ውስጤን ደነዘዘኝ። ያልሞቀ አካሌን ላብ ላብ አለኝ። ብዬ ብዬ ደደብ መንፈስ ላስጠና¡ (ይሄን ቃል ውስጤ እንጂ አንደበቴ አላለውም። ምክንያቱም የሚተነፍስ በድን ሆኛለሁ።)
ልጅቷን አይዞሽ ብዬ ዞር ስል ከናርዶስ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጥን። ስታየኝ(ሲያየኝ) ፈገግ አለች። አለ። ማማተብ ፈለኩ።
ጣቴን መስቀልኛ ላጣምራት ስል እጄን አሰረኝ። እንዳላማትብ ቆለፈኝ
አሁንም የናርዶስ አይን አይኔ ላይ እንደተተከለ ነው። ማማተብ አቃተኝ። እኔን ስታየኝ ሊይዟት አቅም አነሳቸው መሰለኝ ለቀቋት። ፈገግታዋ እየጨመረ ተጠጋችኝ።
"እየጠበኩህ ስትቆይብኝ እኮ ...
ሰው ሁሉ ተኣምር የሚያይ ይመስል አፉን ከፍቶ ዙርያችንን ከቦ ይመለከተናል።
"ለምን ቆየህ?"
እ...
"መልስልኝ እንጂ! ለምን ዘገየህ? አንተን አይደል ስጠብቅ የነበረው።"
"ት ን ሽ ስ ራ በ ዝ ቶ ብ ኝ ነ ው!" አፌ ተንተባተበ። ፈቅጄ አልነበረም ቃል ከአፌ የወጣው። ማን አስገደደኝ? ማን አፌን ከፈተው? ማን በዚህ መንገድ እንድመላለስ እግሬን አስለመደው?
"ስለምን ትጎዳኛለህ? ላንተ ስል ስንቱን ትቻለሁ። የምረጋጋው ሳይህ ነው። አቅም የማገኘው ሳይህ ነው።"
በፍጥነት ገፍትሬያት አልፌያት ሄድኩ። አዳሬን እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ። እንዳፈጠጥኩ ዶሮ ጮኸ። እንዳፈጠጥኩ ወፎች ዘመሩ። እንዳፈጠጥኩ...
በተኛሁበት ልብሴ ፊቴን ሳልታጠብ ስራ ገባሁ። ማስተማር አይበለው! ሁኔታዬ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተለወጠ። እያስተማርኩ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። የተማሪው ፊት ሁሉ የናርዶስ ፊት መሰለኝ። ድምፃቸው ሁሉ ጎረነነብኝ።
"ሰርዬ እንዴ ሰር ምን ሆነህ ነው?"
"አረ ቢሮ ሰው ጥሩ ሰርዬ...
መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ?