በቅርብ የተዋወኳት ልጅ አለች። ናርዶስ ትባላለች። እድሜዋ ከ14 ብዙም የሚያልፍ አይደለም።
እንዴት ተዋወኳት?
ከትምህርት ቤት ስመለስ የማልፈው በነሱ በር ነው። ሁሌ በራቸው ላይ አያታታለሁ። ስታየኝ ፈገግ ትላለች። ላለማስከፋት ፈገግታዋን በስስ ፈገግታ እመልስላታለሁ። ትስቃለች።
አንድ ቀን በደጃቸው ሳልፍ በዚሁ ፈገግታ እየሮጠች ወደ እኔ መጣችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ። ጨበጥኳት። አመሰግናለሁ አለችኝ። ድምጿን ስሰማ ደነገጥኩ። ድምጿ እና መልኳ አይገናኝም። ጎርነን ያለ ድምጽ ነው ያላት። ያልጠበኩት ድምጽ ስለሆነ ትኩር ብዬ አየኋት። ፈገግ አለች። ፈገግ አልኩላት። ደስ አላት። እየሮጠች ወደ ቤቷ ገባች።
ሌላ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ ጠብቃ በተለመደው ፈገግታዋ ካስቆመቺኝ በኋላ ሂሳብ ብዙም ስለማይገባኝ እንድታስጠናኛ ፈልጋለሁ አለቺኝ። ድፍረቷ ገረመኝ ደስ አለኝም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ነገር አልገጠመኝም።
ጊዜ ስለሌለኝ ሰፋ ላለ ጊዜ ማስጠናት እንደማልችል እና ጥያቄዎች ካሏት ጥያቄዎቹን ልሰራላት እንደምችል ነገርኳት። ለተወሰነ ጊዜ በዚህ መንገድ በራቸው ላይ ሳስጠናት ቆየሁ።
የሆነ ቀን በደጃቸው ሳልፍ የነናርዶስ በር ላይ ግርግር አለ። ጠጋ ብዬ አየሁ። ናርዶስ ለያዥ ለገናዥ አስቸግራለች።
"ሴት አይደለሁም ወንድ ነኝ። ሴት ብላችሁ አትጥሩኝ ናርዶስ አይደለሁም።"
"አጭበርባሪ ነው ይሄ መንፈስ እያታለለ ነው...
"ፀበል የለሞ እንዴት...
"አንድ ሰው ጋር ደውሉ እንጂ...
እኔ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ። ናርዶስ...
ግቢያቸው ውስጥ አጥር ተደግፋ ወደ ቆመች ሴት ተጠጋሁና ናርዶስ ምን ሆና እንደሆን ጠየኳት።
"ያማታል! ጉብዝናዋ ላይ አሰሩባት። ቁንጅናዋ ላይ እንደዚህ አረጉባት ። ይኸው ትምህርቷን ካቆመች 3አመት ሆነ። እሷን ለማዳን ያልዞርንበት ሃኪም ቤት ያልተንከራተትንበት ፀበል የለም። ግን ምንም ለውጥ የለም።" እንባዋን በስሱ አፈሰሰችው። እንባዋን በመዳፏ ጠረገችና...
"ሁልጊዜም ከጠዋት እስከ 6 ሰዓት ደህና ትሆናለች። እንጫወታለን እናወራለን ብዙዙ እናወራለን። ድምጿ እንዴት እንደሚያምር። ምን ያደርጋል ደህንነቷ ከ7 ሰዓት አይዘልም። ውስጧ ያለው መንፈስ ይቀሰቀሳል። ድምጿ ይጎረንናል መንፈሱ ማጥመድ ከሚፈልገው ሰው ውጪ ማንንም አትቀርብም አታወራም።" ብላ ትክዝ አለች።
ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ።
እና እስካሁን ሳስጠና የነበረው እሷን ነው ወይስ እሱን ነው?
ቀጣዩ ክፍል 500 Like በኋላ ይቀጥላል