ከአስር ግዜ በላይ •••" ኤፍሬም ይልቅ አይንህን ግለጥ !" ይለኛል። ጭፍኜ ስሄድ የት እንዳየኝ እሱ ነው እሚያውቀው ስለኔ እንደማይመለከተው ደጋግሜ ስነግረው እየደጋገመ
"ኤፍሬም ይልቅ አይንህን ግለጥ ከኔ ጋር በመጣላት የምታተርፈው ነገር የለም ትርፉ መቀያየም ነው ። አንተን እና ቃልኪዳንን የማውቃችሁ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ? ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ የሚማረው የድሬ ዳዋ ልጅስ ቶማስ ብቻ ነው እንዴ? ብዙ ተድሬ ልጆች እኮ እዛ ይማራሉ። እሷን ስታደርስ እና ስትመልስ የሚያይህ ብዙ ነው ። ከኔ ላይ አይንህን አንሳና ዙርያህን ተመልከት ፣ እውነቱን በመሸሽ ወይም ከኔ ጋር በመጣላት ፍቅርህን ማትረፍ የምትችል መሰለህ እንዴ? ና ምታኝ ምታኝ ችግር የለውም ፣ እኔን በመምታት ንዴትህ የሚወጣልህ፣ ቃል ኪዳንም ታማኝ የምትሆንልህ ከመሰለህ ምታኝና ደስ ይበልህ!" ሲለኝ እራሴን አቅቶኝ ዘልዬ አንገቱን አነቅኩት። ምታኝ ምታኝ ከማለት ውጪ ለመሰንዘር አልሞከረም ። የገራዥ ልጄች እንዳላቀቁን ምንም ማለት ምንም መናገር አልቻልኩም ወወቤት ገብቼ ተኛሁ።
አመሻሹ ላይ እህቴ ጋር ሄጄ እራት በልቼ ስመለስ ኪያ የራሱን ልብስና መኝታ ይዞ አብረን ከምኖርበት ቤት ለቋል።
እራስ ምታት እያጣደፈኝ ነው የዋለው ። ማታም አለቀቀኝም። ለቃልዬ አልወልኩም እሷም አልደወለችም ።
በሁለተኛው ቀን አመሻሹ ላይ ደወልኩላት። እንዳነሳችው ገና ለምን ስልክሽን ዘጋሽ ብዬ ሳልጠይቃት ቀድማ ከትናንት ወድያ ቻርጅ ዘግቶባት እንደነበርና ቻርጅ ስታደርገው ብዙ ግዜ መደወሌን መልክት እንደደረሳት መደወል ፈርታ እስክደውል እየጠበቀችኝ እንደነበር ፣ እንደናፈቅኳትና አሁን ለአጭር ሰአትም ቢሆን ልታገኘኝ እንደምትፈልግ፣ ከቻልኩ ወደ ግቢ ሄጄ እንድወስዳት ነገረችኝ ።
መጣሁ እየወጣሽ ጠብቂኝ ከማለት ውጪ ምንም አላልኳትም።
ግቢ ስደርስ ቆማ እየጠበቀችኝ ነበር። ምንም ሳልናገር ቀጥታ ከአንድ ቀን በፊት ከዛኪ ጋር ወደጨፈረችበት ጭፈራ ቤት ይዣት ሄድኩ።
በሩ ላይ ስንደርስ "እንዴ ኤፍዬ ዛሬ እዚህ ነው የምናመሸው?" አለችኝ።
"አዎ" ብያት ገብተን ትንሽ እንደቆየን
"ምነው ቃል ቤቱ አልተመቸሽም እንዴ ? ይሄን ቤት ከዚህ በፊት ታውቂዋለሽ?"
.
ከ150 ላይክ በኃላ ክፍል 41 ይለቀቃል 🌹
https://t.me/saloda_trading