♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
.
🥀..ክፍል 6..🥀
.
.
.
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.
.
.
በደማቁ በእርሳስ በማያምር እና ምንጭርጭሩ በወጣ ፅሁፍ ወረድ ብሎ በተመሳሳይ ፅሁፍ...."ህይወት ብዙ አስመሳይ እና ከሀዲ እንዳሉዋት ግልፅ ነው። ሰው ሳያስመስል የሚኖረው ጥላቻን ፣ ውሸትን ፣ አጭበርባሪነትን፦ ብቻ ነው ጥቂት እውነተኛ ሰዎች አሉ። ግን እነሱን የምናገኛቸው አስመሳዮች ከጎዱን በኋላ ነው እኛም አናምናቸውም ምክንያቱም አምነን ተጓድተናል እውነተኛ ሰዎችም ይከፋሉ ምክንያቱም አስመሳዮች የሆነው ሆኖ ህይወት ቲያትር እኛ ደሞ ቲያትርኛ ነን ትወናችንን ስንጨርስ ደሞዛችንን ለመክፈል እንሄዳለን"። ፅናት ይህንን አንብባ ስትጨረስ ፈራችም ተፅናናችም ደብተሩን ልትገልፀው ስትል ከደረጃ የሚመጣ ኮቴ ሰማች ቋቋቋቋቋ ፅናት የያዘችውን ደብተር በድንጋጤ እና በፍጥነት ከደነችው።
፨የሰማችው የ ሊባኖስን ኮቴ ነበር። በፍጥነት ወደ እሷ ተጠግታ "ይህውልሽ ሻይ አምጥቼልሻለው ጠጪ" አለችና ሻይ የያዘውን እጇን ዘረጋችላት ፅናት እጇን በዝግታ ሰዳ ተቀበለቻት እና የሻዩን ብርጭቆ ጆሮ ይዛ ፈዛ ቀረች። ከመፈዘዟ ያነቃት የሊባኖስ "ጠጪ" የሚል ድምፅ ነበር።
ፅናት "እሺ እሺ እጠጣለው" አለችና አንዴ ጎንጨት አረገች። ሊባኖስ ከለበሰችው ፎጣ ሸሽጋ የያዘችውን ፓስቲ(በዘይት የተጠበሰ ፍርኖ ዱቄት ብስኩት) አውጥታ "እንኪ በሻዩ ብይ" አለቻት። ፅናት ፓስቲ በሻይ በጣምምም የምትወደው ምግብ ነው። እሺ ብላ ተቀብላት ልትበላ ስትል ሊባኖስ ከፓስቲው ጋር የያዘችውን ዶቦ አውጥታ "እሱ ይደረቅብሻል በዳቦ ብይ ብዬ ነው ይህንን እኔ እበላዋለው" ብላ ከእጇ ወሰደችው።
ፅናት ዳቦ ጭራሽ የማትወደው ምግብ ነው በተለይ በሻይማ ጭራሽ አትበላም ሊባኖስን "ይህንን ምግብ ጭራሽ አልወደውም ፓስቲው ይሻለኛል" ማለትን ፈራች። እሺታዋን ገልፃ ከዳቦ በሻይ ጋር ውስጧ መታገል ጀመረ። ግባ አትግባ ፤ውጣ አትውጣ ሊባኖስ ሊባኖስን እያየች የግዷን እሩብ ታክሏን በልታ ከዛ "በቃኝ" አለች። ሆዷ ቢርበውም ዳቦውን መብላት ግን አልቻለችም ፅናት ለመጨረሻ ጊዜ ትናት ጠዋት ከ ትግስት ጋር ትግስት ማታ ማታ እያዞረች ከምትሸጠው የተረፈውን ፓስቲ በሻይ ነው።
ሊባኖስ ፅናትን አየት አድረጋ "ምነው ሚጢጢዋ? አልተመቸሽም እንዴ? አለቻት ። ፅናት በህይወቷ አንዴም ቢሆን አድረጋ ማታውቀው መዋሸትን ነውና በሚንቀጠቀጥ ድምፅ እጆቿን እያፋተገች "እእእ አአአ አዎ ዳቦ አልወድም" አለቻት። ሊባኖስ በግረምት እያየቻት "እና ለምን በላሽ?" አለቻት ቆጠት ብላ ፅናት በድጋሜ መዳፎቿን እያፋተገች በተቆራረጠ ድምፅ "ፈረቼሽ ነው" አለቻት። በሰቀቀን ቀና ብላ እያየቻት" ሊባኖስ የአግራሞት ፊት እያሳየች "ምን?እንዴት? ምኔ ያስፈራል? ምነው እንድትፈሪኝ ያረኩት ነገር አለ?" አለቻት። ፅናት አሁን የሊባኖስ ጥሩነት እየታያት የመጣ ይመስላል ፈገግ ብላ "አይ" አለች። ፍራቻዋ ለቀቅ ሲያረጋት እህቷ ትግስት ትዝ አለቻት። "ወይኔ እህቴ ብላ ብድግ" አለች። ሊባኖስ "አይዞሽ የት ናት ምን ሆና ነው እዚህ የገባችው?" አለቻት።ፅናት እየተርበተበተች የተፈጠረውን ሁሉ አንድም ሳታስቀረ ለሊባኖስ ነገረቻት።
ሊባኖስ ፅናት በነገረቻት የበፀሎት አወዳደቅ አዘነች። ፅናት አሳዘነቻት ውስጧ አቅፈሽ አፅናኛት አቅፈሽ አባብያት አላት። ከዛም ፅናትን በፍጥነት እና በቅልጥፍና ተጠመጠመችባት። ፅናት ደነገጠች ሊባኖስ ስታቅፋት ጠረኗ ይበልጥ ከ አፍንጮዋ ጋር ተገናኝቶ እንደጉድ ይሸታት ጀመር። ፅናት የሊባኖስ ጥሩነት እየታያት ቢመጣም ፍራቻዋ ግን ጭራሽ እየባሰባት መጥቶል። ሊባኖስ በድንገት ፅናትን ከእቅፏ አስወጥታ ትክሻዋን ግጥም አርጋ በሁለት እጆቿ ያዘቻት። ከዛማ ወደ ፅናት ተጠጋች እና አይን አይኗን ታያት ጀመረ። ፅናት አንገቷን ደፋች።
ሊባኖስ "ቀና በይና እኔን ፤ አይን አይኔን እይኝ" አለቻት። ፅናት በሰቀቀን ቀና ብላ ሊባኖስን ማየት ጀመረች። ሊባኖስም ለፅናት "እኔ የምልሽን ሁሉ ትያለሽ ሰማሽኝ" አለቻት ፍጥጥ ብላ ። ፅናት በጉንጯ አዎታዋን ገለፀጭላት። በይ አይንሽን ጨፍኝ ስትላት ፅናት ደንግጣ "እ" አለቻት። "አልሰማሽኝም"? አለቻት። ፅናት "አይ ሰምቼሻለው እሺ ብላ አይኞቿን ከደነቻቸው ከዛ ቃል በቃል እንዲህ አስባለቻት "እኔ ሁሌም የሚመጡብኝን ነገሮች ያለ ፍራቻ ያለ መደናገጥ ጠንክሬ አልፈዋለው። ፈጣሪ መቼም ቢሆን የማልችለውን ፈተና ሊጥለኝ አይሰጠኝም ውስጤ እና እምነቴ ጠንካራ ነው ፈጣሪ የመጥፎ ስሜቶች መሸጋገሪያ ድልድዬ ነው"።
ይንን አስብላት ስታበቃ "እሺ አሁን ውስጥሽን ምን ተሰማው?" አለቻት። ፅናት በረዥሙ ተንፍሳ "ነፃነት ሰላም እና ጥንካሬ" አለቻት። ሊባኖስም "በጣም በሳል ልጅ ነሽ በይ አሁን ተነሽና እህትሽ ስላለችበት የጤና ሁኔታ እንጠይቅ" አለችና የቀኝ እጇን ዘረጋችላት ፅናት አሁን ሊባኖስን ለምዳታለችና ፈገግ ብላ እጇን ያዘቻት እና ደግፋት እህቷን ቅድም ወዳስተኙበት ክፍል ሄዱ በፀሎት ግንንንን የለችም።
ፅናት "እህቴ" አለችና ደነገጠች። ሊባኖስም "ተረጋጊ ሚጢጢዋ ኦፕራሲዮን ክፍል ነው ምትሆነው ኦፕራሲዮን ያረጓታል ብለሽኝ አደል እንዴ?" አለችና ጠቀሰቻት።ፅናት "ልክ ነሽ እሺ" አለቻት ከዛ እስቲ ነይ አረፍ በይ አለችና ወደ አንድ ብቸኛ ወንበረ ወሰደቻት። ፅናት በጣም የድካም እና የጭንቅ ስሜት እየተሰማት ነው ይህ የረሀብ እና የጭንቀቱ ምልክት ነው ሊባኖስም አውቀዋለች። "ስሚ ሚጢጢዋ አቅም አጥሮሻል እኮ ቆይ ምግብ ነገር ላምጣለሽ እዚሁ ጠብቂኝ እሺ ብላት" ሄደች።
ፅናት በጣም እርቧት ስለነበረ በፍጥነት ነው "እሺ ያለቻት። ከዛም ሊባኖስ እሮጥ እሮጥ ዱብ ዱብ እያለች ወደ ምግብ ቤቱ ሄደች። ሊባኖስ አሁንም ያንን ደብተረ ጥላው ነው የሄደችው ፅናት ሊባኖስ ከኮሊደሩ ወደ ደረጃው ስትወረድ ቀጣይ ገልፁን ለማንበብ ተጣደፈች።
እጇ በትንሹ ቢንቀጠቀጥም ከፈታ አየችው በጣም በትልልቅ ፅሁፍ ነው የተፅፈው ግን ይሄኛው የፊት ገልፁ ላይ እንደተጻፈው በሙንጭር ፅሁፍ አልተጻፈም ደብተሩን ብድግ አድረጋ ታፋዎቿ ላይ አስቀመጠችው እና አይኖቿን ወደ ደብተሩ ወረወረቻቸው።ፅሁፎቹ በጣም ተነባቢ ናቸው ነገር ግን አያምሩም ማንበብ ጀመረች።እንዲህ ይላል ...
"ሄዋኔ የምነግርሽን አድምጪ በመጀመሪያ ሰው ተሰባሪ ነውና ሰውን ሳይሆን ዘላለማዊ የሆነውን አምላክሽን እመኚ።ለስላሳው ልብሽን ለሸካራ ልብ ላለመስጠት የፈለግሽው አይነትን ሰው ከጎንሽ አድርገሽ ከእሱ ጋረ ትልቅ ህይወትን ለመመስረት እና ደስተኛ ለመሆን አምላክሽ ተማፃኝ ሁኚ ""
አቋምሽን ፣መልክሽን ፣አለባበስሽን በማየት የሚቀርብሽን አፍቃሪ ነኝ ባይ ሰው ቢመጣ ፈፅሞ ላለመሸወድ አሁንም ደግመሽ የፈጣሪሽ ለማኝ ሁኚ። ውዴ እኛ ሴቶች ከወንዶች በተፈጥሮም በአስተሳሰብም እንበልጣለን ደካማ ጎናችን እምነታችን ነው። ክፉ ሲያጋጥመን ይቀየራል ማለታችን የሆነው ይሁን የቀረው ይቅር ያፈቀርሽውን ሳይሆን ያስፈቀረሽን ፈጣሪ እንዲ ብለሽ ለምኚው አምላኬ ይህ ሰው የልቤን መሻት የሚያሞላልኝ ሰው እንደሆነ ልቤ ምስክር ናት በሙሉ ልቤ እንጂ በሙሉ አይኔ አላየውትም።
.
.
🥀..ክፍል 7 ቶሎ እዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀