♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 8...🌹
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
"ለዚህ ነው ስነርቺኝ ያደርሽው !"
"ኪኪኪኪ እሱን አልክድም አርፌ እንደማልተኛ ታላቅ እህቴ ብዙ ግዜ ትነግረኝ ነበር"
"ሌላስ ማንም ነግሮሽ አያውቅም•••?"
"ሌላ ማለት•••?"
"ሌላ ማለት ••••?ሌላ ማለት••••? እንደኔ ባለ ፍሬ የሆነ ነዋ!"
"ካካካካካካ••••ታናሽ ወንድም ነው ያለኝ ግን አብሮኝ ተኝቶ አያውቅም!"
ስትለኝ •••" በለው በለው እቺ ልጅ ድንግል ነች ማለት ነው•••? እሄ ማለት ወንድ አላውቅም ማለት አይደል•••? ነው እንጂ ! ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል ፣ ገና ብዙ ስራ አለብህ ኤፍዬ!" አልኩ በልሆሳስ አጎንብሼ ጫማዬን እያጠለኩ።
"እ••? •ምን አልክ ኤፊ•••?"
"ወንድምሽ ካንቺ ጋር ያልተኛው ፈጣሪ ሲጠብቀው ነው፣ በእውነት እኔ ያልቻልኩትን እርግጫሽን አንድ ፍሬ ልጅ በምን አቅሙ ይቋቋመዋል!"
"ኪኪኪኪ ወሬ አለብህ ለማንኛውም ወንበሩ ላይ ቁጭ ብዬ ፀጉሬን ሳስተካክል ቁልፍና ቦርሳህን ትራስህ ስር አድርጌልሀለሁ ፣ አገኘኸው••••? " አለችኝ ሁለት እጆቿን ሽቅብ ሰቅላ እየተንጠራራች ። የጇን ወደላይ መወጠር ተከትለው እኔ ላይ የተቀሰሩትን ጡቶቿን ስመለከት ተኩሰው የሚመቱኝ ይመስል ልቤ ፍርስ ስትል ታወቀኝ።
"ጉድህ ፈለ ኤፍዬ ፍቅር መረቡን ጥሎ እያጠመደህ ነው! "አልኩ በልቤ አይኖቼን ጡትና ከጡቷ ስር ባለው ቀጭን ወገቧ ላይ እያንከራተትኩ ሳያት የተሰማኝ ስሜት ከዚህ ቀደም ተሰምቶኝ አያውቅም። የመረታት ፍርሀት ወረረኝ።
" አንስተኸዋል አደል•••? አለችኝ ደግማ ቁልፍ እና ቦርሳውን ወዳስቀመጠችበት እየተመለከተች።
"አዎ አንስቼዋለሁቆንጆ አመሰግናለሁ!"
"ኧረ ባክህ ••••! ያንተ ቆንጆማ አይደለሁም!"
"እና የማን ነሽ•••?"
"ኪኪኪኪ ለግዜው የማንም አይደለሁም የእናት ያአባቴ ብቻ!"
"እስከመቼ•••?"
"እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም!"
"እኔ ግን አውቃለሁ!"
"ምንድን ነው የምታውቀው•••? እስከመቼ እንደሆነ•••?"
"አዎ የኔ እስክትሆኚ ነው!"
"እ. ን. ዴ. ኪኪኪኪ ••• ያንተ እንደምሆን በምን አወቅክ•••?
" ውስጤ ነገረኝ!"
"ታድያ የኔስ ውስጥ ለምን አልነገረኝም•••?"
"ነግሮሻል ባክሽ ለመደበቅ እየሞከርሽ ነው!"
"ተው ባክህ እኔ እስካሁን ምንም የሰማሁት የውስጥም የውጪም ድምፅ የለም!"
"እሄው እኔ እየነገርኩሽ አይደል እንዴ•••?"
"ምን ብለህ•••?"
"የኔ ነሽ ብዬ ነዋ!"
"ኪኪኪኪ ጭራሽ ••••ከየኔ ነሽ የኔ ሁኚ አይቀድምም•••?"
"እሺ የኔ ሁኚ!"
"ለምን•••?"
"እንዴ እንዴት ለምን ስለወደድኩሽ ነዋ!"
"ኪኪኪ ባንድ ለሊት ትናንት ማታ እኮ ደስ አልሽኝ ብቻ ነበር ያልከው!"
"ደስ ያላለ ነገር ይወደዳል እንዴ ቃልዬ ደስ ስላልሽኝ እማ ነው የወደድኩሽ!"
"ትንሽ አልቸኮልክም•••?
"አዎ ቸኩያለሁ ምን ላድርግ ቃልዬ አሁን ተለይተሽኝ ወደ ግቢ ስትሄጂ አንዱ ላፍ የሚያደርግብኝ መስሎ ተሰማኝና ፈራሁ ለዛ ነው!" ።
"ተው ባክህ••••ኪኪኪ•••እስከዛሬ አንዱ ላፍ ያላደረገኝ አንተ እየጠበከኝ ነበር እንዴ?"
"አዎ እየጠበኩሽ ነበር ሁሉም እኮ የግራ ጎኑ ማን እንደሆነች ባያውቅም እየጠበቃት ነው የሚኖረው!"
"ላፍ ያልተደረኩት ነው ያልኩህ ባክህ!"
"ላፍ ያልተደረግሽው እማ ያው ፈጣሪ እኔ እስከማገኝሽ ድብቅ ክልል አድርጎልኝ ነዋ!"
"እንደዛ ካመንክ ታድያ ታድያ አሁን ለምን ፈራህ!?"
"ያው ሰውኛ አስተሳሰቤ ካየሁሽ በኋላ ሀያ አመት ሙሉ ያስቀመጠልኝን በሀያ ደቂቃ የማጣሽ እየመሰለኝ ነዋ!"
"ለዚህ ነዋ ሁሉ ነገርህ ሱሪ ባንገት የሆነው!"
"አቦ ይሄን ያዲስ አበቤዎች ተረትሽን ተይልና ወደዛ የምን ሱሪ ባንገት ነው ሱሪ እማ በእግር እንጂ በአንገት ላይ እንዴት ሆኖ ይሆናል•••? የማይሆነውን!"
"ኪኪኪ አታላግጥ እሺ ! ምን እንዳልኩ በደንብ ታውቀዋለህ ሁሉ ነገርህ ጥድፍድፍ አለኮ!"
"ለምሳሌ ምን••?"
"ምነው ከተገናኘን በኋላ የሆነው ሁሉ በዚች አጭር ግዜ እንዲህ የሚሆን ይመስላል!"
"ምን ሆነና ነው•••? አብረን እራት ስለ በላን•••? አብረን አንድ ክፍል ውስጥ ስላደርን•••?"
"ምነው ከዛ በላይም ፈልገህ ነበር•••?"
"አቦ ብፈልግማ ማን ከልክሎኝ •••? አንቺ•••?"
"በነገራችን ላይ ኤፍዬ ጭዋነትህን ወድጄዋለሁ፣ አመሰግናለሁ እሺ ኤፍዬ!" እያለች ጠጋ ብላ ጉንጬን ሳም ስታደርገኝ ከንፈሬን አጣብቃ ምላሴን የወሰደችው ይመስል መልስ መስጠት ተስኖኝ ፍዝዝ ድንግዝ ብዬ ሳያት •••
"ተነስ እንውጣ ባክህ ታለምጣለህ አይደል •••? ለምንድን ነው እንደዚህ የምታየኝ•••? ተነስ እንውጣ!" አለችኝ።ሁኔታዬ ግን ማልመጥ ሳይሆን እውነት ነበር። ለሷ እያለመጥኩ መስሎ ስለታያት ደስ ቢለኝም ስትስመኝ የተሰማኝ ስሜት ግን የተለየ ነበር እራሴን ታዘብኩት።
እሷ ከፊት እኔ ከጀርባዋ ተከታትለን ከክፍሉ ወጣን። ማታ ያየሁት የቃል ውበት እንደጥዋቷ ፀሀይ ቀስ እያለ የሚፈልቅ፣ ቀስ እያለ የሚሞቅ፣ ቀስ እያለ የሚፈካ ይመስል አብሪያት በቆየሁ ቁጥር ይበልጥ ውብ እየሆነችብኝ ግራ ተጋባሁ ፣ ምናልባት መውደዴ እየጨመረ፣ እሷን የማይበት መነፅርም እየተቀየረ ይሆን•••?
ዛሬውኑ አሁኑኑ የኔ ትሁን አትሁን ቁርጤን ማወቅ ፈለኩ።
ቁርስ አብረን እየበላን ነው።
"ቃልዬ!"
"ወዬ ኤፊ!"
"ቆይ አንድ ወንድ የፍቅር ጥያቄ ለማንሳት ፣ ማለት•••የወደዳትን የኔ ሁኚ ብሎ ለመጠየቅ ቸኮልክ የማይባለው ከተዋወቃት ከስንት ቀን በኋላ ሲጠይቅ ነው•••?"
"ኪኪኪኪ እኔ እንጃ!"
"ካላወቅሽ ታድያ ለምን ቸኮልክ አልሽኝ•••?"
"ስለቸኮልክ!"
"እባክሽ አትቀልጂ ቃሌ!"
"ኤፊ ሙት እየቀለድኩ አይደለም!"
"ለማንኛውም እኔ የልቤን ተናዝዣለሁ አንቺ የማሰቢያ ግዜ ከፈለግሽ እሺ!"
"እእእእእ በችኮላ የተሰነዘረ ጥያቄ ስለሆነ እንዳልሰማሁህ አስበው፣ ለኔ ብቻ ሳይሆን ላንተም የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግሀል!"
"ምንድን ነው የማስበው •••? የምን ግዜ•••?"
"እኔን የማወቂያ!"
"ከዚህ በላይ ላውቅሽ አልፈልግም!"
"እኔ ግን እፈልጋለሁ!"
"እሺ የናትሽ ስም ማነው•••? ስላት ሳቋን ለቀቀችው•
"ምን ላድርግ ቃልዬ ስምሽን ከነአባትሽ ከመታወቂያሽ ላይ አውቂያለሁ፣ የቀረኝ የናት ስም ነው ብዬ እኮ ነው!"
"እህህ አየ አንተ እና የቤተሰብ ስም ማወቅ ታድያ እኔን ማወቅ ማለት ነው ••••? እ ኤፊ የምር እንደዛ ነው የምታስበው•••?"
"ሀይ••••! ታድያ ምንሽን እንዳውቀው ነው የምትፈልጊው?
ከ 50 ላይክ ቡኋላ ክፍል 9 ይለቀቃል🌹