"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!… አንድ ነገር ልንገራችሁ! በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፡፡ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል፣ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል፣ ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል፣ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል።”
#ጋሽ_ስብሃት_ገብረእግዚአብሄር)
ብሩህ ሰኞ
ብሩህ ቀን ይሁንላች!!
መልካም ውሎ
#ጋሽ_ስብሃት_ገብረእግዚአብሄር)
ብሩህ ሰኞ
ብሩህ ቀን ይሁንላች!!
መልካም ውሎ