ፒያሳ መብራት ሃይል ህንፃን ተሻግሮ ከአላፊ አግዳሚው ብር የሚለምኑ ልጆች ነበሩ። አለማመናቸው ትንሽ ፈጠራ የታከለበት ነው። ካርቶንና ምናምን በሚነድበት ምድጃ ላይ በሆነች የብረት ድስት ሽሮ ወጥ ጥደው ይንተከተካል። ህፃን ያቀፉ ሴቶች በሚያሳዝን ሁኔታ ድስቷን ዓይን ዓይን እያዮ አይጠፉም! እና አላፊ አግዳሚውን ወደወጡ እየጠቆሙ "ጋሸ ወጥ ሰርተን እንጀራ መግዣ አጥተን ነው ያለህን በእግዚአብሔር..." ይላሉ! ያው የሆነ የሚያሳዝን ነገር አለው። ሰወች ግማሽ መንገድ ደክመው ግማሹን እርዳን ሲሉ ትብብር እንጂ ልመና አይመስልም።
በተለይ አንዷ ቀይ ሸራፋ ልጅ በቃ በተደጋጋሚ ነው የምታጋጥመኝ። አንድ ቀን በዛው በተጣደው ወጥ አጠገብ አልፈን፣ የእንጀራ መግዣም ተጠይቀን ገዳም ሰፈር አካባቢ ወደነበረች ምግብ ቤት ሄድን። ምሳ አዘን ስንበላ ያች ቀይ ሸራፋ ልጅና አንድ ጎረምሳ ከች አሉ። "ፈጠን ያለ ጥብስና ቅቅል" አለች እሷ። ሁለት ሲንግል አለ ወንዱ! ከዚያ በኋላ ፒያሳን የምታዘወትሩ ሁሉ እንደምታውቁት ያች ድስት ከምድጃ ሳትወጣ እኔ ከአገር ወጣሁ😀 እና ምን ልል ነበር ...? ሰሞኑን የማስበው ነገር ሁሉ መሃል ላይ እየጠፋብኝ ተቸግሪያለሁ...! አወ አንዳንድ ነገሮች ይጣዳሉ እንጅ አይበስሉም! ምክንያት? አለመብሰላቸው የገቢ ምንጭ ነው!! የሆነ ሆኖ ፒያሳ ሲፈርስ ያች ድስት የት ተጥዳ ይሆን?
Alex Abraham