♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 4..🥀
.
.
፨ፅናት ከፍዘቷ ስትነቃ ጩከቷን አቀለጠችው ፤አለቀሰች ውስጧ በሀያሉ ታመመ። በአንድ ሲኮንዶች የተለያዩ አስቀያሚ ስሜቶችን ውስጧ አስተናገደ "አንቺም ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው በፀሎቴ፤ እህቴ አንቺም አንቺም አንቺም እንደ አባባ እና እማማ ጥለሽኝ ልትሄጂ ነው?፤ አይ አይሆንም እባክሽ" የሚሉ ቃላቶችን ከሲቃ ጋር አጓረፈቻቸው።
፨ የበፀሎት የጭንቅላት ደምም ለጉድ ጎረፈ አወይ ስቃይ! አወይ ሀዘን! በቃላት የማይገለፅ ሀዘን ፣የውስጥ ህመም ፣እረ ስንቱን በለጋ እድሜዋ አስተናገደች። አንፑላንስ መጣ፤ አንፑላንስ ጮከ ፤በፀሎትንን ይዘዋት በቃሪዛ ወደ ህክምና ጣቢያ ከነፉ ፅናትም እንድትገባ ባይፈቅዱላትም ታግላና አልቅሳ እንደምንም ገባች።
፨ በስተመጨረሻ ሆስፒታል ደረሱ ያኔ ፅናት ከመኪና ወረዳ የድረሱልኝ ጩከቷን ከ አንፖላንሱ ጋረ አቀለጠችው። ሆስፔታሉ በፅናት እና በአንፖላንሱ ድምፅ ታጀበ። ተጨማሪ ነረሶች መተው በፀሎትን ሆስፒታል አስገቧት ፅናት ውስጧ ተሸበረ ፈራች ውይይይ በቃ በጣም ጨነቃት። ምስኪኗ ትንሽየዋ ፅናት እራስዋን ሳተች።
፨ የነቃችው በነጋታው ጠዋት 1:30 ላይ ነበር። አይኗ ደብዘዝዝ አለባት ከዛም እይታዋ ተስተካከለ። 1:30 አለች። ስአቱን ያወቀችው ባለችበት ክፍል ውስጥ በተሰቀለ የግድግዳ ሰአት ነው።ስትነቃ መጀመሪያ የጠራችው የእህቷን ስም ነበር። "እህቴ በፂዬዬ፤ እህቴ በፀሎቴ " ሲቃ በተሞላበት እና እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ድምፅ ከዛ እንባ በድንቡሽብሽ እኛ በጥቂቱ ውረጭ በመታው ፊቷ ወረደ።
፨ያለችበት ክፍል በድንገት ተከፍቶ አንድ ዶክተር እና ፖሊስ እህቷን ከገፈተራት ልጅ አባት ጋረ ገቡ። ፅናት ሰውየውን ስታየው ፊቷ ተቀያየረ እንባ እና ንዴት ተናነቃት አትችልም እንጂ ተነስታ ብታፈራረጠው እና የምትወዳትን እህቷን አስነስታ የገፈተራትን ልጅ እስከ አባቱ ከዛ ፎቅ ወረውራ ብትገላግላቸው ደስታዋ ነው። ፅናት የወረዋሪው ልጅ አባት ላይ አፈጠጠች። ፖሊሱ ወደ ፅናት ተጠግቶ የተፈጠረውን ነገር ለመናገር አሁን ዶክተሩ መልካም ጤንነት ላይ ናት ስላለ ቃልሽን ትስጫለሽ።" አላት።
፨ ፅናት አሁንም አይኗን ከ ወረዋሪው ወላጅ ላይ አልነቀለችም የፓሊሱን ንግግረ ስምታ ይሆን? ማንም አያውቅም አሁን አይኖን ዞርም ሳታረግ "ዶክተር እህቴ እንዴት ናት?" አለች። ዶክተሩ ፅናት የወረዋሪውን አባትን እያየች እሱን መጠየቋ ግራ ቢያጋባውም "አታስቢ ደና ናት" አላት። ከዛም የገፍታሪው ልጅ አባት ሹክክ ብሎ ከ ክፍሉ ወጣ።
፨ዶክተሩ በፅናት ፊት ላይ የሚያየው እልህ እጅግ አስገረመው አስደነገጠውም ህፃንነቷን አይቶ ንግግሯን እና ሁኔታዋን ሲያይ ገረመው።ፓሊሉ ፅናት እንድትነሳ ክንዷን በመያዝ "ቀስ ብለሽ ተነሺና ወደ ፓሊስ ጣቢያ እንሂድ" አላት። ዶክተሩ ፅናትን ሲያያት ሁኔታዋ ጥሩ ስላልነበረ "እዚህ መሆን አይችልም?" አለ። ፅናት ክንድ ላይ ያረፈውም የፓሊሱን እጅ ያዝ አረጎ
ፖሊሱም አንዴ ፅናትን አንዴ ዶክተሩን እያየ እሺ ጥሩ ብሎ እጁን ከፅናት ክንድ ላይ አንስቷ ወደ ውጪ ወጣ። ከቆይታ በኋላ ፖሊሱ ከመርማሪው ጋራ መጣ።
፨መግቢያ በሩ ላይ ያለውን ወንበር ይዞ ፅናት ከተኛችበት አልጋ አጠገብ ተቀመጠ። ዋና መረማሪ ፖሊሱ የፅናትን ሆዷ ላይ ያጣመረችውን እጅ አንስቶ በእጁ ያዘው ፈገግ ለማለት እየሞከረ "እንደተጎዳሽ ይገባኛል ፤ስለ እዚህ ነገር አውርቼ ባረብሽሽም ምርጫዬ ነበር ግን በተቻለሽ አቅም የምጠይቅሽን ሁሉ መልሽልኝ አላት። እጅ እጇን እያየ ፅናት አገጯን በመነቅነት እሺታዋን ገለፀችለት።
፨ መረማሪው የድምፅ መቅጆዎን ካመቻቸ በኋላ ፅናትን አየት አረጎ የድምፅ መቅጃውን ከማብራቴ በፊት ሁሉም እንዲወጡልሽ ከፈለግሽ ላስወጣልሽ እችላለው አላት። ፅናም "አይ አይሆንም በተለይ የአላዛር አባት እንዲኖረ እፍልጋለው ልጁ ያረገውን ነገር መስማት አለበት" አለች።መረማሪ ፓሊሱ ወደ ፖሊሱ ዞሮ ሽቅብ እያየው "የአላዛረን አባት አስገባው" ብሎ ለፓሊሱ ትዛዝ አስተላለፈ ። ፓሊሱም "እሺ አለቃ እንዳልክ ይሁን "ብሎ ሊጠራው ከክፍሉ ወጣ።
፨ ፅናት "እሱ ሳይመጣ ምንም ማለት አልችልም አልፈልግምም" አለች። ዋና መረማሪ ፓሊሱም "እሺ ጥሩ እንዳልሽ ይሆናል" አለ። ከዛም ዝም ተባባሉ ፓሊሱ ግን ፅናትን በግረምት እያያት ነበረ። እሷም ጨረፍ አረጋ እያየችው ቆየች። ዶክተሩ በአትኩሮት ሁኔታውን ማየት ተያይዞታል ድንገት ፓሊሱ ከአፉ የሆነ ቃል ወጣ "ውብ ነሽ" የሚል።
፨ ፅናት ደነገጠች በእረግጥ ይህ ቃል ለእሷ አዲስ አደለም ያያት ሁሉ የሚላት ነገር ነው። በድንገት በሩ ተከፈቶ የአላዛረ አባት እና ፓሊሱ መጡ። መረማሪው "እሺ አሁን መቀጠል እንችላለን የተፈጠረውን ሁሉ ንገሬኝ ዝግጁ ነሽ አደል? " አላት። ፅናት የአላዛርን አባት በእልህ እያየች "አዎ በሚገባ" አለች።
፨ይህን ስትል አይኗ በሚጥሚጣ የተለወሰ እረጎ መስሎ ነበር። ልክ እንደ ውስጧ ደፍረሶ ነበር። መርማሪው የድምፅ መቅጃውን አበራው። ፅናት መናገር ጀመረች። "ትናት ትናት ትናንትትትት እህቴ ደና ነበረች።እኔም እንደዛው ሰረተፈኬት ተስቷኝ ከትምህርት ቤቱ አንደኛ እንደወጣው ሳውቅ ለእህቴ ላሳያት ፍለኩ በጣምምም ፈለኩ የመማሪያ ክፍላችን ፎቅ ስር ሆኔ ጠበኳት እስክትመጣ በጣም ጎጉቼ ነበረ። በጣም በጣም በጣም በመጨረሻ መጣች። እህቴ መጣችልኝ" አለችና ፈገግ አለች።
፨ ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሁሉ እያለቀሱ እና በፅናት የቃላት አጠቃቀም ተገረመው ነበረ። ፅናት ስታወራ አፉዋን የድምፅ መቅጃው ላይ አይኗን ደሞ የአላዛር አባት ላይ አድረጋ ነበረ። ለተወሰነ ሲኮንድ ፀጥ ብላ በድጋሜ ወሬዋን ቀጠለች። "ከዛማ እህቴ ስትመጣ የምስራቹን ነግሬያት ገና ፍገግ እንኳን ለማለት ሳይፈቅድላት አላዛር! አላዛር! አላዛር! የኔን እህት፣ የኔን ፋና፣ የእኔን ሁሉ ነገረ ከ 2ተኛ ፎቅ ወረወራት"።ብላ ተንሰቀሰቀች።
፨መረማሪው የድምፅ መቅጆውን አቋረጦ ፅናትን ሊያባብላት እጁን ወደ አንገቷ ሲያረገው ፅናት እጁን ይዛ "እንዳታባብለኝ በቃ ሁላችሁም ውጡ" አለች።በቃላቷቾ ክብደት ሁሉም ተገረመዋል። እድሜ ሳይሆን ኑሮ የሰውን ጭንቅላት እንደሚያበስለውም ተረድተዋል። ሁሉም ተከታትለው ክፍሉን ለፅናት ትተውላት ወጡ።
፨ፅናትም ለብቻዋ ክፍልሉ ውስጥ በሀዘን ቁረምት ብላ ቀረች። አይኗን የግድግዶ ሰአቱ ላይ ተከለች የግድግዳ ሰአቱን ወደ ጊዜ ሰአት ቀይራ ከዛም ተነስታ በጣቶቾ አዙራ መቀየረን ተመኘች። ይህን ጊዜ ወይ ወደ ኋላ መልሳ በእህቷ ፍንታ እሷ ለመሆን አልያም ደሞ አሳልፍ እህቷም ደና ሆና መኖርን አለመች። ፅናት ወደ እራስዋ ተመልሳ ፈገግ ብላ "የሞኝ ምኞት ሞኝ ነሽ ፅናት " አለች።
፨ እንዲህ ከእራሷ ጋር የማይሆን ግን ቢሆን የሚያስደስታትን እያሰበች በማሰቧ እየተገረመች እንቅልፍ ጥሏት ሰአታት ነጎዱ።ከእንቅልፏ የነቃችው ዶክተሩ ስለ ጤንነቷ ሊያረጋግጥ ሲመጣ ነበረ። ዶክተሩ "እንዴት ነሽ አሁን" አላት። በውስጧ "ምን እንድመልስለት ጠብቆ ነው?አለችና ለእሱ ግን "ደና ነኝ" አለችው። ዶክተሩ "እሺ ጥሩ" ብሎ ሙቀቷን እየለካት ፅናት ዶክተሩን "ዶክተር" አለችው ልስስስ ባለ አንደበት። "አቤት" አላት እሱም ረጋ ባለ ድምፅ "እህቴን ማየት እፍልጋለው" አለችው። ዶክተሩ አልተቃወማትም።" እሺ ብቻ ነው ያላት"
.
.
ይቀጥላል..
ላይክ ሼር እዳረሱ...