እንዴ ቅዱስ ኤፍሬም አገላለፅ ሁለት ዓይነት እሳቶች አሉ ::
አንደኛው እሳት ቅዱስ ቁርባን ሲሆን :-እርሱም የኃጢያት አረምን ከሰውነት አቃጥሎ የሚያጠፋ መለኮታዊ እሳት ነዉ ::ሁለተኛው ኃጢያት ነዉ እርሱም ሰውነትን የሚያጠፋ እሳት ነዉ ::ከዚህ ከሚያጠፋ እሳት መለኮታዊ እሳት የሆነው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንደሚታደገን ሲናገር እንዲህ ይላል :-
"ከመለኮታዊው እሳት ከቅዱስ ቁርባን በተቀበልኩ ጊዜያት የእኔ ጸሎት በሰውነቴ ህዋሳት ውስጥ በቅለው ያሉትን የኃጢያት አረሞች አቃጥሎ ያጠፋልኝ ዘንድ ነዉ ::ወንድሞቼ ሆይ! በሰውነቴ ህዋሳት ውስጥ ያለውን የኃጢያት እሳት በአምላክ ክቡር ደም አጠፋሁት ::ይህ የጌታዬ ክቡር ደም ሰውነቴን የኃጢያት እሳት እንዳያጠፋው ይጠብቀዋል " ብሏል ::
በሌሊት የሰይጣን ጦር ስለሚበረታ ሠይጣንን እና ፈቃዱን ለማራቅ ሲል ቅዱስ ኤፍሬም መላ ሰውነቱን እና አከባቢውን ሁሉ በትምህርተ መስቀል ያማትብ ነበር :: እዲህ ስለማድረጉም :-
"በሌሊት ወደ እኔ በመቅረብ ከንጽህናየ እንዳያሳድፈኝ የቅድስት ሥላሴን ስም እየጠራሁ በጌታየ በመድሃኒቴ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ እጸ መስቀል በህዋሳቶቼ ሁሉ ላይ አማትባለሁ ::ጌታዬ ሆይ ክብር ለአንተ ይሁን የቅድስት ሥላሴ ስሙ ኃይል እና ብርታት እንዴት ታላቅ ነዉ! ስምህ በወጣትነቴ,በእርጅናየ ብርታት ሆነኝ በእድሜ ዘመኔ ሁሉ ስምህ ጽኑ ግንብ ሆነኝ" ብሏል ::
(የትሕርምት ሕይወት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እንዳስተማረው /መምህር ሽመልስ መርጊያ እንደተረጎመው )